ናይጄሪያውያን እንደራሳቸው የሚያዩት የአፍሪካውያን ኩራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን ሁለት ጊዜ ወደ ናይጄሪያ ሌጎስ የበረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በናይጄርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካንትሪ ማኔጀር ፍሬህይወት መኮንን ተናግረዋል።
ይህም አየር መንገዱ በሳምንት ወደ ናይጄሪያ የሚያርገውን የበረራ አገልግሎት ወደ 31 አሳድጎታል።
ናይጄሪያውያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ መብረር ምርጫቸው ነው ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት አዲስ በተጨመረው የመጀመሪያው የበረራ አገልግሎት አውሮፕላኑ ሙሉ ሰው ይዞ እንደነበር ጠቁመዋል።
አሁን አዲስ የተጀመረው በረራ 3ቱ ከናይጄሪያ ማታ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ጧት የሚገባ ሲሆን አራቱ ከናይጄሪያ ጧት ወጥቶ ከሰዓት አዲስ አበባ የሚገባ ነው ብለዋል።
አዲሱ የበረራ አገልግሎት ከናይጄሪያ ወደ ህንድ ለሚጓዙ መንገደኞች አዲስ አበባ ገብተው በአጭር ጊዜ ቆይታ በትራንዚት ወደ ህንድ መብረር የሚያስችላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከሌጎስ ጧት፣ ቀትር እና ምሽት ወደ አዲስ አበባ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት በመኖሩ ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት መጠቀም እንደሚችሉም ተገልጿል።
በላሉ ኢታላ

11 months ago