12 months ago
በራሴ መቅጣት ልቻል
#ethiopia | በማስተዳድራቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን በራሴ መቅጣት እንድችል የመንገድ ሀብት አጠቃቀም ደንብ አዘጋጅቻለሁ ሲል የአዲስ አበባከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ
በ2017 በጀት አመት 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው በ2017 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው የመንገድ ሀብቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም በትራፊክ አደጋ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡
በበጀት ዓመቱ በመንገድ ሀብት ላይ 195 የትራፊክ አደጋ ሲደርስ ከደረሰው አደጋ 154 በቀለበት መንገዶች እንዲሁም 41 ከቀለበት መንገድ ውጪ ባሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
በ2017 ዓ.ም በደረሰው አደጋ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ሊደርስ ችሏል፡፡
በመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት በህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ በባለስልጣን መስሪያቤቱ ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን በራሱ መቅጣት የሚችልበትን የመንገድ ሀብት አጠቃቀም ደንብ ባለስልጣኑ አዘጋጅቶ በፍትህ ቢሮ ምልከታ እየተደረገበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ደንቡ ሲፀድቅ መንገዶች ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ባለስልጣኑ በራሱ ለመቅጣት ፍቃድ ስለሚያገኝ ለሚያከናውነው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን የቁጥጥር ስራ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
#kgethiopia

1 year ago
አሜሪካና ቻይና በቲክ ቶክ ላይ ስምምነት ደረሱ !!
#ethiopia | ዋሽንግተንና ቻይና በቲክ ቶክ ባለቤትነት ማዕቀፍ ላይ ስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል ።
በድርድሩ የተሳተፉት የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት እንዳስታወቁት ቲክቶክ በአሜሪካ ያለውን የባለቤትነት ድርሻ በተመለከተ በማድሪድ የተደረገው ወይይት አመርቂ ውጤት አስገኝቷል።
በማድሪድ የተደረገው የንግድ ንግግር በቲክ ቶክ ላይ ለአሜሪካ ባለቤትነት መንገድ ለመክፈት ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የፊታችን አርብ ስምምነቱን ያጸናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቻይና በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ከመስጠት መቆጠቧን ድርድሩን ተከትሎ የወጣው መረጃ ያሳያልል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካና ቻይና ድርድር እና ቲክቶክ
#ethiopia | በቻይናውያን ባለሀብቶች ባለቤትነት የተያዘው ቲክቶክ በአሜሪካ ገዢ እየፈለገ ባለበት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ እና የቻይና ባለሥልጣናት በስፔን የንግድ ድርድር ማድረግ ጀምረዋል።
ድርድሩ የሚመራው በአሜሪካው የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት እና የቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሂ ላይፌንግ ሲሆኑ፣ በሁለቱ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባላቸው አገራት መካከል የንግድ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ቲክቶክ እንዲታገድ ሲወተውቱ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ይህንን አቋማቸውን በመቀየር ለሦስት ጊዜ ያህል መተግበሪያው የሚታገድበትን ጊዜ አራዝመዋል።
ትራምፕ እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች እንዳሉት "እንዲሞት ልንተወው [ቲክቶክን] እንችላለን። ወይንም ደግሞ... አላውቅም። ሁኔታዎች አሁን በቻይና ላይ የተመሠረተ ነው። ብዙም ግድ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም" ብለዋል።
ቲክቶክ በአሜሪካ የሚታገድበት የመጨረሻው ቀን ረብዕ ሲሆን፣ ለአራተኛ ጊዜ ሊራዘም ይችላል የሚል ተስፋ አለ።
ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገዢ እስኪገኝ ድረስ የሚዘጋበትን ቀን ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ መተግበሪያው በመላው ዓለም ቢሊዮኖች የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት።

ኢኩይቲ(equity) ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ በፋይናንስ ሴክተሩ ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳየ !!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን ከኢኩይቲ(equity) ባንክ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ጀምስ ምዋናጊ ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ በፋይናንስ ሴክተሩ መሰማራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ይደረግለታል።
የኢኩይቲ ባንክ ስራ አስፈጻሚ ጀምስ ምዋናጊ (ዶላር/ር) የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጪ ባለሀብቶች ክፍት ማደርጉ ምቹ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርገው ኢንቨስትመንት ለሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ የውጭ ኩባንያዎች ምሳሌ መሆን እንደሚፈልግጊእንደሚፈግ ገልጸዋል።
ኢኩይቲ ባንክ ኬንያ እና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ረጅም ልምድ ያለው ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም ነው።

Sponsored by
Surafel
1 year ago
የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ተቀየረ ⵑⵑ
#ethiopia | የቴስላ እና የ SpaceX ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኤለን መስክ፣ በዓለም እጅግ ባለጸጋነት ማዕረግን ለኦራክል ኩባንያ መስራች ለሆኑት ላሪ ኤሊሰን አስረክበዋል።
ይህ ለውጥ የተከሰተው ኦራክል ባወጣው ጠንካራ የገቢ ሪፖርት ምክንያት ነው። የኦራክል አክሲዮን ዋጋ በ41 በመቶ በመጨመሩ፣ የላሪ ኤሊሰን ሀብት በአንድ ቀን ውስጥ 101 ቢሊዮን ዶላር እንዲያድግ አድርጎታል።
ይህም በታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የአንድ ቀን የሀብት ጭማሪ ነው።
አሁን ላይ የላሪ ኤሊሰን ጠቅላላ ሀብት 393 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኤለን መስክ ሀብት ደግሞ 385 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል።
የኦራክል የገቢ ዕድገት ዋነኛው ምክንያት ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ በሚያገለግሉ አገልግሎቶቹ ላይ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ነው። ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ አብዮት የሀብት ደረጃዎችን እንደገና እየቀየረ ነው።

በበጀት እጥረት ኢራቅ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አልተገኘችም
#ethiopia | የገንዘብ ሚኒስቴር ገንዘብ ባለመልቀቁ ምክንያት ኢራቅ በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው ቁልፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ መገኘት እንዳልቻለች አንድ ባለስልጣን ሐሙስ ዕለት ገለጹ።
የቴክኒክ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ናጅላ አል-ዋኤሊ ለሻፋቅ ኒውስ እንደተናገሩት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባው ጉባኤ የሚያስፈልገውን በጀት አላቀረበም።
ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሺያ አል-ሱዳኒ የአየር ንብረት ፖሊሲ በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለኢራቅ የ2025 የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP30) ልዑክ ገንዘብ መመደባቸውን አክለዋል።
COP30 የሚካሄደው በ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ስምምነት ስር በአዲስ አበባ በተከፈተው የአየር ንብረት ሳምንት 2025 ጉባኤ ማግስት ነው። ይህ ጉባኤ የኃይል ሽግግር እና የአየር ንብረት ፋይናንስን ለመወያየት መድረክ ሆኖ ያገለግላል።
አል-ዋኤሊ አክለውም፣ “የድርድር ቡድኑ ኢራቅን እና ኢኮኖሚዋን ለመከላከል በ COP30 ላይ ይሳተፋል።”

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኤርባስ ኤ350-1000 ግዥ 153 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አገኘ
#ethiopia | አየር መንገዱ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ለመግዛት በዩኬ ኤክስፖርት ፋይናንስ (ዩኬኢፍ) የተደገፈ የ153 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ነው የተፈራረመው።
ይህ ስምምነት አየር መንገዱ በአፍሪካ ውስጥ የላቁ አውሮፕላኖች ግንባር ቀደም ኦፕሬተር ሆኖ አቋሙን በማጠናከር በአየር መንገዱ እየተካሄደ ባለው የበረራ ማስፋፋት እና በማዘመን ላይ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ልዩ ኤ350-1000 አራት አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለማቅረብስ የተደረገው ስምምነት አካል ሲሆን የመጀመሪያው በህዳር 2024 መረከቡ አየር መንገዱ የዚህ ሞዴል የመጀመሪያው አፍሪካዊ ያደርገዋል።
ሁለተኛው እና ሦስተኛው ኤ350-1000ዎች በታህሳስ 2024 እና በጃንዋሪ 2025 የተረከበ ሲሆን አራተኛው በቅርቡ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ 46 በመቶ ያህሉ አሁንም የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተነገረ
#ethiopia | የውሃ እና ኢነርጂ ሚ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብታጠናቅቅም አሁንም ለንግግር እና ለድርድር በሯ ክፍት ነው።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ 46 በመቶ የሚሆነው የኤሌትሪክ የማያገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት እንደሚያግዝ አስታውቀዋል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት 54 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕቅድ ከአምስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2030 ቢያንስ 90 በመቶ የአገሪቱ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ትራምፕ በአገራት ላይ የጣሉት አብዛኛው ታሪፍ "ሕገ ወጥ" ነው ተባለ
#ethiopia | የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በበርካታ አገራት ላይ የተጣሏቸው አብዛኞቹ ታሪፎች ሕገ ወጥ ናቸው ሲል ብይን ሰጠ።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ውሳኔው ትራምፕ በአብዛኛው የዓለም አገራት ላይ "በአጸፋ" የጣሉት ታሪፍ ላይ እንዲሁም በቻይና ፣ በሜክሲኮ እና በካናዳ ላይ በጣሉት ታሪፎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።
የፌዴራል ጉዳዮችን የሚመለከተው የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰባት ለአራት በሆነ ድምጽ ባሳለፈው ውሳኔ፣ፕሬዚደንት ትራምፕ ታሪፉ የተጣለው 'አስቸኳይ የኢኮኖሚ ኃይል ሕግ' መሠረት ነው ሲሉ ያቀረቡትን መከራከሪያ ሃሳብ " ከሕግ ጋር የሚጻረር" ሲል ውድቅ አድርጎታል።
የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔውን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ጊዜ ለመስጠትም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እስከ አውሮፓውያኑ ጥቅምት 14 ድረስ ተግባራዊ እንደማይሆን ተገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017ዓ.ም ላይ የሰጠው ማብራረያ ⵑⵑ
#ethiopia | በዚህም መሰረት፡-
1. በገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 እንደተመለከተው ግብር ከፋዮች በየሶስት ወሩ ለሚከፍሉት ግብር መሰረት የሚሆነው ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉት ግብር ነው:: ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉት ግብር ማለት ደግሞ ባለፈው አመት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለውን እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የተከፈለውን ግብር እንዲሁም እነዚህ ሂሳቦች ተቀንሰው በአመቱ መጨረሻ አስታውቀው የከፈሉትን ግብር ይጨምራል፡፡ በመሆኑም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የክፈሉት ግብር በየሶስት ወሩ ለሚከፈለው 25% ግብር ስሌት መሰረት መሆን አለበት፡፡
ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የተከፈለው ግብር በየሦስት ወሩ 25% ለሚከፈለው ግብር ክፍያ ተቀናሽ የሚደረገው የወቅቱ የግብርዘመን ሲሆን በየካቲት ወር 2018 ለሚፈፅሙት የመጀመሪያው 25% ግብር ክፍያ ተቀናሽ የሚደረገው ቅድመ ግብር የሐምሌ 2017፣ የነሐሴ 2017 እና የመስከረም 2018 ዓ.ም (ከሂሳብ ጊዜያቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት) ነው፡፡ የሁለተኛ እና የሶስተኛ 25% ክፍያም ላይተቀናሽ የሚደረገው እንደቅደም ተከተላቸው የየሶስት ወራቱ ይሆናል፡፡
እ.ኤ.አ December 31 ሂሳባቸውን የሚዘጉ ግብር ከፋዮች የ2025 የመጀመሪያው 25% ግብር ክፍያ የሚፈፅሙት August 2025 ሲሆን ተቀናሽ የሚደረገው ቅድመ ግብርየJanuary, February እና March 2025 (ክሂሳብ ጊዜያቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት) ነው፡፡ የሁለተኛ እና የሶስተኛ 25% ክፍያም ላይ ተቀናሽ የሚደረገው እንደቅደም ተከተላቸው የየሶስት ወራቱ ይሆናል፡፡
በዚህ ተራ ቁጥር ከተሰጠው ማብራሪያ ጋር ተያይዞ ግብር ከፋዮች የሚያነሱት ተጨማሪ ጥያቄ ወይም ድጋፍ ካለ በታክስ አስተዳደር አዋጁ በተደነገገው አግባብ በመ/ቤታችሁ ምላሽ ይሰጣቸው፡፡
2. ሂሳባቸውን እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 2024 የሚዘጉ ግብር ከፋዮች ያቀረቡት የገቢ ማስታወቂያ
ኪሳራ ወይም ምንም አልሰራንም የሚል ከሆነ በየሶስት ወሩ የሚከፈለው ግብር የሚሰላው እ.ኤ.አ. ከ2024 በፊት ካሉት የግብር አመታት ውስጥ በመጨረሻ ግብር በተከፈለበት አመት የከፈሉትን ግብር መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግብር ከፋዮች ፀንተው ስራ ላይ ባሉ የታክስና ሌሎች ሕጎች ሰነዶችን ይዞ ስለማቆየት በተደነገጉት አንቀፆች ከተጠቀሱት አመታት በላይ ያለውን የግብር አመት አይጨምርም፡፡ ከዚህ ውጪ ባለፉት አመታት ምንም አይነት ግብር ያልከፈሉ ከሆነ በተያዘው የግብር አመት ሶስት ወራት ባከናወኑት የንግድ ስራ እንቅስቃሴ ላይ ሊከፍሉት የሚገባው ግብር ተሰልቶ ሊከፍሉ ይገባል፡፡
3. በገቢ ግብር አዋጁ በተፈቀደው መሰረት ያጋጠማቸው ኪሳራ በመሸጋገር ላይ ያለ ግብር ከፋዮች አማራጭ አነስተኛውን ግብር 2.5% ከፍለው ከዚያ በላይ ሊከፍሉት የሚገባ ግብር ካለ ኪሳራው ከ2.5% በላይ ከሆነው ግብር ጋር ይካካሳል፤ በዚህ አይነት ሊካካስ የሚችል ግብር ከሌለ ኪሳራው ወደሚቀጥለው የግብር አመት ይሸጋገራል፡፡
4. አማራጭ አነስተኛ ግብር (2.5%) የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ሊከፍሉት የሚገባው ግብር ሲሰላ በግብር አመቱ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው ግብር እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የከፈሉት ግብር ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
5. በገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ አንቀጽ 23 በተመለከተው መሰረት አማራጭ አነስተኛ ግብር ለ5 አመታት የሚሸጋገር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አማራጭ አነስተኛ ግብር ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ኪሳራ ወይም ምንም አልሰራንም የሚል ማስታወቂያ የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች አነስተኛውን ግብር የሚከፍሉ ስለሆነ፤ በሚቀጥለው የግብር አመት በየሶስት ወሩ ለሚከፍሉት ግብር መሰረት የሚሆነው የከፈሉት አማራጭ አነስተኛ ግብር ነው። #kgethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደ ጅምላ ብድር አቅርቦት ለመሸጋገር ማቀዱ ተገለጸ !!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሁን የሚከተለውን የችርቻሮ ብድር (ለግለሰቦችና ድርጅቶች ቀጥተኛ ብድር) አሰራር በመቀየር፣ ወደ ጅምላ ብድር አቅርቦት ለመሸጋገር ማቀዱ ተገለጸ።
ይህ አዲስ የቢዝነስ ሞዴል በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በዴሊዮት በተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት የተጠና ሲሆን፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት፣ ባንኩ ብድርን በቀጥታ ለግለሰቦች እና ለነጠላ ድርጅቶች ከማቅረብ ይልቅ፣ የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ብድሮችን ለንግድ ባንኮችና ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያቀርባል። እነዚህ ተቋማት ደግሞ በልማት ባንክ መስፈርት መሰረት በተመረጡ ዘርፎች ለሚንቀሳቀሱ አልሚዎች ብድሩን ያበድራሉ።
ሪፖርተር እንደዘገበዉ ይህ የቢዝነስ ሞዴል የልማት ባንክን የመንግስት ፖሊሲ ባንክነት ከማጠናከሩም በላይ፣ የመንግስት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት ዘርፎች ላይ ሀብት በማሰባሰብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና፣ ባንኩ በ2017 የሂሳብ ዓመት ከብድር መልስ 24 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱ ተዘግቧል።

የሎጎ ነገር
#ethiopia | በአሜሪካ ከ600 በላይ ሬስቶራንቶች ያሉት ክራከር ባሬል ሎጎ የመቀየር እቅዱን ሰረዘ።
ፕሬዝደንት ትራምፕን ጨምሮ የበርካታ ደንበኞች ወቀሳን ያተረፈው የክራከር ባሬል አዲስ ሎጎ በተዋወቀ በጥቂት ቀናት ከስራ ውጭ ሆኗል።
ኩባንያው ምሽት ላይ በኤክስ ገፁ አዲሱን ሎጎ በደንበኞች ፍላጎት እንደተወ አስታውቋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕም ውሳኔውን አሞግሰዋል።
ኩባንያው ለሪብራንዲንግ 700 ሚሊየን ዶላር መድቦ ሲሰራ ነበር።
ወደ 50 አመት የሚጠጋው የሬስቶራንቱ ሎጎ የእንጨት በርሜል የተደገፈ ሰውን ከፅሁፍ በተጨማሪ ያካተተ ነበር።
ሆኖም ስራ ላይ ሊውል የነበረው አዲስ ሎጎ የኩባንያውን ፅሁፍ ብቻ የያዘ ቀለል ያለ ምልክት ነበር።
የተለያዩ ዘገባዎች እንደጠቀሱት አተርፍ ተብሎ የተጀመረ የሎጎ ቅያሬ ያስከተለው ተቃውሞ ኩባንያው በገበያ ዋጋው እንዲቀንስ እንዲሁም የገንዘብ ኪሳራ ጭምር እንዲያስተናግድ እንዳደረገው ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ 2400 ሚሊየነሮች አላት
#ethiopia | በቀጣዩ በአፍሪካ የሚሊየነሮች ቁጥር በ65 በመቶ ይጨምራል።
በአህጉሪቷ 25 ቢሊየነሮች አሉ፣ የሚሊየነሮች ብዛት ግን 122 ሺ 500 ደርሷል።
ደቡብ አፍሪካ 41ሺ 100 ሚሊየነሮች ስትመራ ግብፅ 14ሺ 800፣ ሞሮኮ 7ሺ 500፣ ናይጄርያ 7ሺ 200 ኬንያ 6ሺ 800 በመያዝ ከአንድ እስከ 5 ያለውን ቦታ ይዘዋል።
በየጨማሪ 5ቱ አገራት ከአህጉሪቱ የሚሊየን ዶላር ባለሃብቶች 63% የሚሸፍኑ ሲሆን ቢሊየነሮቻቸው 88% ይይዛል።
ኢትዮጵያ በዶላር የሚሊየነር ብዛት ከአፍሪካ 10 ደረጃን ይዛለች ሲል ሄንሌ ኤንድ ፓርትነርስ የ2025 የአፍሪካ ባለፀጎች ሪፖርት ሲያወጣ ነው የጠቀሰው።

የትራምፕ እና የሊሳ ኩክ ስራ ልቀቂና አልለቅም ሙግት !!
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፌደራል ግምጃ ቤት ገዥ ሊሳ ኩል ከኃላፊነታቸው እንደሚያነሱ ተናገሩ።
ትራምፕ 'ቱሩዝ ሲሻል' በተባለው የግላቸው የማኅበራዊ የትስስር ገፅ ይፋ ባደረጉት እና ለሊሳ ኩክ በተፃፈ ደብዳቤ በአስቸኳይ ከብሔራዊ ባንኩ ቦርድ አባልነታቸው እንዲነሱ የደረሱበትን ውሳኔ ይገልፃል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ትራምፕ በቤት ግዢ የብድር ስምምነቶች ላይ የተሳሳተ መግለጫ ለማውጣታቸው አሳማኝ "በቂ ምክንያት" አለ ካሉ በኋላ፤ ገዥዋን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ጠቅሰዋል።
ለዚህ ምላሽ የሰጡት ኩክ ትራምፕ ከሥራቸው ለማባረር ምንም ሥልጣን የላቸውም፤ እኔም ሥራዬን አልለቅም ብለዋል።
"ሥራዬን በገዛ ፈቃዴ አልለቅም። ከ2022 ጀምሮ ሳደርገው እንደነበረው የአሜሪካን ምጣኔ-ሀብት ለማገዝ ኃላፊነቴን መወጣቴን እቀጥላለሁ" ብለዋል።
የፌደራል ግምጃ ቤት እ.አ.አ በ1951 ከአሜሪካ መንግሥት ነፃነቱን ያገኘ ገለልተኛ ተቋም ነው።

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ አዲስ መመሪያ አወጣ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ላይ ያለውን የባለሀብቶች እምነት ለማሳደግ እና የክትትል ስርዓቱን ለማጠናከር የሚያስችል አዲስ መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል።
መመሪያው በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይም እንደ ገንዘብ ገበያ፣ የጋራ ፈንዶች እና የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ፈንዶች ያሉ የፋይናንስ መሣሪያዎች ላይ ያለውን ግልጽነትና የቁጥጥር ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ነው።
የመመሪያው ዓላማ፡ መመሪያው የፈንድ አሰራሮችን ግልጽ የሆኑ ሕጎችን የሚያስቀምጥ ሲሆን፣ ባለሀብቶችን ለመጠበቅና የገበያውን ታማኝነት ለማጎልበት ዝርዝር የመረጃ ይፋ የማድረግ መስፈርቶችን ያካተተ ነው።
የባለስልጣኑ አላማ በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ የላቀ የተጠያቂነትና ግልጽነት ደረጃን በመጣል፣ ሰፊ የባለሀብቶች ቁጥር እንዲሳተፍ፣ የፋይናንስ ፈጠራዎችን እንዲያነቃቃ እና ጠንካራ የካፒታል ገበያ በመፍጠር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ መሆኑን ተጠቁሟል።

መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን 35 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዕቅዱ አጠፈ
#ethiopia | መንግሥት በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ መሠረት የኢትዮ ቴሌኮምን 35 በመቶ ድርሻ ለውጭ ኩባንያዎች ለመሸጥ ማቀዱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ግን ዕቅዱን ማጠፉ ታወቀ፡፡
ሪፖርተር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንዳስነበበው መንግሥት ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያሰበው ዕቅድ በቅርብ ዓመታት ተግባራዊ አይደረግም ፡፡
በቀጣይ የኩባንያውን ተጨማሪ ድርሻ ለመሸጥ ‹‹በመጀመሪያ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተሸጠው ድርሻ ምን ያህል ያዋጣል?›› የሚለው መታየት እንደሚኖርበት፣ በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ድርሻ ለውጭም ሆነ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የመሸጥ ዕቅድ እንደሌለና በቅርብ ጊዜ ውስጥም እንደማይኖር አስታውቀዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሊጀመር ነው
በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ለ4 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው እና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ-መቀሌ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ስራዎችን ዳግም ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ግምገማዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ባቀረበበት ወቅት እንዳስታወቀው፣ በግጭቱ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩትን የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ-መቀሌ የባቡር መስመሮችን እንደገና ለማስጀመር አስፈላጊ የሆኑ ግምገማዎችን አጠናቋል።
ግንባታው ሲካሄድ የነበረው የ392 ኪሎ ሜትር ይህ የባቡር መስመር ፕሮጀክት በግጭቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይታወቃል።እ.ኤ.አ. በ2015 በ1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት፣ አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንዳስረዳው፣ ኮርፖሬሽኑ ስራዎቹን ዳግም ለማስጀመር ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ አንፃር ከባድ የፋይናንስ ጫና ውስጥ ይገኛል። ይህ ጫና ከባቡር ኢንቨስትመንቶች ጋር በተያያዘ ካለው ከፍተኛ የውጭ ዕዳ እና የገንዘብ ችግር የመነጨ ነው።
ይህንን ተግዳሮት ለመቋቋም፣ ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አፈጻጸሙን በስፋት እየገመገመ ሲሆን፣ አማራጭ የገቢ ምንጮችን በመፈለግ እና የንብረቶቹን አጠቃቀም በማሻሻል ላይ ትኩረት ማድረጉ ተመላክቷል። በበጀት ዓመቱ ከሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎችና ከግንባታ ፕሮጀክቶች እስካሁን ድረስ 710 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።
[KGEthiopia]

የሀበሻ እጀ ሰፊነት ተመሰከረ
📌ኢትዮጵያዉን ችሮታ በማድረግ ከአለም ሀገራት 22ኛ ደረጃን ያዙ።
#ethiopia | በየአመቱ የአለም ሀገራትን የችሮታ ደረጃ የሚያወጣው የአለም ልግስና ሪፖርት በ2025 ኢትዮጵያን ከ101 ሀገራት 22ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል።
ሪፖርቱ ኢትዮጵያውያን የገቢያቸውን 1.51 ፐርሰንት ለበጎ አድራጎት ስራዎች፣ ለሀይማኖታዊ ምፅዋትና ለሌሎች ልገሳዎች ያውላሉ ብሏል።
ሪፖርቱ አፍሪካውያን ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነፃፀር የተሻሉ ለጋሾች እንደሆኑም አሷይቷል።
አውሮፓዉያን የገቢያቸውን 0.64 ፐርሰንት ሲለግሱ አፍሪካውያን ግን የገቢያቸውን 1.5 ፐርሰንት ወይም የአውሮፖውያንን እጥፍ ያህል ይለግሳሉ።
አፍሪካውያን በብዙ ኢኮኖሚያዊ ጫና ውስጥ ሆነዉ የተሻለ ልገሳ ማድረጋቸው ችሮታ ከሀብት በዘለለ ከጥብቅ ማህበረሰባዊ ግኑኝነትና ሀይማኖታዊ ምክንያቶች የሚመነጭ እንደሆነ አሷይቷል።

Comments