5 months ago
🌍 በአፍሪካ ዋንጫ በስታዲየም ተመልካቾች ቁጥር ሪከርድ ተሰበረ!
#ethiopia | በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፣ ገና ፍፃሜው ሳይደረስ በታሪክ ከፍተኛው የተመልካች ቁጥር የተመዘገበበት ውድድር በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
📊 አዲሱ የሪከርድ ቁጥር
ውድድሩን ለማጠናቀቅ ገና ሶስት ወሳኝ ጨዋታዎች እየቀሩት፣ እስካሁን ባለው መረጃ 1,116,959 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) ተመልካቾች በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታዎቹን ታድመዋል። ይህም በአህጉሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛው የተመልካች ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።
🚀 ለሪከርዱ ስኬት ምክንያቶች
ለዚህ አስደናቂ ቁጥር መመዝገብ በዋናነት የሚጠቀሱት፦
* የሞሮኮ ዘመናዊ ስታዲየሞች፦ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዙና ለተመልካች ምቹ የሆኑ መሠረተ ልማቶች።
* የደጋፊዎች ፍቅር፦ የአፍሪካ ደጋፊዎች ለብሔራዊ ቡድኖቻቸው ያላቸው ከፍተኛ ስሜት።
* አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፦ የውድድሩን ድምቀት የጨመሩ ዲጂታል አሰራሮች።
⏳ ተጠባቂ ፍልሚያዎች
ይህ ሪከርድ በቀጣይ በሚደረጉት ታላላቅ ጨዋታዎች ይበልጥ እንደሚጨምር ይጠበቃል፦
* ግብፅ ከ ሴኔጋል (ለፍፃሜ ለማለፍ የሚደረግ ትንቅንቅ)
* ሞሮኮ ከ ናይጄርያ (ለፍፃሜ ለማለፍ የሚደረግ ትንቅንቅ)
* ታላቁ የፍፃሜ ጨዋታ
እነዚህ ተጠባቂ ጨዋታዎች በስታዲየም የሚገኘውን የተመልካች ቁጥር ወደ ማይገመት ደረጃ ያደርሱታል ተብሎ ይታመናል። አፍሪካ በሞሮኮ ምድር የእግር ኳስ ጥበቧንና አንድነቷን ለአለም እያሳየች ትገኛለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#የአፍሪካዋንጫ #ሞሮኮ #እግርኳስ #ሪከርድ #ግብፅ #ሴኔጋል #ናይጄርያ #afcon #morocco #footballrecords #caf

6 months ago
ማንችስተር ዩናይትድ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል
#ethiopia | የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች በአፍሪካ ያፈሯቸው ደጋፊዎች ብዛት ይፋ ሲደረግ የእንግሊዙ ማንችስተር ዩናይትድ ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።
በመላው አለም ከ1.1 ቢሊዮን በላይ ደጋፊዎችን ማፍራት የቻለው ክለቡ በአፍሪካ የደጋፊዎቹ ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ይገኛል ተብሏል።
ከዚህ በፊት በአህጉሪቱ በደጋፊዎች ብዛት ቼልሲ ቀዳሚ የነበረ ሲሆን አሁን ቦታውን ለዩናይትድ አስረክቧል።
ዩናይትድ በናይጄርያ እና ኬኒያ ከፍተኛ የደጋፊ ቁጥር ማፍራቱንም ነው የተገለፀው።
አርሰናል ከዩናይትድ በመቀጠል በአፍሪካ ሁለተኛው ከፍተኛ ደጋፊ ያፈራ ክለብ ሆኗል።
ክለቡ የቀድሞ የክለቡ ኮኮብ ቴሪ ሄነሪ እና አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በበርካታ አፍሪካዊያን ተወዳጅ መሆናቸው ተከትሎ ነው ከፍተኛ ደጋፊ ማፍራት የቻሉት ተብሏል።
ለበርካታ አመታት ከፍተኛ ደጋፊዎችን በማፍራት ቀዳሚ የነበረው ቼልሲ ሶስተኛ ደረጃ የተቀመጠ ሲሆን የስፔኖቹ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ክለቦች ሆነዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ምን ማለት ይቻላል?
#ethiopia | ሀገር ሆነው አንድም የመንገደኞች አውሮፕላን የሌላቸው ሀገራት እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቃለን?
የ100 አመት እድሜ ያለው የአቬሽን ዘርፉ በየጊዜው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ሀገራት ዘርፉ ያስተዋወቀውን የመንገደኞች አውሮፕላን መጠቀም ከጀመሩም ዘመናት አስቆጥረዋል።
ይህ ቁጥር ስንመለከት ብዙዎቻችን እንዴት ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።
100 አመት ባስቆጠረው ዘርፍ በመላው አለም አሁን ያሉት የመንገደኞች አውሮፕላን ብዛት 39ሺህ ብቻ መሆናቸው የአያታ መረጃ ይነግረናል።
ይህ መረጃ 2024/2025 መረጃ ነው።
በአለም ትላልቅ ብለን የምንጠራቸው ሀገራት ሳይቀሩ በእጃቸው ያላቸው የመንገደኞች አውሮፕላን ብዛት ከ200 እንደማይበልጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ለአብነት ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገራት እንኳንስ አውሮፕላን ይቅርና አየር መንገድ እንኳን እንደሌላቸው ነው መረጃው የሚነግረን።
ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገራት ከ20 በላይ የመንገደኞች አውሮፕላን ያላቸው ሀገራት ከአምስት አይበልጡም።
ከአፍሪካ ሀገራት በኢትዮጵያ ልክ የሚደርስ አንድም ሀገር የለም።
ኢትዮጵያ በያዘችው የመንገደኞች አውሮፕላን ብዛት ከአፍሪካ ብቻም ሳይሆን ከአውሮፓ ሀገራት ጭምር እንደምትበልጥ መረጃው የሚጠቁመው።
አለማችን ካላት ጠቅላላ የመንገደኞች አውሮፕላ ከፍተኛው ቁጥር የሚገኘው በሰሜን አሜሪካ ሲሆን አሜሪካና ካናዳ ከፍተኛውን ቁጥር ይወስዳሉ።
የአውሮፓ ሀገራት እንደዚሁም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እያንዳንዳቸው ከ200 አስከ 400 የሚደርስ የመንገደኞች አውሮፕላን እንዳለቸው ተነግሯል።
ጥቂት የኤዢያ ሀገራት እንደ ቻይና ጃፓን ሲንጋፖር እና ህንድ ያሉትም በአውሮፓ ልክ የሚደርስ አውሮፕላን አላቸው።
በአፍሪካ ከ50 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላቸው ለገራት አንድም የመንገደኞች አውሮፕላን እንደሌለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተፈጥሮ ሀብቷ የበለጸገችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄርያ በተለያዩ ምክንያቶች ዛሬም ድረስ አንድም የመንገደኞች አውሮፕላን የላትም።
ጎረቤታችን ኤርትሪያም ብትሆን በእጇ ያለው አንድ የኪራይ አውሮፕላን ብቻ ነው።
ግብጽ፣ ኬኒያ፣ ሞሮኮና አልጄሪያ እያንዳንዳቸው ከ20 በላይ የመንገደኞች አውሮፕላን እንዳላቸው ይታወቃል።
በአፍሪካ ከ100 በላይ የመንገደኞች አውሮፕላን ያላት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው በመንገደኞች አውሮፕላን ብቻም ሳይሆን በሁሉም መስኮች እንደሆነ ነው የተገለጸው።
የመንገደኞች አውሮፕላን ስንል አነስተኛ አውሮፕላኖች የጭነትና ወታደራዊ አውሮፕላኖችን አይጨምርም።

7 months ago
ናይጄርያ ጋቦንን 4 ለ 1 በማሸነፍ ለጥሎ ማለፍ ፍጻሜ ደረሰች
#ethiopia | በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከምድባቸው ምርጥ 2ኛ ሆነው የጨረሱ አራት ሀገራት ለኢንተርኮንቲኔንታል የመጨረሻ የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።
ናይጄርያ ጋቦንን በማሸነፍ ለጥሎ ማለፍ ፍጻሜ መድረሷን አረጋግጣለች።
ሁለቱ ቡድኖች የተገናኙበት መደበኛ 90 ደቂቃ አንድ አቻ ቢጠናቀቅም አሸናፊውን ለመለየት በተጨመረው 30 ደቂቃ ናይጄርያ 4 ለ 1 አሸንፋ ለመጨረሻው ጨዋታ ደርሳለች።
በሞሮኮ በተደረገው ጨዋታ ቪክቶር ኦሲሚህን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ኦኮር አዳም እና ቺድራ ኢጁክ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
ማሪዮ ሌሚና የጋቦንን አንድ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።
በአንተነህ ሲሳይ

9 months ago
ኢትዮጵያ 2400 ሚሊየነሮች አላት
በቀጣዩ በአፍሪካ የሚሊየነሮች ቁጥር በ65 በመቶ ይጨምራል።በአህጉሪቷ 25 ቢሊየነሮች አሉ፣ የሚሊየነሮች ብዛት ግን 122 ሺ 500 ደርሷል።
ደቡብ አፍሪካ 41ሺ 100 ሚሊየነሮች ስትመራ ግብፅ 14ሺ 800፣ ሞሮኮ 7ሺ 500፣ ናይጄርያ 7ሺ 200 ኬንያ 6ሺ 800 በመያዝ ከአንድ እስከ 5 ያለውን ቦታ ይዘዋል።
በተጨማሪ 5ቱ አገራት ከአህጉሪቱ የሚሊየን ዶላር ባለሃብቶች 63% የሚሸፍኑ ሲሆን ቢሊየነሮቻቸው 88% ይይዛል።
ኢትዮጵያ በዶላር የሚሊየነር ብዛት ከአፍሪካ 10 ደረጃን ይዛለች ሲል ሄንሌ ኤንድ ፓርትነርስ የ2025 የአፍሪካ ባለፀጎች ሪፖርት ሲያወጣ ነው የጠቀሰው።
Seledadotio

#ethiopia | በቀጣዩ በአፍሪካ የሚሊየነሮች ቁጥር በ65 በመቶ ይጨምራል።
በአህጉሪቷ 25 ቢሊየነሮች አሉ፣ የሚሊየነሮች ብዛት ግን 122 ሺ 500 ደርሷል።

በየጨማሪ 5ቱ አገራት ከአህጉሪቱ የሚሊየን ዶላር ባለሃብቶች 63% የሚሸፍኑ ሲሆን ቢሊየነሮቻቸው 88% ይይዛል።

#kgethiopia

Sponsored by
Surafel
10 months ago
አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው።
መጀመሪያ በቴያትር የታዩት በመንግስቱ ለማ በተጻፈው ያላቻ ጋብቻ ሲሆን ከዚያ በአንዳንድ እንግሊዝኛ ትርኢት (The game of chess, ‘Waiting for Godot’) እንዲሁም በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ተጫወቱ።
አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) ለታሪክ የሚተላለፉ ህያው ስራዎች ሰርቷል እስቲ ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ በጥቂቱ እንያቸው፤ በሃገር ውስጥ ካለው ታዋቂነትና ለሙያው ካደረገው አስተዋጽኦ ለመጠቀስ ያህል ፡-
በቤተኪነጥበባት ወቴአትር፡-
ያላቻ ጋብቻ ተዋናይ
ሮሚዎባ ዡልየት ተዋናይ
ጠልፎ በኪሴ ተዋናይም አዘጋጂም
ዳንዴው ጨቡዴ ››
ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ (በእንግሊዝኛ) ተዋናይ
ኦቴሎ (በአንግሊዝኛ) ተዋናይም አዘጋጂም
አዳ ኦክ አራክል (በእንግሊዝኛ)ከሎ.ጸ.ገ.መ ተዋናይ
በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ(ብሔራዊ) ቴአትር፡-
የበጋ ሌሊት ራዕይ ተዋናይ
አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ተዋናይ
እናት ዓለም ጠኑ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
ዋናው ተቆጣጣሪ ተዋናይ
ጠያቂ ተዋናይ አዘጋጅ
በቀይካባ ስውር ደባ አዘጋጅ
ተሓድሶ አዘጋጅ
የአዘውንቶች ክበብ አዘጋጅ ተዋናይ
በሃገር ፍቅር ቴአትር፡-
ጠልፎ በኪሴ አዘጋጅ/ተዋናይ
የወፍ ጎጆ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
የቬኒሱ ነጋዴ ተዋናይ
ናትናኤል ጠቢቡ ተዋናይ
ድብልቅልቅ ተርጓሚ/ ተዋናይ
ማዕበል ተርጓሚ አዘጋጅ
በፊልም በሃገርና በዓለም አቀፍ፡-
ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር
ሻፍት ኢን አፍሪካ
ጉማ
ዚ አፍሪካን ስፓይ
ዜልዳ
አፍሪካ
ዘግሬቭ ዲገር
ዘ ግሬት ሪቤሊየን
እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምሃራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገ ኛል፡፡
በትርጉም በኩልም ደበበ ከቴአትር፡-
ያልታመመው በሽተኛ
ድብልቅልቅ
ጎርፉ
ከመጽሐፍ ደሞ
የዳዊት ወልደጊዮርጊስን
የደም እንባ
የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ
የእምነቴ ፈተና
ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሶስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ/ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኘ፡፡
በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መስራች ፕሬዛዳንት በመባል ይጠራል፡:
ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡
ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይሀን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡
ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ኡጋንዳ፤ኬንያ፤ማላዊ፤ኮንጎ ብራዛቪል፤አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤አይርላንድ፤ብራዚል፤ሰሜን አሜሪካ፤እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ካናዳ ይገኙበታል፡፡
ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ገዢውን ፓርቲ ያንበረከኩና ቅንጅትና ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡
ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡
ጋሽ ደቤ ጋደኛም ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።
ነፍስ ይማር
viaጌጡ ተመስገን

የኪነ ጥበቡ ዋርካ አርፈዋል
#ethiopia | አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በሕክምና በተለያዩ ሆስፒታሎች ይከታተሉ ነበር።
***
ጋሽ ደቤ !

እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምህራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገኛል፡፡
በትርጉም በኩልም ደበበ ከቴአትር፡-
ያልታመመው በሽተኛ
ድብልቅልቅ
ጎርፉ
ከመጽሐፍ ደሞ
የዳዊት ወልደጊዮርጊስን
የደም እንባ
የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ
የእምነቴ ፈተና
ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሦስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤ በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኝቷል፡፡
በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መሥራች ፕሬዚዳንት በመባል ይጠራል፡:
ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡
ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይህን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡
ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ ኡጋንዳ፤ ኬንያ፤ማላዊ፤ ኮንጎ ብራዛቪል፤ አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤ አይርላንድ፤ ብራዚል፤ ሰሜን አሜሪካ፤ እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ ካናዳ ይገኙበታል፡፡
ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ቅንጅትን ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡
ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡
ጋሽ ደቤ ጋደኛም፤ ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።

11 months ago
በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ ለፍጻሜ ደረሰች
#ethiopia | ለ13ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ሞሮኮ ጋናን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሰች፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ 90 ደቂቃውን አንድ አቻ አጠናቀዋል፡፡ ኡዝራዎይ ለሞሮኮ ንያምክያ ደግሞ ለጋና ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተጨመረው 30 ደቂቃ ግብ ባለመቆጠሩ በተሰጠው መለያ ምት ሞሮኮ 4 ለ 2 አሸንፋለች፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ በተከታታይ ለፍጻሜ የደረሰችበትን ውጤት አስመዝግባለች፡፡
እሑድ በሚደረገው ፍጻሜ ሞሮኮ ከ9 ጊዜ ሻምፒዮኗ ናይጄርያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#africa #ebcsport #morroco

ናይጄሪያውያን እንደራሳቸው የሚያዩት የአፍሪካውያን ኩራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን ሁለት ጊዜ ወደ ናይጄሪያ ሌጎስ የበረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በናይጄርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካንትሪ ማኔጀር ፍሬህይወት መኮንን ተናግረዋል።
ይህም አየር መንገዱ በሳምንት ወደ ናይጄሪያ የሚያርገውን የበረራ አገልግሎት ወደ 31 አሳድጎታል።
ናይጄሪያውያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ መብረር ምርጫቸው ነው ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት አዲስ በተጨመረው የመጀመሪያው የበረራ አገልግሎት አውሮፕላኑ ሙሉ ሰው ይዞ እንደነበር ጠቁመዋል።
አሁን አዲስ የተጀመረው በረራ 3ቱ ከናይጄሪያ ማታ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ጧት የሚገባ ሲሆን አራቱ ከናይጄሪያ ጧት ወጥቶ ከሰዓት አዲስ አበባ የሚገባ ነው ብለዋል።
አዲሱ የበረራ አገልግሎት ከናይጄሪያ ወደ ህንድ ለሚጓዙ መንገደኞች አዲስ አበባ ገብተው በአጭር ጊዜ ቆይታ በትራንዚት ወደ ህንድ መብረር የሚያስችላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከሌጎስ ጧት፣ ቀትር እና ምሽት ወደ አዲስ አበባ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት በመኖሩ ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት መጠቀም እንደሚችሉም ተገልጿል።
በላሉ ኢታላ