የብርነሽ ደሴ ተከታታይ ድል
የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ በድምቀት ተጠናቀቀ
#ethiopia | ዛሬ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የሴቶች ታላቁ ሩጫ ላይ አትሌት ብርነሽ ደሴ ለተከታታይ ዓመት አሸናፊ ሆናለች።
ካለፈው ዓመት ክብሯን ያስጠበቀችው ብርነሽ ደሴ (ከፀደይ ባንክ) 15:22:91 በመግባት 1ኛ ስትሆን፣ ሮቤ ዲዳ 2ኛ እንዲሁም ሰናይት ጌታቸው 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
የከንቲባዋ መልዕክት፦ ውድድሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ ይችላሉም!" በሚል አነቃቂ ንግግር አአድርገዋል።
ለአሸናፊዋ አትሌት የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ካለፈው ዓመት በዕጥፍ አድጎ 100 ሺህ ብር ተበርክቶላታል።
ተሳትፎ፦ በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋርን ጨምሮ ታላላቅ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና አትሌቶች ተገኝተዋል።
ይህ የ23ኛው ዓመት የሴቶች ታላቁ ሩጫ፣ ሴቶች ያላቸውን በራስ መተማመንና ብቃት ለዓለም ያሳዩበት ደማቅ የድል ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።
#getu #ethiopia #womenrun #greatethiopianrun #safaricom #addisababa #athletics #adanechabiebie #birneshdesse #meseretdefar #ቅድሚያለሴቶች #የሴቶችሩጫ #ታላቁሩጫ #አሸናፊዎች #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago