Logo
FastMereja
ሴንቸሪ ፕሮሞሽን የ35ኛውን “ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ 2019” ሊያካሂድ ነው!
#fastmereja :-ሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ 35ተኛዉን ታላቅ የአዲስ አመት የንግድ ትርኢት እና ባዛር ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለ21 ተከታታይ ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል እና በመስቀል አደባባይ እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በሰጡት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።

ባለፉት 27 ዓመታት ከ60 በላይ ታላላቅ ሁነቶችን እና 34 የንግድ ትርኢቶችን ያዘጋጀው ሴንቸሪ ፕሮሞሽን፤ የዘንድሮውን የ2019 ዓ.ም. የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ለማዘጋጀት በኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት የወጣውን ጨረታ በማሸነፍ ወደ ተለመደው ስራው መመለሱን አስታውቋል።

በዚህ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ላይ ከ500 በላይ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ የንግድ ወኪሎች እና ልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

በዚህ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ላይ የተለያዩ እጣዎች የተዘጋጁ ሲሆን በዚህም ላቅ ያሉ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል 1ኛ ዕጣ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ ዘመናዊ አውቶሞቢል (መኪና) 2ኛ ዕጣ የቢ.ኤም.ደብሊው (BMW) ኤሌክትሪክሞተር ሳይክል እንዲሁም 3ኛ ዕጣ የኤሌክትሪክ ብስክሌት እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።

በተጨማሪም ከነሐሴ 16 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ በየምሽቱ የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሚቀርቡ ሲሆን፤ ከነሐሴ 16 እስከ 21 ባሉት ቀናት ደግሞ ለአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት የተዘጋጁ ልዩ የባህል ጭፈራዎችና የየዕለቱ የሽልማት ውድድሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
📷 ከበደ መክብብ

23 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.