9 days ago
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 60 ሺህ አደገ
**********************
26ኛው ባንክ ኦፍ አሜሪካ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ የምዝገባ መርሐ ግብር "ሩጫዬ ቀለሜ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ከ"ባንክ ኦፍ አሜሪካ" ጋር በተደረገው አጋርነት፤ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የዘንድሮው ውድድር፣ ከ60 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በይፋዊ የማስጀመር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እንደገለፁት፣ ታላቁ ሩጫ ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለዓለም የሚያስተዋውቅና ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ትልቅ መድረክ በመሆኑ መላው ህዝብ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዮ ሙሐመድ በበኩላቸው፣ ታላቁ ሩጫ ባለፉት 26 ዓመታት ከውድድር አዘጋጅነት ወደ ጠንካራ ተቋምነት በመሸጋገር ዓለም አቀፍ ብራንድ መሆን መቻሉን ገልፀዋል።
አክለውም ውድድሩ ስፖርትን የዕለት ተዕለት ባህል ለማድረግና የሀገርን ገፅታ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካን የመሰለ ግዙፍ ተቋምን ከውድድሩ ጎን ማሰለፍ መቻሉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቁሞ፣ ዋና ዓላማው ታላቁ ሩጫን ከዓለም ቀዳሚ ከሆኑ ውድድሮች ጋር ማስጠራት እንደሆነ ገልጿል።
አትሌት ኃይሌ አክሎም ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ውድድሮች በሙሉ ሰዓታቸው የሚመዘገብ በመሆኑ ተሳታፊዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩሏ፣ ውድድሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ጠቁማ፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ውድድሩን በዓለም ደረጃ ቁጥር አንድ የማድረግ ህልም ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብላለች።
ጎን ለጎንም የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ዳግማዊት የገለጸችው።
በአዲስ የሺዋስ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ #greatethiopianrun #ቱሪዝም

5 months ago
የብርነሽ ደሴ ተከታታይ ድል
የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ በድምቀት ተጠናቀቀ
#ethiopia | ዛሬ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የሴቶች ታላቁ ሩጫ ላይ አትሌት ብርነሽ ደሴ ለተከታታይ ዓመት አሸናፊ ሆናለች።
ካለፈው ዓመት ክብሯን ያስጠበቀችው ብርነሽ ደሴ (ከፀደይ ባንክ) 15:22:91 በመግባት 1ኛ ስትሆን፣ ሮቤ ዲዳ 2ኛ እንዲሁም ሰናይት ጌታቸው 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
የከንቲባዋ መልዕክት፦ ውድድሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ ይችላሉም!" በሚል አነቃቂ ንግግር አአድርገዋል።
ለአሸናፊዋ አትሌት የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ካለፈው ዓመት በዕጥፍ አድጎ 100 ሺህ ብር ተበርክቶላታል።
ተሳትፎ፦ በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋርን ጨምሮ ታላላቅ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና አትሌቶች ተገኝተዋል።
ይህ የ23ኛው ዓመት የሴቶች ታላቁ ሩጫ፣ ሴቶች ያላቸውን በራስ መተማመንና ብቃት ለዓለም ያሳዩበት ደማቅ የድል ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።
#getu #ethiopia #womenrun #greatethiopianrun #safaricom #addisababa #athletics #adanechabiebie #birneshdesse #meseretdefar #ቅድሚያለሴቶች #የሴቶችሩጫ #ታላቁሩጫ #አሸናፊዎች #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ሩጫ ለጤና
የክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጉብኝት
#ethiopia | ነገ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ አስመልክቶ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጎብኝተዋል።
ዓላማ፦ "AKTIVE AGAINST CANCER" የተሰኘው ንቅናቄ በሩጫ ውድድሩ አማካኝነት ሴቶች የካንሰር ህመምን ቀድሞ ለመከላከልና ጤናቸውን ለመጠበቅ እንዲተጉ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ዶክተር ኤርጎጌ እንዲህ ያሉ ትብብሮች ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው ገልጸው፣ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ሴቶችን የሚያበረታታ መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ካንሰርን ለመከላከልና ለማገገም ያለውን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅ ከአክቲቭ አጌንስት ካንሰር ጋር ለአራት ዓመታት የሚቆይ ስምምነት መፈራረሙ ተገልጿል።
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለካንሰር ማዕከሉ ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል።
ለ23ኛ ጊዜ የሚከናወነው የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ፣ ነገ መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
ሩጫው ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ ለጤናና ለግንዛቤ ያለውን ፋይዳ ለመጋራት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#getu #ethiopia #womenempowerment #cancerawareness #safaricom #greatethiopianrun #health #addisababa #ቅድሚያለሴቶች #ካንሰርንእንከላከል #ታላቁሩጫ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
Comments