22 hours ago
የዓለም ሻምፒዮኑ ጀግናው ክብሮም ንጉሴKebrom muaythia and kickboxing champion . ደማቅ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊደረግለት ነው!
የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ ላደረጉ፣ የኢትዮጵያን ስም በኩራት ላስጠሩ ጀግኖች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የሁላችንም ታሪካዊ ድርሻ ነው!
ኢትዮጵያውስጥ Ethio Fight Night አሸናፊ እንዲሁም
በታኅሣሥ ወር 2023 ዓ.ም (December 2023) በጣሊያን ሀገር በታዋቂው Fight Clubbing አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የሞይታይ ሻምፒዮና (Muay Thai World Championship) ላይ በ67 ኪሎ ግራም ክብደት ሙሉ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር፣ የዓለም ሻምፒዮን (World Champion) በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘውና የሀገር ኩራት የሆነው የሳሪስ አዲሱ ሰፈር ልጅ ክብሮም ንጉሴ (The King) ታላቅ የክብር እና የምስጋና መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።
ክብሮም ንጉሴ በዓለም አቀፍ የማርሻል አርት መድረኮች (እንደ Bellator እና WPG Combat ያሉ) የብራዚልና የሌሎች ሀገራት ጠንካራ ተፎካካሪዎችን በበላይነት በመርታት የሚታወቅ፣ የሁለት ጊዜ የጣሊያን K1 ሻምፒዮን እና የኢንተርኮንቲኔንታል ሻምፒዮን በመሆን በፅናትና በደምና በላቡ የተጓዘ እውነተኛ የኢትዮጵያ አልማዝ ነው።
ይህንን ታላቅ ድል እና የሀገር ባለውለታ በደማቅ ሁኔታ ለመዘከር፣ መላው የሳሪስ ወጣቶች ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ደማቅ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር (Appreciation & Recognition Ceremony) አዘጋጅተዋል።
ይህ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ከ 500 በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ የኢትዮፋይት (EthioFight)night )&etfc አዘጋጆች ፡ተወዳዳሪዎች እና አዘጋጆች፣ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የሳሪስ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የክብር እንግዶችና አጋር ድርጅቶች በነቂስ የሚገኙበት ይሆናል።
የሰፈራችንን፣ የከተማችንንና የሀገራችንን ጀግና በጋራ ሆነን እንቀበለው፤ እናበረታታው! ሁላችሁም ሚዲያዎችና ስፖርት አፍቃሪዎች በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

7 days ago
የደቡብ አትላንቲክ የዓሣ ነባሪ መጠለያ ሀሳብ ዳግም ውድቅ ሆነ
ዓሣ ነባሪዎችን ከአደንና ከተለያዩ የባሕር አደጋዎች ለመጠበቅ የቀረበው የደቡብ አትላንቲክ የጥበቃ ቀጣና ሀሳብ ዳግም ሳይፀድቅ ቀርቷል። ሀሳቡ በአርጀንቲና፣ ብራዚልና ኡራጓይ የቀረበ ሲሆን፣ በአውስትራሊያ ሆባርት ከተማ በተካሄደው 70ኛው የዓለም አቀፉ የዓሣ ነባሪ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ተወያይቶበታል።
ሀሳቡ ቢፀድቅ በደቡብ አትላንቲክ ሰፊ የባሕር አካባቢ ከንግድ ዓሣ ነባሪ አደን የተጠበቀ ቀጣና ይፈጠር ነበር። የመጠለያው ዓላማም ዓሣ ነባሪዎችን ከአደን በተጨማሪ በባሕር ላይ ለሚያጋጥሟቸው ሌሎች ስጋቶች ጥበቃ ማጠናከር ነው። ዓሣ ነባሪዎች በባሕር ሥነ-ምህዳር ውስጥ ጠቃሚ ሚና ስላላቸው፣ የሚኖሩበትንና የሚፈልሱበትን አካባቢ መጠበቅ የባሕር ሥነ-ምህዳሩን ጤና ለመጠበቅ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ዓሣ ነባሪዎች በረጅም ርቀት ስለሚፈልሱ ከትላልቅ መርከቦች ጋር መጋጨት ለእነሱ ከሚያጋጥሙ አደጋዎች አንዱ ነው። ሰፊና በተገቢው የሚተዳደር የባሕር ጥበቃ ቀጣና መፍጠር እንደ መርከብ ግጭት ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ሊያግዝ ይችላል።
ይሁንና ሀሳቡ ለመፅደቅ ከሚያስፈልገው የሦስት አራተኛ ድምፅ ድጋፍ በታች በማግኘቱ ሳይፀድቅ ቀርቷል። የጀርመን የዜና ወኪል epd እንደዘገበው፣ ይህ ለደቡብ አትላንቲክ የዓሣ ነባሪ መጠለያ ለመመስረት የቀረበው ሀሳብ ዳግም ለወደፊት ውይይት እንዲተላለፍ አድርጓል። የጀርመን መንግሥት በበኩሉ ለሀሳቡ ድጋፍ መስጠቱን ገልጿል።
ቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል

9 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የብራዚል አሰልጣኝ ለሰጡት አስተያየት የህንዱ አምበል መልስ ሰጠ፡፡ የፊታችን ቅዳሜ ብራዚልና ህንድ ታሪካዊ የሚባለውን የወዳጅነት ግጥሚያ ያደርጋሉ፡፡ በኮልካታ ለሚደረገው ለዚህ ግጥሚያ ህንድ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች፡፡ የብራዘል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተወካዮች ወደዚያው አቅንተው በከተማው የሚገኘውን ሳልት ሌክ ስታዲየም ከጎበኙ በኋላ በሜዳው ደስተኛ አለመሆናቸውን ገልፀው ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎም የህንድ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ሜዳውን አስተካክሎታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዳሜውን ግጥሚያ በተመለከተ የብራዚሉ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ስለህንድ እግር ኳስ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ይህ የባህል ችግር እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ህንድ በሌሎች ስፖርቶች ጥሩ አቋም ያላት ቢሆንም የእግር ኳስ ባህል ግን የላትም፡፡ አዳስ የተጨዋቾች ትውልድ ለመፍጠር መስራት ይገባቸዋል›› ብለዋል፡፡ ለዚህ አስተያየት ምን መልስ እንዳለው የህንድ አምበል የሆነው ጉርፔት ሲንግ ሳንዱ ተጠይቋል፡፡ ከገልፍ ኒውስ ለቀረበለት ለዚህ ጥያቄ ሲመልስም ‹‹እንደአንቸሎቲ ያለ ሰው ስለእግር ኳስ ምክር ሲሰጥ ሁሉም ሰው ማዳመጥ እንዳለበት አምናለሁ፡፡ በእግር ኳስ በማደግ ላይ ያለን አገር በመሆናችን የሰጡን አስተያየት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡›› ብሏል፡፡ እንደገለፀውም ነገሮች የሚጀምሩት መሰረታዊ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ነው፡፡
በሚቀጥሉት አመታት አሰራሮችን በማስተካከልና ከትልልቅ ቡድኖች ጋር በመጫወት ባህሉን ለማሳደግ እንደሚጥርም አስታውቋል፡፡ ቅዳሜ አምስት ጊዜ የአለም ሻምፒዮን ከሆነችው ብራዚል ጋር የሚያደርጉት ግጥሚያም የዚሁ አካል መሆኑን አስረድቷል፡፡ ህንድ በአለም የእግር ኳስ ደረጃ በ138ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ቢሆንም በቅርቡ ግን መሻሻሎችን እያሳየች ነው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ግጥሚያዋን ያደረገችው በአለም 44ተኛ ደረጃ ካላት ፓናማ ጋር ሲሆን በጨዋታውም አንድ ለአንድ ተለያይታለች፡፡ የህንድ አምበሉ በመጨረሻም ‹‹አንቸሎቲ ከዚህ ከብራዚል ግጥሚያ በኋላ ተጨማሪ ምክሮች እንደሚሰጡን ተስፋ አደርጋለሁ›› ብሏል፡፡

14 days ago
ፈርጣማዉ ዳኛ ለፍጥነታቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዋል
በብራዚል ሊግ ዳኛ የሆኑት አንደርሰን ዳሮንኮ ከብራዚል ሊግ የዳኞች ኮሚቴ በቀረበላቸው ምክረ ሃሳብ ከሰዉነት ክብደታቸዉ ወደ 12 ኪሎግራም መቀነሳቸዉ ተዘግቧል።
የአለማችን ፈርጣማዉ ዳኛ በመባል የሚታወቁት እኚህ የ 45 አመት አርቢትር ለፍጥነት እና ቅልጥፍና በሚል ነዉ ኪሎአቸዉን እንዲቀንሱ የታዘዙት።
ዳኛዉም ለህልማቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዉ ጨዋታ መርተዋል። በርከት ያሉ የእግርኳስ ተመልካቾች በዳኛዉ የሰዉነት ቅርጽ መለወጥ ጥያቄ ፈጥሮባቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ አድረወገዉት ነበር።

Sponsored by
Surafel
15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ጨዋታ የለም› ሲሉ የብራዚሉ አሰልጣኝ አንቸሎቲ ተናገሩ፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም የፊታችን ኦክቶበር 3 በህንድ ኮልካታ ከተማ ብራዚልና ህንድ የወዳጅነት ግጥሚያቸውን ያደርጋሉ፡፡ የአምስት ጊዜ የአለም ሻምፒዮኖቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለዚህ ግጥሚያ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጡት ገልፀው ‹‹ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ጨዋታ የለም›› ብለዋል፡፡
እንደቪኒሺየስ ጁኒየርን የመሳሰሉ ኮከብ ተጨዋቾችን ያካተተችው ብራዚል በአለም የእግር ኳስ ሰንጠረዥ በ5 ደረጃ ላይ የምትገኝ ናት፡፡ በአብዛኛው የክሪኬትስ ወዳጅ የሆነችው ህንድ ደግሞ ለእግር ኳስ ያን ያህል ብትሆንም በርካታ ህዝቧ ለአለም አቀፍ ተጨዋቾች አድናቆት አለው፡፡ ህንድ እንዲህ አይነት አለም አቀፍ የወዳጅነት እግር ኳስ ውድድር ስታስተናግድም የመጀመሪያዋ በመሆኑ ጉዳዩ ትልቅ ትኩረትን ስቧል፡፡ አንቸሎቲ በንግግራቸው ‹‹ብራዚል በአለም ዙሪያ ሁሉ ደጋፊዎች አሏት፡፡ በህንድ መጫወት ለእኛ ትልቅ ደስታ ነው፡፡ የምንጫወተው ደግሞ በብራዚል ለሚገኙ ብቻም ሳይሆን በህንድ ላሉም ደጋፊዎቻችን ጭምር ነው›› ብለዋል፡፡
ጨዋታው ምንም እንኳ የወዳጅነት ቢሆንም አንጋፋው ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ግን በሙሉ አቅማቸው እንደሚጋጠሙ ገልፀዋል፡፡ የ67 አመቱ አሰልጣኝ ጨምረውም ‹‹ይህ የወዳጅነት ጨዋታ ቢሆንም ዝግጅት የምናደርግበትም ነው፡፡ ስለዚህም ለእኛ የወዳጅነት የሚባል ቀለል አድርገን የምንመለከተው ጨዋታ የለም›› ማለታቸውን ዘታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል፡፡ ህንድ በፊፋ የእግር ኳስ ሰንጠረዥ በ138ተኛ ደረጃ ብትቀመጥም በአለም ዋንጫ ተሳትፋ ግን አታውቅም፡፡

18 days ago
እግር ኳስን ለማቆም ጫፍ ደርሶ የነበረው ኮከብ - ራፊንሃ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢቢሲ ስፖርት አምደኛው ጊሌም ባላጌ፥ ብራዚላዊው ኮከብ "የእግር ኳስ ህልሜ አክትሞለታል" የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን አጋጣሚ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይተርካል።
በብራዚሏ ፖርቶ አሌግሪ ከተማ የተወለደው ራፋኤል ዲያዝ ቤሎሊ (ራፊንሃ) እግር ኳስን የጀመረው እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳስ ባለው ፍቅር ብቻ አልነበረም።
ስኬታማ እግር ኳስ ተጫዋች መሆን፥ በከፋ ድህነት፣ በወንጀልና በአደንዛዥ ዕጽ ከሚታወቀው የትውልድ መንደሩ ማምለጫው ብቸኛ መንገድ መሆኑን ስለተረዳም ጭምር ነው።
የህልሙን መንገድ ተከትሎ ገና በልጅነቱ እግር ኳስን ቢጀምርም፤ የ18 ዓመት ወጣት እያለ ያጋጠመው የህይወት አጣብቂኝ ለዛሬ ስኬቱ መስፈንጠሪያ ሆኖታል።
የስፖርት አምደኛው እንደሚለው፥ በዚያ ወቅት ራፊንሃ ከሚጫወትበት የአቫይ ወጣት ቡድን ውጪ ሆኗል፤ ጉዳት አስተናግዷል፤ ፈላጊ ክለብ አጥቶ የእድል በሮች ሁሉ ተከርችመውበት ነበር።
እነዚህ ሁኔታዎች እግር ኳስ የማቆም አፋፍ ላይ አድርሰውት በነበረበት ወቅት፥ እናቱ የሰጡት ምክር ያበቃለት ለመሰለው ህልሙ ነፍስ ዘርቶለታል።
"የእግር ኳስ ጉዞህን ለማቆም ከወሰንክ፤ ቀሪውን እድሜህን አሁን ባለህበት ሁኔታ ለመኖር እንደወሰንክ እወቀው" ነበር ያሉት።
ጊሌም ባላግ በዚህ አምዱ፥ ከዚያች ቅጽበት በኋላ ራፊንሃ እስከ ባርሴሎና መልበሻ ቤት ያደረገው ጉዞ የጽናት፣ የዲሲፕሊን እና ራስን የማብቃት ታሪክ ነው ሲል ይገልጻል።
በእግር ኳስ ሕይወቱ ያሳየው ከፍታ የተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን፤ የዓላማ ጽናት፣ የመስዋዕትነትና ለህልም የመኖር መሻት ውጤት መሆኑን ያነሳል።
ራፊንሃ እንደ አብዛኞቹ ብራዚላውያን ከዋክብት ብቃቱን በሀገሩ ብራዚል ሊጎች ለማሳየት አልታደለም፤ በዚህም ምክንያት ከአውሮፓ ዝቅተኛ ሊጎች መጀመር ግድ ብሎታል።
በፈረንጆቹ 2016 የፖርቹጋሉን ክለብ ቪቶሪያ ጊማሬሽ የወጣት ቡድን ከተቀላቀለ በኋላ ወደ ዋናው ቡድን ያደገ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ ሌላኛው የፖርቹጋል ክለብ ስፖርቲንግ አመራ።
በቀጣዩ ዓመት ወደ ፈረንሳዩ ሬን በማምራት ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማቅናት ሊድስ ዩናይትድን መቀላቀል ችሏል።
የሊድስ ቆይታው በማርሴሎ ቤልሳ ስር ከኳስ ክህሎቱ ባሻገር ተክለሰውነቱን ያጠነከረበትና ቴክኒካዊ ብቃቱን ያጎለበተበት ነበር።
በሁለት ዓመት የኢላንድ ሮድ ቆይታው በፕሪሚየር ሊጉ በ29 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ባሳየው አስደናቂ ብቃት በ50 ሚሊየን ፓውንድ መነሻ የዝውውር ሂሳብ ባርሴሎናን መቀላቀሉ አይዘነጋም።
በብሉ ግራናዎቹ ቤት በወቅቱ የክለቡ አሰልጣኝ በነበረው ዣቪ ስር፥ ራፊንሃ እንደ ስብስቡ አማራጭ የሚቆጠር እንጂ በቋሚነት የሚሰለፍ ተጫዋች አልነበረም።
በቋሚነት በሚጀምርባቸው ጨዋታዎችም በጊዜ ተቀይሮ የሚወጣ የነበረው ተጫዋቹ፤ በባርሴሎና ቤት በፍጥነት ለመድመቅ ተቸግሮ ነበር።
በፈረንጆቹ 2024 የካታላኑ ክለብ ከቀድሞ ተጫዋቹ ጋር ተለያይቶ ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ሲሾም ለራፊንሃ ሁኔታዎች ተቀየሩ።
በሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎና ተከላካዮችን ለማለፍ የማይቸገር፣ በግብ ፊት ምህረት የለሽ ቁልፍ ተጫዋች መሆን ችሏል፤ በአሰልጣኙ የተሰጠው ሚና በራስ መተማመኑን ከፍ እንዳደረገለት ይነገራል።
በዚህ የውድድር ዓመት ብቻ በላሊጋው ለተከታታይ ሁለት ጊዜ ሀትሪክ መስራት የቻለው ብራዚላዊ የመስመር አጥቂ፥ በ12 ግቦች የላ ሊጋውን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ይገኛል።
በሀንሲ ፍሊክ ስር ለክለቡ ባደረጋቸው 98 ጨዋታዎች 69 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል፤ 32 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ከባርሴሎና ጋር ሦስት ጊዜ የላ ሊጋ ሻምፒዮን ሆኗል፤በ2024/25 የውድድር ዓመት የውድድሩ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ገና በ18 ዓመቱ እግር ኳስን ለማቆም ተቃርቦ የነበረው የባርሴሎና አምበል፤ በ2025ቱ የባሎንዶር ሽልማት ምርጥ 5 ውስጥ መካተት ችሎም ነበር።
በኃይለማሪያም ተገኝ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አዲስ ምዕራፍ፤ ደጅ የሚጠና ሳይሆን ደጅ የሚጠናለት
*******************
የብሪክስ አባል ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ የሀብት፣ የቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከል መዳረሻ ናቸው።
የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ አካሄድም ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የዚህ ጥምረት አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል።
ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁት፣ ሀገራችን የጥምረቱ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ጫናዎችን ተገዳድራ ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችላትን አቅም እንድትገነባ አስችሏታል።
የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ጌትነት ትርፌ (ዶ/ር)፤ የብሪክስ አባል መሆን በዓለም የበላይነት የሚደረጉ የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ጫናዎችን መቋቋም የሚያስችል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ የውሳኔ ሰጪነት ሚና፣ የትሩፋቱ ተሳታፊነት፣ ድርሻና መብት እንደሚኖራትም ጠቁመዋል።
አባልነቱ ቀድሞ የነበሩ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በይበልጥ እንዲጠናከሩ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የጠቆሙት ዶክተር ጌትነት፤ "ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ደጅ የሚጠና ሳይሆን ደጅ የሚጠናለት ነው" ብለዋል።
የብሪክስ ብሔራዊ ጥቅም በተጠናከረ ቁጥር የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲም አብሮ እየተጠናከረ እንደሚሄድም አብራርተዋል።
የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተመራማሪው አሊ ሁሴን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኗ ለራሷ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲሰማ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሚኖረው የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያፋጥነው ተመራማሪው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከህንድ እስከ ቻይና፣ ከሞስኮ እስከ አቡዳቢ፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ብራዚል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በማጠናከር አዳዲስ ገበያዎችንና የፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ ያስችላታል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ ጥምረት መቀላቀሏ ከደህንነት ስጋት ወጥታ ወደ ብልፅግና ጎዳና የመሸጋገሯ ታላቅ ማረጋገጫ መሆኑን ያነሱት ተመራማሪው፣ ለአፍሪካ አህጉርም የድልድይነት ሚናዋን እንድትጫወት የሚያስችላት አዲስ ምዕራፍ መሆኑን አመልክተዋል።
በሀይማኖት ከበደ

20 days ago
ኢትዮጵያ በብሪክስ አባል ሀገራት ስለምን ተፈላጊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጀመረቻቸው የዲፕሎማሲ ስኬቶች መካከል የብሪክስ አባል መሆኗ ታላቅና ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን (በመቀጠልም ኢትዮጵያን፣ ግብጽን፣ ኢራንን እና ዩናይትድ አረብ ኤሚሬቶችን) ያቀፈው ይህ ስብስብ፤ የዓለምን የጂኦ-ፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መልክዓ ምድር ዳግም እየቀረጸ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሀገሪቱ ከአህጉራዊ ተሰሚነቷ ባለፈ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ትንተና ዳይሬክቶሬት ባልደረባ የሆኑት ወንድሙ መኮንን፤ ‹‹Ethiopia and BRICS: Prospects and Challenges›› በሚል ርእስ በ‹‹Journal of Political Science and International Relations›› ዓለም አቀፍ የጥናት መድብል ላይ ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፋቸው፤
‹‹የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ቦታ፣ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ያላት የመሪነት ሚና እና እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ለብሪክስ ሀገራት ሳቢ አጋር አድርጓታል። ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ብሪክስ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰፊ መገኘት እንዲኖረው ከሚያደርገው ስትራቴጂ አካል አንዱ ነው፤ ይህም ኢትዮጵያ የምትገኝበት ይህ ቀጣና ለመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቅርበት፣ ለቀይ ባህር መገኛ አካባቢ መሆኑና በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታን በማስጠበቅ ረገድ ካለው ከፍተኛ የሆነ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው›› ሲሉ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ለመሆን ስትወስንም ከራሷ ብሔራዊ ጥቅም ባሻገር አባላቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ስትራቲጂካዊ ጠቀሜታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
የብሪክስ አባል ሀገራት አጠቃላይ የኢኮኖሚ ምርት ከ28 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያለው በመሆኑ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው። በጋራ ከዓለም ህዝብ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑትን የሚይዙ ሲሆን፣ ለዓለም አቀፉ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ትልቅ ድርሻ ያበረክታሉ።
በተጨማሪም አራት ተጨማሪ አባል ሀገራት ማለትም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በመጨመራቸው የብሪክስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አቅም የበለጠ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ የዚህ ስብስብ አካል መሆን ለኢትዮጵያ በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛል።
የሩሲያው ሎባቼቭስኪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆነው ተመስገን ወ/ጻድቅ፤ ‹‹Ethiopia's Membership in BRICS: Opportunities and Challenges›› በሚል ርዕስ ባለፈው ግንቦት ወር ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፍ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ያለውን ፋይዳ በስፋት ዳስሰዋል።
ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ ሀገር በመሆኗ፣ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና እና መግቢያ በር፣ ትላልቅ የልማት እቅድ በመተግበር ላይ የምትገኝ ሀገር በመሆኗ እና የቀጣናው መሪ መሆኗን በመቀጠሏ የብሪክስ አባል መሆኗ በአባል ሀገራቱ መካከል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ያላት ቁርኝት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በ”ውቀት ልውውጥ ያሉ አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ባላት ፍላጎት የሚመራ ነው።
የብሪክስ ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተፅዕኖ ማሳደጋቸውን በቀጠሉበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ አዳዲስ ገበያዎችን ለማግኘት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎቿ ላይ ፈጠራን ለማስፋፋት በዚህ ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ቦታዋን ለመያዝ ትፈልጋለች።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር መጣመር፤ በቀጣናዊ ውህደት፣ በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እና በዓለም አቀፍ ትብብር ላይ የሚያስከተለውን የተወሰነ አንድምታ የመረዳት አስፈላጊነት በመኖሩ ነው።
በኢትዮጵያ እና በብሪክስ መካከል ያለው ግንኙነት በተለይም በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም እንዳለው ያመላክታሉ።
የብሪክስ ሀገራት ባላቸው ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም እና በትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ባላቸው ልምድ፣ የኢትዮጵያን ታላላቅ የልማት ግቦች በመደገፍ ረገድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
በአፍሪካን ስተዲስ ሪቪው የታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ እንደተመላከተው፤ ቻይና እንደ ኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመሳሰሉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና የመሠረተ ልማት ዘርፎች ላይ ግንባር ቀደም ኢንቨስተር ሆና ወጥታለች።
በተመሳሳይ ህንድ የሀገሪቱን እያደገ የመጣ የሠራተኛ ኃይል እና የገበያ አቅም በመጠቀም በኢትዮጵያ የእርሻ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ናት።
ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ባለፈ በሌሎች ዘርፎችም ለምሳሌ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በክህሎት ማሳደግ እና በጋራ የምርምርና ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በኢኮኖሚ ዘርፍ ያለው ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እያደገ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ የማምረት አቅሟን ለማሳደግ እና በዋና ዋና ዘርፎች የእሴት ሰንሰለቱን ከፍ ለማድረግ ያለው ጠቀሜታ ጉልህ ነው።
በተረፈ ወርቁ

23 days ago
የመደመር እሳቤ ያበበበት ታሪካዊ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ በብሪክስ ፕላስ እና አዲሱ የጂኦፖለቲካ አሻራ
*************************
ኢትዮጵያ በ1923 ዓ.ም የመንግሥታት ማህበር (League of Nations) አባል ለመሆን ያደረገችው እልህ አስጨራሽ ጥረት፣ በመቀጠልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራችና አንጋፋ ሀገር በመሆን ያስመዘገበችው ደማቅ ታሪክ የዲፕሎማሲዋ መሰረት ነው።
ዛሬ በዚህ ምዕተ ዓመት ደግሞ ታሪካዊ ቀጣይነቱን ያረጋገጠ ሌላ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ አሻራን ማሳረፍ ተችሏል።
ከታኅሣሥ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ የብሪክስ ፕላስ ሙሉ አባል በመሆን የዓለም አቀፉ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዋና ተዋናይነቷን አረጋግጣለች።
ይህ ታላቅ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፉክክር እና ትብብርን በሚያስታርቀው የመደመር እሳቤ የተገበረው የላቀ የመሪነት ዲፕሎማሲ ፍሬ ነው።
አካሄዱ ወዳጅ እና ጠላት ከሚል ጠባብ ፍረጃ የተላቀቀ፣ አጋርነትን ማብዛት ላይ ያተኮረ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት በጽኑ መሰረት ላይ ያቆመ ነው።
ከ40 በላይ ሀገራት አባል ለመሆን ወረፋ በያዙበት በዚህ መድረክ ኢትዮጵያ ቀዳሚ መሆኗ የዲፕሎማሲ ክብደቷን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የብሪክስ መሪዎች የኢትዮጵያን ታላቅ ህልምና ስትራቴጂካዊ ቦታ ተረድተው አባል እንድትሆን የመረጡበት ቁልፍ ምክንያቶች በርካታ ናቸው።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ለቀይ ባህር እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ቅርብ በመሆኗ የብሪክስ ሀገራት በቀጣናው ያላቸውን ተፅእኖ ለማስፋት ምቹ መድረክ ትሆናቸዋለች።
በተጨማሪም ሰፊ የገበያ እድል እና የሰው ኃይል ባለቤት መሆኗ፣ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ፣ ከነባሮቹ አባላት (ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ) ጋር ያላት ጠንካራ የሁለትዮሽ አጋርነት እና የባለብዙ ዋልታ (Multipolar) ዓለም ራዕይ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው።
ገለልተኛ የውጭ ፖሊሲ የምትከተለው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፋይናንስና ፖለቲካ ተቋማት ፍትሃዊ መሆን አለባቸው ብላ የምታምነው ጽኑ አቋም ከብሪክስ መሠረታዊ ራዕይ ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣጣማል።
ይህ አባልነት የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ፍላጎታችንን ያማከለ ከመሆኑም በላይ በቀጣናችን ተፎካካሪዎቻችን ሊፈጥሩ የሚችሉትን የወደፊት መሰናክል አስቀድሞ በብልሃት ያመከነ ዲፕሎማሲያዊ ብስለት ነው።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አስራ አንዱ የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለማችንን 49 በመቶ የህዝብ ቁጥር፣ 36 በመቶ የቆዳ ስፋት፣ 40 በመቶ የዓለም አቀፍ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እና 23 በመቶ የሚሆነውን የዓለም አቀፍ ንግድ ይወክላሉ።
ከምዕራባውያኑ የቡድን ሰባት (G7) ስብስብ ጋር ሲነጻጸር የብሪክስ ፕላስ የበላይነት እጅግ አስገራሚ ነው። የብሪክስ ፕላስ ኢኮኖሚ 88 ትሪሊየን ዶላር ወይም የዓለማችንን 45 በመቶ ሲሸፍን፣ የጂ-7 ሀገራት ግን 62 ትሪሊየን ዶላር ወይም 31 በመቶ ላይ ይገኛል።
ከህዝብ ብዛት አንጻር ብሪክስ ፕላስ ከ3.3 ቢሊየን በላይ ህዝብ (ከዓለም አጠቃላይ ህዝብ ግማሹን) ሲያቅፍ፣ ጂ-7 ግን 800 ሚሊየን ህዝብ ብቻ አለው። ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ እና ዋና ዋና የንግድ ማዕከላትም በዚሁ ስብስብ እጅ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ 37 በመቶ የውጪ ንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወነው ከብሪክስ ሀገራት ከነበሩትና አዳዲስ አባላት ከሆኑት እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኢንዶኔዥያ ጋር ነው።
አባልነቱ ብሪክስ ፔይ (BRICS Pay) በተባለው አዲስ የክፍያ ስርአት እና በሀገር ውስጥ ገንዘብ የመገበያየት እድልን በመክፈት የውጪ ምንዛሬ እጥረታችንን ለመቅረፍ ትልቅ በር ይከፍታል።
በተጨማሪም 100 ቢሊየን ዶላር ካፒታል ያለው አዲሱ የልማት ባንክ (New Development Bank) ከምዕራባውያን የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታ ነጻ የሆነ አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ አባልነት ጋር ሲቀናጅ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚያመጣ የታመነበት ተስፋ ነው።
"ለጽናት፣ ለፈጠራ፣ ለትብብር እና ለዘላቂነት" በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ላይ ሀገራችን በዓለም አቀፍ የንግድና የአየር ንብረት ድርድር ላይ ድምጿን ከፍ አድርጋ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቷን አረጋግጣበታለች።
የብሪክስ ፕላስ ማዕበል የዓለማችንን የጂኦፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ትርክት እየቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የታሪካዊ ሽግግሩ ተመልካች ሳይሆን ዋና ተዋናይ መሆን ችላለች።
መንግሥት በመደመር እሳቤ አጋር በማብዛት እና ብሄራዊ ጥቅምን በማስቀደም ያረጋገጠው ይህ የዲፕሎማሲ ስኬት መላው ኢትዮጵያዊ የሚኮራበት እና የሚደግፈው የጋራ ድል ነው።
በሜሮን ንብረት
#ethiopia #ebc #bricsplus #medemer #ethiopiandiplomacy #geopolitics

24 days ago
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ በኒው ዴልሂ
******************
በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ መስራችነት የተጀመረው የብሪክስ (BRICS) ጥምረት፣ በቅርቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ አባል ሀገራትን በመቀላቀሉ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ መጥቷል።
በአሁኑ ወቅት የብሪክስ አባል ሀገራት ከዓለም ህዝብ ቁጥር ከ40 በመቶ በላይ እንዲሁም ከዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ከሩብ በላይ የሚይዙ ግዙፍ የኃይል ሚዛን መሆናቸው ይታወቃል።
የዘርፉ ተንታኞች እንደሚያመለክቱት፣ ጥምረቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጠነከረ የመጣበት ዋና ምክንያት ፍትሃዊ ያልሆነውን የቆየ የፋይናንስ ሥርዓት በመገዳደር አዲስ አማራጭ ይዞ በመውጣቱ ነው። በተለይም የብሪክስ ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ ለታዳጊ ሀገራት ከፖለቲካዊ ጫና ነፃ የሆነ የብድር አማራጭ እያቀረበ ይገኛል። በተጨማሪም በአባል ሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ማደግ እና ጥምረቱ የደቡብ ዓለም (Global South) ድምፅ ሆኖ መውጣቱ ለጥምረቱ መጠናከር የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው።
በኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ያሳተፈች ሲሆን፣ በጉባኤው ጎን ለጎንም ከህንድ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ አቡዳቢ እና ቬትናም መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶች ተካሂደዋል።
“ዘላቂነትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ጥንካሬን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የመሪዎቹ ጉባኤው፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ሰፊ አቅም የፈጠረ መድረክ ነበር።
ከዚህ ግዙፍ የባለብዙ ወገን መድረክ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች የኢትዮጵያን ተሰሚነትና ተመራጭነት ያሳዩ ወሳኝና ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ መገለጫዎች ናቸው።
ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ ጋር የተደረጉት ዉይይቶች የሀገራችንን የመከላከያ አቅም ከማሳደግ ባሻገር፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች የነበረንን አጋርነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ናቸው።
በተመሳሳይ ከማሌዢያ፣ ከቪየትናምና ከኢራን መሪዎች ጋር የተደረጉት የትኩረት ምክክሮች ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ገለልተኝነቷንና ነፃነቷን ጠብቃ፣ ከምዕራቡም ሆነ ከምስራቁ ዓለም ጋር ሚዛናዊ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ትስስር የመፍጠር ብስለቷን ያንጸባረቁ ናቸው።
ኢትዮጵያ በጉባኤው ላይ ያቀረበቻቸው እና ትኩረት ያገኙ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችም የሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የተሰሚነት ደረጃ ይበልጥ ያጎላ ነው፡፡
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ በቀረበው የኒው ዴልሂ ዲክላሬሽን ላይ ለኢትዮጵያ የተሰጡት ድጋፎች የሀገሪቱን ሁለገብ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች ይበልጥ የሚያጎለብቱ ሆነው ተገኝተዋል።
በዚህም የብሪክስ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እና በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት ውስጥ የምታደርገውን ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።
ብሪክስ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፉን COP 32 የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ላቀረበችው ጥያቄ እና ለፕሬዝዳንትነቱ ያላትን ዝግጁነት ሙሉ ድጋፉን ሰጥቷል።
የባህር በር እና የንግድ አማራጭን በተመለከተ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት ቀዳሚ የኢኮኖሚ ህልውና ጉዳይ መሆኑ የገለፀች ሲሆን፣ ሀገሪቱ የወታደራዊ እና ንግድ ወጪዎችን ለመቀነስ ሰላማዊ እና የምክክር መንገዶችን እንደምትከተል አብራርታለች።
ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ፣ የዲጂታል ክፍያ እና የዳታ ልውውጥ ስራዎችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ፣ አፍሪካን ማዕከል ያደረገ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ለማልማት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም በመድረኩ ገልጻለች።
ይኸው የብሪክስ ጉባኤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪነት መድረኮች ላይ የሚገባት ድምፅ እንድታገኝ፣ የፋይናንስ እና የገበያ አማራጮቿን እንድታሰፋ ትልቅ መንገድ የከፈተና የዲፕሎማሲ አቅሟ ከፍ ብሎ እንዲታይ ያስቻለ መድረክ ሆኖ አልፏል።

25 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) በህንድ ኒው ዴልሂ ሲካሄድ የቆየው የዘንድሮው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ፣ የተለመዱትን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከሪያ እና የጋራ ፖሊሲ ቃላቶች በመለዋወጥ ተጠናቋል። ይሁንና ጉባዔው አንድ ትልቅ እና አንገብጋቢ ጉዳይን ሆን ብሎ በዝምታ አልፎታል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት አብዛኛዎቹን አሥራ አንድ የብሪክስ አባላት እና አሥር አጋር ሀገራትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ቢሆንም፣ ቡድኑ ባወጣው የጋራ መግለጫ ላይ ጦርነቱን አላነሳም፤ እንዲሁም ግልጽ አጥቂ የሆነችውን አሜሪካን ከማውገዝ ተቆጥቧል። ይህ ሁኔታ ብሪክስ ያለውን ግዙፍ የኢኮኖሚ ጡንቻ ወደ ተባበረ የጂኦ-ፖለቲካዊ እርምጃ ለመቀየር ምን ያህል እንደሚቸገር ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።
የብሪክስ ፖለቲካዊ ድክመት አሁን ብቻ የተከሰተ አይደለም። ባለፈው ግንቦት ወር በኒው ዴልሂ በተካሄደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይም ተመሳሳይ ሽኩቻ ታይቶ ነበር። በወቅቱ ኢራን የአሜሪካ እና የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ በቡድኑ በይፋ እንዲወገዝላት ብትጠይቅም፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግን የራሷን የደህንነት ስጋት እና የኢራንን ጥቃቶች ያላካተተ መግለጫ እንዲወጣ አልፈቀደችም። ይህ የሚያሳየው፣ የብሪክስ አባላት ቁጥር ማደግ የቡድኑን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ቢያሰፋውም፣ በተጓዳኝ ደግሞ እንደ ኢራን እና ኤምሬትስ ያሉ አደገኛ ቀጠናዊ ጠላትነቶችን ወደ ድርጅቱ ውስጥ ይዞ እንዲገባ አድርጎታል።
ብሪክስ በአሜሪካ ከሚመራው የምዕራባውያን የዓለም ሥርዓት የተለየ አማራጭ ለመፍጠር የተቋቋመ ቢሆንም፣ አባላቱ ከአሜሪካ ጋር ባላቸው የተለያየ የጥቅም ትስስር የተነሳ የጋራ አቋም መያዝ ተስኗቸዋል። ለምሳሌ ህንድ ብሪክስን የምትጠቀመው የራሷን የስትራቴጂክ ነጻነት ለማስፋት እንጂ ፀረ-አሜሪካ ጦር ለመገንባት አይደለም፤ በመሆኑም ከምዕራባውያን ጋር ያላትን ወታደራዊ እና የኢኮኖሚ ትስስር እያጠናከረች ትገኛለች። ሩሲያ የብሪክስን መድረክ የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለማምለጫ ብትጠቀምበትም፣ ከአሜሪካ እና ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጋር ቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ውስጥ መግባትን አትፈልግም። ቻይናም ቢሆን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቱን መለወጥ ብትፈልግም፣ አሜሪካ ለኤክስፖርት ምርቶቿ ትልቅ ገበያ በመሆኗ በየጉዳዩ ሁሉ ከዋሽንግተን ጋር መላተም አያዋጣትም። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል እና ኢንዶኔዥያ ያሉት ሀገራት ዋነኛ ፍላጎታቸው ፍትሃዊ የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት እንዲፈጠር እና ለታዳጊ ሀገራት የልማት ብድር እንዲስፋፋ እንጂ፣ በጂኦ-ፖለቲካዊ ፍልሚያዎች የቻይና ወይም የሩሲያ መጠቀሚያ መሆን አይደለም።
እንዳስተዋልነው ከሆነ ብሪክስ በባለብዙ-ማዕከል ወጥመድ ውስጥ ወድቋል። የስብስቡ ትልቁ ጥንካሬው ብዝሃነቱ ቢሆንም፣ ይኸው ብዝሃነቱ ደግሞ የጠራ ጂኦ-ፖለቲካዊ ርምጃዎችን በጋራ እንዳይወስድ ማነቆ ሆኖበታል። የኢራን ጦርነት ይህንን ተቃርኖ ይበልጥ አጉልቶታል። ይሁንና፣ ይህ የፖለቲካ አቋም ማነስ እንደ በረከት ሊታይ ይችላል። ብሪክስ አሜሪካን በቀጥታ ጦርነት እና ግጭት ከመውጋት ይልቅ፣ የዓለምን የፋይናንስ ሥርዓት እና ተቋማትን በማሻሻል፣ ዶላርን በሌሎች የክፍያ አማራጮች በመተካት እና ለታዳጊ ሀገራት የዲፕሎማሲ አማራጭ በመሆን ሥርዓቱን ቀስ በቀስ ለመለወጥ መገደዱ ይበልጥ ዘላቂ እና አዋጭ የሆነ ኃይል እንዲኖረው ያደርገዋል።
ብሪክስ በዚህ ልክ በውስጥ ልዩነቶች እየታመሰ እና የጋራ ፖለቲካዊ አቋም መያዝ እየተቸገረ፣ በእርግጥም የዓለምን የኃይል ሚዛን ሊቀይር እና የአሜሪካን ተጽዕኖ ሊገታ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? ወይስ የኢኮኖሚ ትብብሩ ብቻውን በቂ ነው? ሐሳብዎን እንዲያስቀምጡ ጋብዘናል።

26 days ago
የብሪክስ መሪዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጠቃላይ ሪፎርም እንዲደረግበት ጠየቁ
*****************
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) እና የፀጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይበልጥ ዴሞክራሲያዊ እና ውክልናን ያረጋገጡ እንዲሆኑ አጠቃላይ የማሻሻያ (ሪፎርም) ዕርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠየቀ።
ከዚህ ቀደም ተመድ እና የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም እንዲደረግባቸው እና አፍሪካ ተገቢውን ውክልና እንድታገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጠየቃቸው አይዘነጋም።
የብሪክስ መሪዎች ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ ላይ፣ በተለይም አሁን ያለውን የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዋቅር የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ይበልጥ እንዲያንጸባርቅ አድርጎ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
መግለጫው በተለየ ሁኔታ አሁን እየተካሄደ ያለውን የቀጣዩን የተመድ ዋና ጸሐፊ ምርጫ ሒደት በማንሣት፣ በድርጅቱ ታሪክ እስካሁን ድረስ አንዲትም ሴት ለዋና ጸሐፊነት ተመርጣ እንደማታውቅ በትኩረት አንሥቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ከላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን አንድ ሰው ብቻ፣ ከአፍሪካ እና ከእስያ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሁለት ሰዎች ብቻ ይህንን ቦታ መያዛቸውን በማስታወስ የውክልና ክፍተቱን አመላክቷል።
የተመድን የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርምን በተመለከተም መሪዎቹ ጠንካራ አቋም አንፀባርቀዋል። ምክር ቤቱ አሁን ላለው ዓለም አቀፍ ፈተና ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዲችል የአዳጊ ሀገራትን ውክልና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ እና በተለይም በአፍሪካ ሀገራት በ‘ኤዙልዊኒ ስምምነት’ እና በ‘ሲርቴ የአቋም መግለጫ’ ላይ የተንጸባረቀው ሕጋዊ ጥያቄ ዕውቅና ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም የደቡቡን ክፍለ ዓለም ድምፅ እንዲጎላ የሚያደርግ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት ቻይና እና ሩሲያ፣ ብራዚል እና ሕንድ በተመድ ውስጥ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ያላቸውን ድጋፍ ዳግም አረጋግጠዋል።
በተመድ ሴክሬታሪያት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የውሳኔ አሰጣጥ ሒደቶች ላይ አፍሪካን፣ እስያን እና ላቲን አሜሪካን ጨምሮ አዳጊ ሀገራት ፍትሐዊ የጂኦግራፊያዊ ውክልና ሊኖራቸው እንደሚገባ የብሪክስ መሪዎች አሳስበዋል።
በእነዚህ ተቋማት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሴቶችን በተለይም ከአዳጊ ሀገራት የመጡ ሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
የተመድ የሥራ አስፈጻሚዎች እና የከፍተኛ ኃላፊዎች ሹመት የትኛውንም ሀገር ወይም የሀገራት ስብስብ የበላይነት የሌለበት እና ግልጽነትን የተከተለ መሆን እንዳለበት አቋማቸውን አንፀባርቀዋል።
መሪዎቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላላ ጉባኤውን ለማነቃቃት፣ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ምክር ቤቱን (ECOSOC) ለማጠናከር እና የሰላም ግንባታ መዋቅሩን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ሆን ብሎ የገንዘብ መዋጮን በመከልከል የዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ተቋማትን ሥራ ለማዳከም የሚደረጉ የተናጠል ሙከራዎችን አጥብቀው አውግዘዋል።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #brics #newdelhideclaration #brics2026

የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እና ዓለም አቀፍ መሪነት ደገፈ
በኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ መደገፋቸውን ገለፁ።
በጉባኤው ማጠቃለያ መግለጫ ላይ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ አዲሶቹ አባል ሀገራት ፍትሃዊና አሳታፊ የዓለም ንግድ ስርዓት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።
ከንግድ በተጨማሪም አባል ሀገራቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት አፍሪካን ወክላ እንድትወዳደር ብቸኛ ዕጩ አድርገው ደግፈዋታል።
በተመሳሳይ የዓለም አቀፉን COP32 የአየር ንብረት ጉባኤ እንድታዘጋጅና እንድትመራ የቀረበውን ጥያቄ በመደገፍ የአፍሪካን መሪነት አጎልብተዋል።
Seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በህንድ፣ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ጉባኤ ላይ የተሰባሰቡት የዓለማችን ታዳጊ የኢኮኖሚ ኃያላን ሀገራት፣ ከምዕራባውያን የሚሰነዘርባቸውን ጫና እና ማዕቀብ በጽኑ አውግዘዋል። ምዕራባውያን የተቆጣጠሩትን የዓለም ሥርዓት ሚዛን ለማስጠበቅ የሚሞክረው ይህ ስብስብ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
በጉባኤው ላይ የኢራኑን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያንን ጨምሮ ታላላቅ መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዕውቅና ውጪ የሚጣሉ የብቻ ማዕቀቦችን አጥብቀው ተቃውመዋል። በተለይም በሲቪል መሠረተ ልማቶች እና በሰላማዊ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ "ሆን ተብለው የታቀዱ ጥቃቶች" ሊቆሙ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃት በተዘዋዋሪ ኮንነዋል። መሪዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ "ዓለም አቀፍ ሕግን እና የተመድ ቻርተርን የሚጥሱ እንዲህ ያሉ ሕገ-ወጥ እርምጃዎች ሊወገዱ ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
የብሪክስ መሥራች የሆነችው ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት፣ እንዲሁም ኢራን ከአሜሪካ በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ መሆናቸው ይታወቃል። የኢራኑ ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን ሀገራቱ ከምዕራባውያን የፋይናንስ ሥርዓት ጥገኝነት እንዲላቀቁ ጥሪ በማቅረብ፣ "በአባላት መካከል በሚደረግ የንግድ ልውውጥ የየራሳችንን ብሔራዊ ገንዘብ መጠቀምን ማስፋፋት አለብን" ብለዋል።
በሌላ በኩል የዚህ ጉባኤ አዘጋጅ የሆነችው ህንድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት የዲፕሎማሲ ሚዛን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ። ሞዲ በአንድ በኩል ከሩሲያ እና ኢራን ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ስታጠናክር (ከጉባኤው በፊት ከሁለቱም መሪዎች ጋር ለየብቻ ተወያይተዋል)፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከአሜሪካ እና አውሮፓ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ትስስር እያሰፋች ትገኛለች።
ባለፈው ግንቦት ወር የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢራን ጦርነት ዙሪያ የጋራ መግለጫ ማውጣት ተስኗቸው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የተሻለ መግባባት ላይ የደረሱ ይመስላል። የብሪክስ ስብስብ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ብራዚል፣ ግብፅ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስን ያካተተ 11 አባል ሀገራት ያሉት ግዙፍ ጥምረት ነው።
ከዚህ ዜና የምንረዳው ትልቁ ቁምነገር፣ የዓለም የኃይል ሚዛን አቅጣጫውን እየቀየረ መሆኑን ነው። ብሪክስ አሁን ላይ የኢኮኖሚ ስብስብ ብቻ መሆኑ አክትሞ፣ የምዕራባውያንን (በተለይም የአሜሪካን) የዶላር እና የማዕቀብ ፖለቲካ በይፋ የሚሞግት የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ሆኖ እየወጣ ነው።
እናንተስ ምን ይመስላችኋል? ይህ የብሪክስ ሀገራት ጥምረት በእርግጥም የዶላርን የበላይነት እና የምዕራባውያንን ጫና ተቋቁሞ አዲስ የዓለም ሥርዓት መፍጠር የሚችል ይመስላችኋል? ሐሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን!

27 days ago
የኢትዮጵያ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት
*************************
በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ላለፉት ዘመናት አንድ ወገን ብቻ ይመራ የነበረው “ባለ አንድ ማዕከል” የኃይል ሚዛን አሁን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ባለ ብዙ ማዕከላት እሳቤ እየተቀየረ ይገኛል።
አዳዲስ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ኃይሎች በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልተው እየወጡ ባሉበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በውጭ ግንኙነቷ ተመልካችና ውሳኔ ተቀባይ ሆና ከመቀጠል ይልቅ ንቁ ተሳታፊና የኖረ ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ሚናዋን እንደገና እያደሰች ትገኛለች።
ይህንን የዓለም አቀፍ ሥርዓት መዋቅራዊ ለውጥ በግልጽ የሚያሳየው ታሪካዊ ክስተት ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሆና በይፋ የተቀላቀለችበት ታኅሣሥ 22ቀን 2016 ዓ.ም ነው።
ይህም የሀገራችን ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ላይ እንዳደረሰው ይታመናል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ስብስብ አባል እንድትሆን የቀረበላት ጥሪ እና ሙሉ አባልነቷን ማረጋገጧ በተለመዱ የዲፕሎማሲ አካሄድ የተገኘ ውጤት አይደለም።
ይልቁንም ሀገራችን በምስራቅ አፍሪካ ያላትን የጂኦ-ፖለቲካዊ ክብደት፣ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ የኢኮኖሚ አቅም እና የታሪክ ባለቤትነቷን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመሰከረችበት አጋጣሚ ነው።
ከዓለም ሕዝብ ቁጥር፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ (GDP) እና የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙት ታዳጊ ሀገራት ጋር በጋራ መሰለፍ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ያላትን የመደራደር አቅም በእጅጉ ያሳድገዋል።
ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ሕብረት መስራች በመሆን በታሪክ የሚታወቅ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ተሟጋች በመሆኗ፣ የብሪክስ አባልነቷም ይህንኑ ታሪካዊ መርህ በዘመናዊ መልኩ የማስቀጠል አካል ነው።
ይህም ታዳጊ ሀገራት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቂ ድምፅና ውክልና እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንድትሆን ያደርጋታል።
በብሪክስ ስር የሚገኘው “አዲሱ የልማት ባንክ” ለኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና የልማት ፕሮጀክቶች ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ከፖለቲካዊ መስፈርቶች ነፃ የሆነ አማራጭ ያቀርባል።
የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በርካታ በሮችን የሚከፍት ሲሆን፤ እንደ ቻይና፣ ሕንድ፣ ብራዚል እና ሩሲያ ካሉ የቡድኑ አባላት የሚመጣውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ የመሳብ ዕድል ይፈጥራል።
የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ታላላቅ የዓለም ገበያዎች ያለ ምንም ገደብ እንዲገቡና የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃም ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል እና በግብርና ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ያፋጥናል።
ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከምዕራባውያን ወዳጆቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጥ ወይም መተው ማለት አይደለም።
ይልቁንም ሀገራችን ከምዕራቡም ሆነ ከምስራቁ ዓለም ጋር የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የተመጣጠነ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን የመከተል ብስለቷን ያሳያል።
ይህ አካሄድ ኢትዮጵያ በማንኛውም ወገን ጥገኛ ሳትሆን ብሔራዊ ጥቅሟን በብቃት እንድታስከብርም ያስችላታል።
ዓለም ወደ አዲስ ባለ ብዙ ማዕከል አወቃቀር በምትሸጋገርበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ድምፅ በማስተጋባት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በማጠናከር እና የራሷን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ረገድ ቁልፍ ሚናዋን መጫወቷን ትቀጥላለች።
በአድማሱ አራጋው
#brics #ethiopiandiplomacy #multipolarworld #newdevelopmentbank #ethiopiarising

ብሪክስ ለኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ እና የቱሪስት ፍሰት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪክስ ለኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ እና የቱሪስት ፍሰት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ የጥምረቱ ሙሉ አባል ከሆነች ጊዜ ጀምሮ ብሪክስ በባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ያላትን ተፅዕኖ ከመጨመሩም በላይ፣ ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጥቅሞችን እንድታገኝ በር ከፍቶላታል።
በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ እና የብሪክስ ተወካይ ሀይማኖት እሸቱ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት÷ ብሪክስ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አዳዲስ እድሎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡
በተለይም የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን የሀገሪቱን የቱሪስት ፍሰት እና የአቪዬሽን ዘርፍ ለማነቃቃት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
የብሪክስ ጥምረት የዓለምን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር እና ፈጣን ኢኮኖሚ የያዙ ሀገራትን ያቀፈ እንደሆነ እና ይህም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲሁም አዳዲስ የገበያ እድሎችን እየከፈተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አባል ሀገራቱ በጋራ የቱሪዝም ምርቶችን የሚያስተዋውቁበት፣ የኢንቨስትመንት እና የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት የጋራ መድረክ ለመፍጠር ኢትዮጵያ ንድፈ ሃሳብ ማቅረቧንም ጠቁመዋል፡፡
እንደ ቲቪ ብሪክስስ ዘገባ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ሕንድ እና ብራዚል ካሉ ትላልቅ የቱሪስት ምንጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እንደሆነ እና ይህም ለኢትዮጵያ አቪዬሽን እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለው ሰፊ የአፍሪካ የበረራ መዳረሻዎች አጠቃላይ አፍሪካን ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሚያገናኝ ዋና የአቪዬሽን ድልድይ ሆኖ እንዲያገለግል አስችሎታል፡፡
በተጨማሪም በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል የሚደረጉ የቀጥታ በረራዎች መጨመር የጉዞ ሂደትን ቀላል ከማድረጉም በላይ የአየር መንገዱን ገቢ እያሳደገው ይገኛል፡፡
በ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ወጪ በሚገነባው ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የብሪክስ አባል ሀገራት የገንዘብ እና ቴክኒካል ድጋፎችን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን የሀገሪቱን የቱሪስት ፍሰት እና የአቪዬሽን ዘርፍ በማነቃቃት ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እያበረከተ ይገኛል፡፡
በሚኪያስ አየለ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝደንት ፑቲን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰማ፡፡ በህንድ አስተናጋጅነት የሚከናወነው 18ተኛው የብሪክስ ጉባኤ ከወዲሁ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በህንድ ኒውዴልሂ ከተማ በሚገኘው ባህራት ማንዳፓም የተሰናዳው 18 የብሪክስ አባል አገራት ጉባኤ ነገ ቅዳሜና እሁድ ይከናወናል፡፡ ይህ ጉባኤ የ11ዱን የብሪክስ አባል አገራት ማለትም ብራዚል፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራን፣ ሩሲያ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካና ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ መሪዎችን አንድ ላይ የሚያገናኝ ነው፡፡ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደገለፀው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ጠዋት የገቡ ሲሆን እሳቸውን ተከትለው የኢራኑ ፕሬዝደንት መሱድ ፐዚኪሺያን ህንድ ደርሰዋል፡፡
የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂፒንግ ነገ ቅዳሜ የሚገቡ ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎዛ እዛው ናቸው፡፡ ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስን በጉባኤው የሚወክሉት የአቡ ዳቢው አልጋ ወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያ ሲሆኑ ብራዚል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡ የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የግብፁን ፕሬዝደንት አልሲሲን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎች በስብሰባው ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡
ከብሪክስ አባል አገራት መሪዎች በተጨማሪ የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒትር አንዋር ኢብራሂም፣ የቬተናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ሚንህ ሁንግና የፊሊፒንስ ፕሬዝደንት ፈርዲናልድ ማርቆስ በጉባኤው የሚገኙ ከመሆናቸውም በላይ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝና የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጉባኤ ጎን ለጎን የተለያዩ አገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ለምሳሌ የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በነገው እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸውን የሩሲያ ፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የህንዱ ፕሬዝደንት ናሬንድራ ሞዲም ነገ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ለመወያየት ሌላ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

29 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በጸጥታ ስጋትና በምሽት የሰዓት እላፊ ገደብ ምክንያት በየከተሞቹ ለማደር የሚገደዱ የጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች፣ ህገ-ወጥ "የኮቴ ክፍያ" እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑ ተሰምቷል። አሽከርካሪዎቹ እንደሚያነሱት ከጅቡቲ እና ከሌሎችም አካባቢዎች እቃ ጭነው የሚመጡ ባለ ተሳቢ ከባድ ተሽከርካሪዎች ለአንድ አዳር 1 ሺሕ 200 ብር ለመክፈል ይገደዳሉ። እንዲሁም ገልባጭ ሲኖትራክና በተለምዶ "ካሶኒ" ተብለው የሚጠሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች 800 ብር፣ ኤፍ ኤስ አር (FSR) 700 ብር፣ የጭነት አይሱዙዎች ደግሞ 500 ብር የኮቴ ክፍያ እንዲከፍሉ ግዳጅ ተጥሎባቸዋል።
ይህ ጉዳይ የአሽከርካሪዎች ምሬት ብቻ አይደለም፤ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የተጠመደ የሰዓት ቦምብ ነው። አሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ የሚከፍሉት እያንዳንዱ ህገ-ወጥ ክፍያ በመጨረሻ የሚጫነው በሸማቹ ላይ በመሆኑ፣ ለኑሮ ውድነት መባባስ ቀጥተኛ ምክንያት ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታሪክን ስንመረምር በመንገድ ትራንስፖርት ላይ የሚደረግ እንዲህ ዓይነት ያልተገባ ብዝበዛ መንግስታትን ክፉኛ አናውጧል። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ2018 በብራዚል የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች በነዳጅ ዋጋ እና በህገ-ወጥ የኬላ/የመንገድ ክፍያዎች ምክንያት ያደረጉት ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሽባ ከማድረጉም በላይ የሚሼል ቴመርን መንግስት ህልውና እስከመፈታተን ደርሶ ነበር። በናይጄሪያም በኬላዎች ላይ በፖሊስና በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝርፊያ ታላላቅ ሀገር አቀፍ ተቃውሞዎችን አስነስቷል። የትራንስፖርት እና የንግድ መስመሮች በህገ-ወጥ "ቀረጥ" ሰብሳቢዎች እጅ መውደቅ የመንግስትን የሕግ የበላይነት የሚያሳጣ፣ የዜጎችን አመኔታ የሚሸረሽርና አደገኛ የፖለቲካ ቀውስ የሚጋብዝ ነው።
መንግስት የንግድ እና የትራንስፖርት መስመሮቹን ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻለ፣ እየፈጠረ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ማዕበልም ጭምር ነው! ህገ-ወጥ "የኮቴ" ሰብሳቢዎችን ዝም ማለት፣ የኑሮ ውድነትን በይፋ መፍቀድ እና የመንግስትን ስልጣን ለጎዳና ኃይሎች አሳልፎ መስጠት ነው። ትራንስፖርት የሀገር ደም ስር በመሆኑ፣ መንግስት የነፃ ንግድ ዝውውርን በማረጋገጥ በአስቸኳይ ህግ ሊያስከብር ይገባል!

1 month ago
በምርቃቱ ቀን የጋዝ ሲሊንደር ተሸክሞ የዋለው ወጣት
#ethiopia | በብራዚል ኢንጂነሪንግ የተመረቀው ወጣት ሎሬንዞ ሞንፋርዲኒ በምርቃት ስነ ሥርዓቱ ወቅት በትከሻው ያኖረው ቁስ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
ወጣቱ በምርቃቱ ዕለት የጋዝ ሲሊንደር ተሸክሞ በመገኘት ለአባቱ ያለውን የላቀ አክብሮትና ምስጋና ገልጿል። አባቱ ለ26 ዓመታት ያህል በጋዝ ማደል ሥራ ላይ ተሰማርተው በመስራት የወጣቱን የትምህርት ህልም እውን ለማድረግ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል።
ለሎሬንዞ ይህ ተሸክሞት የቀረበው የጋዝ ሲሊንደር ተራ ቁስ ሳይሆን የአባቱ የዓመታት ድካም፣ ጥረት እና የመስዋዕትነት ምልክት ነው።
ወጣቱ የምርቃት ስኬቱ የራሱ ብቻ ሳይሆን አባቱ እስከዚያች ታላቅ ቀን ድረስ እንዲደርስ ያደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍና መስዋዕት ማሰብያ እንደሆነ ተናግሯል።
ይህ የልጆች ስኬት ጀርባው ትልቅ ታሪክና ዋጋ ያለውን የቤተሰብ ፍቅርና ድካም ለዓለም ያሳየ ድንቅ ክስተት ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ጋብሬል ማርቲኔሊ፣ በአርሰናል ቤት የተጻፈ የትጋት ታሪክ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሰናል የቅርብ ዓመታት የዳግም ግንባታ ጉዞ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል ጋብሬል ማርቲኔሊ አንዱ ነው። ወጣቱ ብራዚላዊ በፍጥነቱ፣ በጉልበቱ፣ ተከላካዮችን በአንድ ለአንድ ለመጋፈጥ ባለው ድፍረቱ እና ጎል ለማስቆጠር ባለው ክህሎት የመድፈኞቹ ደጋፊዎችን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
ጋብሬል ቴዎዶሮ ማርቲኔሊ ሲልቫ በፈረንጆቹ 2001 በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት ጉዋሩልዮስ ተወለደ።
የእግር ኳስ ህይወቱን በኮረንቲያንስ አካዳሚ በመጀመር በኋላም በኢቱዋኖ ቀጠለ። በኢቱዋኖ በዋናው ቡድን ዕድል ካገኘ በኋላ የብራዚላዊው ወጣት ችሎታ በአውሮፓ የተለያዩ ክለቦች ዓይን ውስጥ ገባ።
በመጨረሻም እ.ኤ.አ በ2019 አርሰናል፣ ተስፈኛውን ታዳጊ ተጫዋች ወደ ሰሜን ለንደን አመጣው። ማርቲኔሊ በአርሰናል ቤት የተሰጠውን ዕድል በፍጥነት በመጠቀም ለቡድኑ የሚያስፈልገው የግብ ስጋት ሆነ።
ማርቲኔሊ ወደ አርሰናል ሲመጣ ብዙዎች እንደ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋች ብቻ ይመለከቱት ነበር። እሱ ግን የሰዎችን ግምት በፍጥነት ለወጠው። ፍጥነቱን በመጠቀም በግራ ክንፍ ተከላካዮችን መጫን፣ ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ መግባት እና ጎል ማስቆጠር የአጨዋወቱ ዋነኛ መለያዎች ሆኑ።
በተለይም በ2019/20 የውድድር ዘመን ያሳየው ብቃት የአርሰናል ደጋፊዎች በወጣቱ ላይ ትልቅ ተስፋ እንዲጥሉ አደረገ። እሱ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ትጋትና የማይታክት ሩጫ ለቡድኑ አጨዋወት መለያ እየሆነ መጣ።
ለማርቲኔሊ የአርሰናል ቆይታ እጅግ የሚታወሰው የ2022/23 የውድድር ዘመን ነው። በዚያ ወቅት ተጫዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ 36 ጨዋታዎች በመሳተፍ 15 ጎሎችን አስቆጠረ፤ በተጨማሪም 5 የግብ እድሎችን ፈጥሯል፡፡
ይህ የግል ብቃቱ ብቻ ሳይሆን አርሰናል እስከ መጨራሻው ሰዓት የሊጉ አሸናፊ ለመሆን ከፔፕ ጓርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር የተፋለመበት ወቅት ነበር። ማርቲኔሊ፣ ቡካዮ ሳካ እና ሌሎች ወጣት ተጫዋቾች የአርሰናልን የወደፊት ቡድን ምስል እንዲያሳይ አጨዋወት አሳይተዋል።
ማርቲኔሊን ከሌሎች የክንፍ ተጫዋቾች የሚለየው ነገር በኳስ ላይ ያለው ችሎታ ብቻ አይደለም። ኳስ ሲበላሽበት ወዲያውኑ መልሶ ለመንጠቅ የሚያደርገው ጥረት፣ ተከላካይን በፍጥነት ለመጫን ያለው ፍላጎት እና ከኳስ ውጭ የሚያደርጋቸው ሩጫዎቹ ናቸው።
የግራ ክንፍ ቦታውን በመያዝ ወደ ውስጥ በመግባት በቀኝ እግሩ ጎል ለመሞከር የሚያደርገው እንቅስቃሴም የተለመደ ነበር። በአርሰናል ቤት ቆይታው 41 ግችንና 24 ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበሉ የሚያሳየውም በቡድኑ የማጥቃት ሥርዓት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ተፅዕኖ ነው።
በመጨረሻዎቹ የአርሰናል ቆይታው የማርቲኔሊ የመጫወቻ ጊዜ እንደ ቀድሞው የተረጋጋ አልነበረም። የቡድኑ የማጥቃት አማራጮች መጨመር፣ የተጫዋቾች ውድድር እና ራሱ የማርቲኔሊከቡድኑ እኩል ማደግ አለመቻል በቋሚ 11 ውስጥ የመሰለፍ እድሉን አመነመነው፡፡
በ2025/26 የውድድር ዓመት 30 ጨዋታዎች ቢያደርግም በ11 ብቻ ነው በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት የቻለው፡፡ በዚህም አንድ ግብና 4 የግብ እድሎችን ብቻ አስመዝግቧል።
በአጠቃላይ በአርሰናል ቆይታው 191 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በማድረግ 41 ግቦችና 24 የግብ እድሎችን በማስመዝገብ በመድፈኞቹ ቤት የራሱን ታሪክ አኑሯል፡፡
ብራዚላዊው አቦ ሸማኔ በተዘጋው የዝውውር መስኮት ወደ ሳዑዲው አል ሂላል እግር ኳስ ቡድን ተዛውሯል፡፡ ከአርሰናል መለየቱ ለብዙ የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ቀላል የሆነ ዜና አልነበረም። በተለይም በቡድኑ ውስጥ ካሳለፈው ረጅም ጊዜ እና ከደጋፊዎች ጋር ከፈጠረው ትስስር አንፃር መሰናበቱ የአንድ ዘመን የታሪክ ምዕራፍ መዝጊያ ይመስላል።
ከአርሰናል ጋር ያሳለፋቸው ዓመታት ሲደመሩ ማርቲኔሊ በክለቡ ታሪክ ውስጥ የራሱን ምዕራፍ ጽፏል። ወደ ክለቡ የመጣው እንደ ወጣት ተስፈኛ ነበር፤ የወጣው ግን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ነው፡፡
ማርቲኔሊም ከአርሰናል የሚወጣው በፍጥነቱ ተከላካዮችን ሲያስጨንቅ፣ ግብ ሲያስቆጥር፣ በሜዳ ላይ ሲሮጥ እና የመድፈኞቹን ማልያ በኩራት ሲለብስ የታዩትን ትዝታዎች ትቶ ነው።
ከለንደን ወደ ሳዑዲ የተደረገው ጉዞ ለማርቲኔሊ አዲስ ምዕራፍ ቢሆንም፣ በአርሰናል የተጻፈው ታሪክ ሁሌም የእግር ኳስ ሕይወቱ አንድ ትልቅ ክፍል ሆኖ ይዘልቃል።
በአቤል ነዋይ

ኢትዮጵያ በ73ኛው የሚስ ወርልድ የባህል ውዝዋዜ ውድድር አንደኛ ደረጃን ያዘች
#fastmereja | በ2026 በሚካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ምርጥ ውዝዋዜዎች ዘርፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
እንደ ቢፔጀንት ኮርነር ይፋዊ ደረጃ አሰጣጥ መረጃ፣ የኢትዮጵያ ተወካይ ውበትንና ባህላዊ እሴትን በተላበሰ ድንቅ የውዝዋዜ ብቃት የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ የቀደመች ሲሆን፣ ማሌዢያ እና ህንድ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ፍሬንች ጊያና እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ደግሞ በምርጥ አምስቱ ውስጥ ተካተዋል።
በዚሁ ዝርዝር ውስጥ
ኩክ አይላንድስ
ፈረንሳይ
ብራዚል
ቦሊቪያ
ቬትናም
ላኦስ
ኢንዶኔዢያ
ኢኳቶሪያል ጊኒ
ቺሊ
ፖላንድ
ቤልጂየም
ስፔን
ታይላንድ
ኔፓል
ስሪላንካ የተወከሉ ተወዳዳሪዎች በምርጥ 20 ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት ችለዋል።
የውድድሩ የዳኝነት አካላት የኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ያቀረበችውን ድንቅ የባህል እንቅስቃሴ፣ አልባሳት እና አጠቃላይ የውዝዋዜ ክህሎት ከፍተኛ ነጥብ በመስጠት እንዳደነቁት ተነግሯል።
#fastmereja | በ2026 በሚካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ምርጥ ውዝዋዜዎች ዘርፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
እንደ ቢፔጀንት ኮርነር ይፋዊ ደረጃ አሰጣጥ መረጃ፣ የኢትዮጵያ ተወካይ ውበትንና ባህላዊ እሴትን በተላበሰ ድንቅ የውዝዋዜ ብቃት የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ የቀደመች ሲሆን፣ ማሌዢያ እና ህንድ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ፍሬንች ጊያና እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ደግሞ በምርጥ አምስቱ ውስጥ ተካተዋል።
በዚሁ ዝርዝር ውስጥ
የውድድሩ የዳኝነት አካላት የኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ያቀረበችውን ድንቅ የባህል እንቅስቃሴ፣ አልባሳት እና አጠቃላይ የውዝዋዜ ክህሎት ከፍተኛ ነጥብ በመስጠት እንዳደነቁት ተነግሯል።
1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር የቦንድ ግዢ ዕቅዱን ማሳወቁን ተከትሎ የዶላር አቅም መዳከሙ፣ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች አዳዲስ የትርፍ አማራጮችን ፍለጋ ፊታቸውን ወደ ታዳጊ ገበያዎች እንዲያዞሩ እያደረጋቸው መሆኑን የኢኮኖሚ ትንታኔዎች አመለከቱ። ባለፈው ወር የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት የዋጋ ንረትን እና የዕዳ ጫናን ለማርገብ በማሰብ፣ የረዥም ጊዜ የመንግስት የዕዳ ሰነዶችን (ቦንዶችን) መልሶ የመግዛት ዕቅድን በእጥፍ ማሳደጋቸው ይታወሳል።
በብሩኪንግስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሮቢን ብሩክስ እንዳሉት ታዳጊ ገበያዎች በቀጣይነት ከፍተኛ የሆነ "የገንዘብ ጎርፍ" ያስተናግዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ታላላቅ ያደጉ ሀገራት የመንግስት ቦንድ ወለድን ለመቀነስ የሚያደርጉት ጥረት፣ ባለሀብቶች በዝቅተኛ ወለድ ገንዘብ ተበድረው ከፍተኛ ትርፍ ወደሚያስገኙ ታዳጊ ገበያዎች እንዲያፈሱ ምቹ ሁኔታ ስለፈጠረላቸው ነው። የአሜሪካ መንግስት በገበያው ውስጥ ጣልቃ መግባቱ፣ የብድር ወለድ በድንገት እንዳያሻቅብ በማድረግ የባለሀብቶችን ስጋት በእጅጉ ቀንስዋል።
በቲዲ ሴኪዩሪቲስ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዓለም አቀፍ የታዳጊ ገበያ የቦንድ ፈንዶች ባለፈው ሳምንት ብቻ 967 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የገንዘብ ፍሰት አግኝተዋል፤ ይህም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ አለው። በሌላ በኩል ባለሀብቶች ይበልጥ አስተማማኝ ወደሆኑ የሀብት ማከማቻ አማራጮች ፊታቸውን በማዞራቸው፣ የአሜሪካው ውሳኔ ለወርቅ ዋጋ መናርም ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በለንደን የዩኒየን ባንኬር ፕራይቪ የውጭ ምንዛሬ ስትራቴጂ ኃላፊ ፒተር ኪንሴላ...የአሜሪካ መንግስት እርምጃ ዶላርን በማዳከሙ ምክንያት ከፍተኛ ወለድ የሚከፍሉ የታዳጊ ሀገራት ገንዘቦች ዋነኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለምሳሌ የቦንድ ግዢው ከተዋወቀ ወዲህ የደቡብ ኮሪያ ዎን በ2.83 በመቶ፣ የብራዚል ሪያል በ0.64 በመቶ፣ እንዲሁም የደቡብ አፍሪካ ራንድ በ0.59 በመቶ በዶላር ላይ ብልጫ ማሳየት ችለዋል።
እንደ ትንታኔው ከሆነ ብራዚል እና ቱርክ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል። ብራዚል 14 በመቶ እንዲሁም ቱርክ 37 በመቶ የሆነ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ በማቅረባቸው በባለሀብቶች ዘንድ ተመራጭ ሆነዋል። በተመሳሳይ ኮሎምቢያም በዚህ ዓመት ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለች ሲሆን፣ የሀገሪቱ የገንዘብ ዋጋም ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ በ20 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በአንጻሩ እንደ ህንድ ያሉ የእስያ ሀገራት ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ያላቸው በመሆኑ (የህንድ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ምጣኔ 5.25 በመቶ ነው)፣ ከሌሎች ታዳጊ ገበያዎች አንጻር ተመራጭነታቸው ዝቅተኛ መሆኑን የስክዋክ ቦክስ እስያ ዘገባ አመልክቷል። የኢራንን ጦርነት ተከትሎ ከታዳጊ ገበያዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወጥቶ የነበረው የውጭ ገንዘብ፣ አሁን በአሜሪካ የቦንድ ግዢ ፖሊሲ ምክንያት ዳግም እያንሰራራ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አስረድተዋል።

ቅኝ ያልተገዙት ሁለቱ ሀገራት በአዲስ ምዕራፍ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ታይላንድ በጂኦግራፊ የተራራቁ ሀገራት ናቸው። አንድ ግዙፍ ታሪክ ግን ያቀራርባቸዋል፤ የዓለም ታሪክ ሀገራቱን “በቅኝ ግዛት ያልተንበረከኩ” ብሎ መዝግቧቸዋል።
ሁለቱም ሀገራት በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የአውሮፓ ቅኝ ግዛት ማዕበል ተቋቁመው ሉዓላዊነታቸውን ጠብቀው ማቆየት የቻሉ ታሪክ ተጋሪዎች ናቸው።
በቀድሞ ስሟ ሲያም (የአሁኗ ታይላንድ) በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዝና ፈረንሳይ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሰፊ ግዛቶችን ሲቆጣጠሩ፣ በሁለቱ ኃያላን መንግሥታት መካከል ስትራቴጂያዊ ሚዛንነቷን ተጠቅማ ነፃነቷን ጠብቃለች፤ የታይላንድ ጥበበኛ መሪዎች ሀገራቸውን በዲፕሎማሲና በፖሊሲ ማሻሻያዎች ከቅኝ ግዛት ታድገዋል።
በተመሳሳይ ወቅት አውሮፓ አፍሪካን ስትቀራመት ኢትዮጵያ በዓድዋ ጦርነት ጣሊያንን በማሸነፍ ነፃነቷን ያስጠበቀች ሀገር ሆና ተመዝግባለች።
ለሁለቱም ሀገራት ታሪካቸው የብሔራዊ ኩራት ምንጫቸው ነው። ይህ የታሪክ ተጋሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እርሾ ሆኗል። ይህ የጋራ ትርክት በሁለቱ ሀገራት መካከል የመከባበርና የመተማመን መንፈስ እንዲፈጠር አስተዋፅኦም አድርጓል።
ታይላንድና ኢትዮጵያ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በ1956 ዓ.ም የጀመሩ ሲሆን ÷ ይህንን ግንኙነታቸውን ተከትሎም የንግድና የባሕል ግንኙነታቸውን አጠናክረው ቆይተዋል፡፡ ከትናንት እስከ ዛሬ የተሻገረው የሀገራቱ ግንኙነት ኢትዮጵያ ለምትከተለው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እንደማሳያ የሚቆጠር ነው።
ሁለቱ ሀገራት የዜጎችን ጥበቃን በተመለከተ ስምምነቶች ያሏቸው ሲሆን ታይላንድ ወደ ማይናማር ተጭበርብረው ተወስደው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነታቸውን ተጠብቆ እንዲመለሱ ድጋፍ አድርጋለች።
ኢትዮጵያና ታይላንድ የጋራ የኢኮኖሚ እድገት መሻትን ይጋራሉ፤ ይህም ለአዳጊ ባለኢኮኖሚ ሀገራቱ በደቡብ ደቡብ ቅኝት ሌላ የትብብር መድረካቸው ነው። እንዲሁም ባንኮክ በህክምና ቱሪዝም ሰፊ ልምድ ያላት ሲሆን አዲስ አበባ በዘርፉ የአፍሪካ ፊት ቀደም የመሆን ግብ አስቀምጣለች።
በብራዚል በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ወቅት የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪስ ሳንጋምፖንሳ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋር በመገናኘት በተለይ በቱሪዝምና በህክምና አገልግሎት ዘርፎች የትብብር እድሎችን መርምረው ነበር።
ዛሬ ይህ እያደገ የመጣ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው የስራ ጉብኝት የመጀመሪያው በከፍተኛ ሃላፊነት ያለ የታይላንድ መሪ ይፋዊ ጉብኝት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ይህም ታይላንድ ከአፍሪካ አጋሮቿ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ዛሬ ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ጠቃሚ የማምረቻና የሎጂስቲክስ ማዕከል ተደርጋ የምትታይ በመሆኗ፣ ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ተደርጎ ተወስዷል።
በአፈወርቅ እያዩ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጂአይኤ እና ጉቤሊን ጀም ላብ የተባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ኢትዮጵያ በመዳብ ማዕድን የበለጸገና ተቀባይነት ያለውን የ'ፓራይባ ቶርማሊን' መስፈርት የሚያሟላ አዲስ የከበረ ድንጋይ መገኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ሁለቱ ላቦራቶሪዎች ባወጡት መግለጫ መሠረት፣ ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው የተባለ የቶርማሊን ማዕድን መረጃ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ መሰራጨቱን ተከትሎ፣ ሁለቱም ተቋማት የየራሳቸውን ገለልተኛ ምርመራ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። እያንዳንዱ ተቋም የተለያዩ ናሙናዎችን ለብቻው ከመረመረ እና መረጃዎችን ካጠናቀረ በኋላ፣ በማዕድኑ መነሻ እና ምደባ ላይ ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
ጂአይኤ ከኢትዮጵያ የመጣ ነው የተባለውን ይህንን ማዕድን በሰኔ ወር መመርመር መጀመሩን ገልጾ፣ በኋላም ከመቶ በላይ የሚሆኑ ያልተጠረቡ እና የተጠረቡ ናሙናዎችን ለጥናት መቀበሉን አስታውቋል። በሌላ በኩል ጉቤሊን ጀም ላብ ይህንን ማዕድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው በግንቦት ወር ሲሆን፣ በወቅቱ የተመረመሩት ድንጋዮች ከዚህ ቀደም ከብራዚል፣ ሞዛምቢክ ወይም ናይጄሪያ ከተገኙት ማዕድናት ጋር የማይመሳሰል ኬሚካላዊ ባህሪ አሳይተው እንደነበር ሪፖርት አድርጓል። ላቦራቶሪዎቹ እንዳረጋገጡት ከኢትዮጵያ የተገኘው ማዕድን በዋናነት ከመዳብ የተገኘ ቀለም ያለው በመሆኑ፣ ተቀባይነት ባለው የ'ፓራይባ ቶርማሊን' ብያኔ ውስጥ ይካተታል። ማዕድኑ ሰማያዊ፣ አረንጓዴ-ሰማያዊ፣ ሐምራዊ እና ቀለም አልባ የሆኑ ያልተጠረቡ ድንጋዮችን የሚያካትት ሲሆን፣ በርካታ ድንጋዮችም የየራሳቸው የተለያየ ቀለም እና ስብጥር አላቸው።
ይህ አዲስ ግኝት ኢትዮጵያን ከዚህ ቀደም ማዕድኑ ይገኝባቸው ከነበሩት ሀገራት በመቀጠል አራተኛዋ የፓራይባ ቶርማሊን ምንጭ ያደርጋታል። እ.ኤ.አ. በ2019 'ጀምስ ኤንድ ጀሞሎጂ' በተሰኘ መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ እንዳመለከተው፣ የመዳብ ይዘት ያለው ፓራይባ ቶርማሊን ከዚህ ቀደም በብራዚል፣ ናይጄሪያ እና ሞዛምቢክ የተገኘ ሲሆን፣ የማዕድኑ መገኛ ቦታ በዋጋው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በጋራ መግለጫው መሠረት፣ ሁለቱም ላቦራቶሪዎች በኢትዮጵያው ማዕድን ውስጥ ቫናዲየም፣ እርሳስ እና ጋሊየም የተባሉትን ንጥረ ነገሮች በከፍተኛ መጠን አግኝተዋል። እነዚህ ልዩ ባህሪያት የኢትዮጵያን ድንጋዮች ከሌሎች አካባቢዎች ከተገኙት በቀላሉ ለመለየት የሚያስችሉ ሲሆን፣ ወደፊትም የማዕድናትን መገኛ ስፍራ ለመለየት ለሚደረጉ ጥናቶች ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ። ተቋማቱ ከኢትዮጵያ የሚወጣው ማዕድን በስፋት ወደ ገበያ ሲገባ ተጨማሪ መረጃዎችን ማሰባሰባቸውን እንደሚቀጥሉ እና የጥናታቸውን ዝርዝር ግኝቶች በቀጣይነት በሚወጣው መጽሔታቸው ላይ እንደሚያሳትሙ አስታውቀዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ የተሳሳተ መረጃ ማቅረቧ በማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆነ፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ትላንት ሰኞ ኦገስት 24 በማህበራዊ ሚዲያው ባሰራጨው መረጃ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት አወድሷል፡፡ በትራምፕ ‹‹አሜሪካ ትቅደም›› የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ የሁለቱ አገራት አጋርነት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡
ጨምሮም ‹‹ይህ አጋርነት ለአሜሪካዊያንና በአፍሪካ ሁለተኛዋ ባለትልቅ ኢኮኖሚ ለሆነችው ኢትዮጵያ የበለጠ ትርፍ ወደሚያስገኙ አሜሪካ ኢንቨስትመንቶች ያመራል›› በማለት አስታውቋል፡፡ ይህ አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዛሬ በሰፊው መነጋገሪያ ለመሆን ችሏል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት አንዳንዶቹ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ውስጥ 2ተኛዋ ባለትልቅ ኢኮኖሚ ብሎ ማስቀመጡን የተቹ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት ስለአፍሪካ በቂ እውቀት እንደሌላቸው ሲገልፁ ታይተዋል፡፡
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) በቅርቡ ባወጣው የአለም ኢኮኖሚ አውትሉክ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ በ9ነኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ይህ አለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅት በጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ላይ ተመስርቶ በሰጠው የኢኮኖሚ ደረጃ በአፍሪካ ሶስቱ ባለትልልቅ ኢኮኖሚዎች ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅና ናይጄሪያ መሆናቸውን ይፋ ማድረጉም የሚታወቅ ነው፡፡ የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ ላይ እንዲህ አይነት ስህተት ሲፈፅም ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በቅርቡ በብራዚል በተደረገ አንድ ኮንፈረንስ በርካታ የአፍሪካ አገራት በተሳሳተ የካርታ አቀማመጥ ላይ እንዲሰፍሩ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ የኒው ዮርክ (ማንሃተን) የፌደራል አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ጃኔት ቫርጋስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከ75 ሀገራት የሚመጡ ስደተኞች ላይ ጥለውት የነበረውን የኢሚግሬሽን ቪዛ እገዳ ሕገ-ወጥ ነው ሲሉ ውድቅ አደረጉት። ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ፣ ሚኒስትሩ አመልካቾችን በዜግነታቸው ብቻ በመለየት የቪዛ ሂደታቸውን እንዲቋረጥ ያደረጉበት አሰራር ከተሰጣቸው የሕግ ሥልጣን በላይ መሆኑን አመልክቷል።
ይህ የተሻረው የቪዛ እገዳ ከጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሆኖ የቆየ ሲሆን፤ ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ጃማይካን፣ ሄይቲን፣ ሶማሊያን፣ ብራዚልን፣ ኮሎምቢያን፣ ኡራጋይን፣ አልባኒያን፣ ፓኪስታንን፣ ባንግላዴሽን እና በርካታ የአፍሪካ እንዲሁም የካሪቢያን ሀገራትን ያካተተ ነበር። የትራምፕ አስተዳደር እና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዚህ እገዳ በምክንያትነት ያቀረቡት፣ ከእነዚህ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ በሕዝብ ድጎማ እና በመንግሥት ረዳትነት ላይ ጥገኛ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋትን ነበር።
ይሁን እንጂ በካቶሊክ የሕግ ኢሚግሬሽን ኔትወርክ ፣ አፍሪካን ኮሚኒቲስ ቱጌዘር እና በእገዳው በተጎዱ የአሜሪካ ዜጎች ስፖንሰሮች አማካኝነት የቀረበውን ክስ የተመለከቱት ዳኛ ጃኔት ቫርጋስ፣ ውሳኔውን "ግልጽ የሕግ ጥሰት" ሲሉ ገልጸውታል። ዳኛዋ በውሳኔያቸው ላይ እንደገለጹት፣ የፌደራል የኢሚግሬሽን ሕጉ የቆንስላ ኃላፊዎች የአመልካቾችን ቪዛ በዜግነታቸው ምክንያት ብቻ በጅምላ እንዲያግዱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፈቃድ እንደማይሰጥ እና ይህ የጅምላ እገዳ በኮንግረስ ከተቀረጸው የኢሚግሬሽን ሥርዓት ጋር በቀጥታ እንደሚጋጭ አስረድተዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በበኩሉ፣ የተዘረጋው ጥብቅ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ለሀገር ውስጥ ደህንነት እና ኢኮኖሚ አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ይሟገታል። ይሁን እንጂ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሕግ ባለሙያዎች የአስተዳደሩን ፖሊሲዎች የሕግ አግባብነት፣ የዜጎችን የመደመጥ መብት እና በዘር ላይ የተመሰረተ መድልዎን በተመለከተ በፍርድ ቤት መሞገታቸውን ቀጥለዋል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው በዚህ የቪዛ እገዳ መሻር ውሳኔ ዙሪያ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።

የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው ስምምነት
ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ማዕቀፍ ስታካሂድ የቆየችውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር በስኬት በማጠናቀቅ የስምምነት ሰነድ ተፈራርማለች።
የስምምነት ሰነዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ዋና ተደራዳሪ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ተፈራርመዋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ÷ ስምምነቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እና የፖሊሲ ምህዳር ሙሉ በሙሉ ባስጠበቀ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ዲፕሎማሲያዊ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት ሙሉ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ወሳኝ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች በበኩላቸው÷ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የቆየ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት እና የምታካሂዳቸውን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሙሉ ቁርጠኝነት መደገፏን የምትቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት ከቻይና፣ ሩሲያ፣ አርጀንቲና፣ ቱርክ፣ ብራዚል፣ ጃፓን፣ ሕንድ፣ ኒውዚላንድ እና ታይላንድ ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶችን ተፈራርማለች።

በክለቡ ባስ ላይ የማሪዋና ዕጽ ተያዘ
#ethiopia | በሳኦ ፓውሎ ክለብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶቡስ ላይ እፅ ተያዘ።
የክለቡ አባላትና አመራሮች ግን በድርጊቱ እንደሌለበት ተገልጿል።
በብራዚል የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ 86 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማሪዋና በአውቶቡስ ላይ መያዛቸው ነው የተገለፀው።
አውቶቡሱ የሳኦ ፓውሎ እግር ኳስ ክለብ ለተለያዩ ጉዞዎች በኮንትራት የሚጠቀምበት የኪራይ ተሽከርካሪ ነው ተብሏል።
በወቅቱ የክለቡ ተጫዋቾችም ሆኑ የስፖርት ቡድኑ አባላት በተሽከርካሪው ውስጥ አልነበሩም ሲሉ ፖሊሶች ተናግረዋል።
የሳኦ ፓውሎ ክለብም በጉዳዩ ላይ እጁ እንደሌለበትና ከድርጅቱ ጋር ያለውን አገልግሎት በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #sãoPaulo #bolivia #teambus #𝐌𝐀𝐑𝐈𝐉𝐔𝐀𝐍𝐀

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዩኤን ዋች ‹‹የኤርትራ በሰብአዊ ምክር ቤት መመረጥ አስከፊ ቀልድ ነው›› አለ፡፡ መቀመጫውን በጄኔቭ ያደረገውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን አሰራር የሚከታተለው ‹ዩኤን ዋች›› ዛሬ ባወጣው መግለጫ ኤርትራ በተመድ ሰብአዊ መብት ምክር ቤት ውስጥ የማህበራዊ መድረክ ሊቀመንበር ሆና መመረጧን አጥብቆ እንደሚቃወም ገለፀ፡፡ ውሳኔውንም ‹‹በአለም ላይ ካሉ ጨቋኝ መንግስታት አንዱን የሰብአዊ መብትን ለማሳደግ በሚጥር አካል ውስጥ ሀላፊነት መስጠር አስከፊ ቀልድ ነው›› ብሎታል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሂሌል ኑየር ሲናገሩ ‹‹ኤርትራ በወታደራዊ ሀይል የምትተዳደር የአንድ ፓርቲ አምባገነን አገር ስትሆን በፍሪደም ሀውስ ከ100 ነጥብ ውስጥ 3 ያገኘች ናት፡፡ ይህ ማለት የሰብአዊ መብት ሪከርዷ እጅግ የከፋ ነው›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹የኤርትራ መንግስት እ.ኤ.አ ከ1993 አገሪቱ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ ምንም አይነት ብሄራዊ ምርጫ አላካሄደም፡፡
እንደባርነት የሚቆጠር የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን ያስፈፅማል፡፡ የሚተቹትንና ጋዜጠኞችን ለአስርት አመታት ያለምንም ክስ ያስራል፡፡ የፖለቲካ እስረኞችንና የሀይማኖት አባቶችን ያሰቃያል፡፡ ይህ የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ ተብሎ የሚጠራው መንግስት ከሰብአዊ መብቶች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ የኤርትራን መንግስት እዚህ ወንበር ላይ ማስቀመጥ እጅግ መጥፎ ቀልድ ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የራሱን ደንቦች ማክበር እያቃተው ለመሆኑ ይህ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቀሱት ዳይሬክተሩ አስከትለውም ‹‹በሰብአዊ መብት ምክር ቤቱ ውስጥ የተወከሉትን ሁለንተናዊ መብቶች እንደሚከላከሉ የሚናገሩ መንግስታት በተለይም እንደፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ፣ ጣሊያን፣ ስፔን፣ ብራዚልና ስዊዘርላንድ የመሳሰሉ የምክር ቤቱ አባላት ይህንን የኤርትራን ሹመት አውግዘው መግለጫ እንዲያወጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ይህ አፀያፊ ሹመት እንዲቀለበስ በማድረግም የኤርትራ መንግስት በሰብአዊ መብት ረገድ ምንም እውቅና እንዳይሰጠው ማድረግ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡ በማጠቃለያቸውም ‹‹ይህ ሹመት አምባገነንነትን የሚሸልምና የሰብአዊ መብት ምክር ቤቱ የተነሳለትን አላማ የሚክድ ነው፡፡ አለም ይህንን እየተመለከተ ነው፡፡ ዝም የሚሉ ዲሞክራሲዎች ለዚህ አሳፋሪ ውሳኔ ሀላፊነቱን ይወስዳሉ›› በማለት መግለፃቸውን ከመግለጫው ላይ ተመልክተናል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) አርሰናል የኒውካስል ዩናይትዱን አማካይ ብሩኖ ጊማሬስን ለማስፈረም ያቀረበው የመጀመሪያ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። ኒውካስሎች በሴንት ጄምስ ፓርክ የሁለት ዓመት ኮንትራት (እንዲሁም ተጨማሪ የአንድ ዓመት አማራጭ) የቀረውን የ28 ዓመቱን ብራዚላዊ ኮከብ ማቆየት እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል። ተጫዋቹ እሁድ ዕለት ከብራዚል የተነሳ ሲሆን፣ ከክለቡ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በስፔን ላ ማንጋ በሚገኘው የኒውካስል የቅድመ-ውድድር ልምምድ ላይ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ተቀላቅሏል።
ብሩኖ ጊማሬስ በ2022 ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ40 ሚሊዮን ፓውንድ ኒውካስልን ከተቀላቀለ በኋላ፣ ለክለቡ ባደረጋቸው 195 ጨዋታዎች 31 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
ይህ የዝውውር ሂደት የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሃው መልቀቃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። ጊማሬስ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የቀድሞ አሰልጣኙን ምስል በማጋራት "የዚህ ክለብ ንጉስ!! ላደረግህልን ሁሉ እናመሰግናለን፤ የተሻልኩ ተጫዋች እና ሰው ስላደረግከኝ አመሰግናለሁ" በማለት አድናቆቱን ገልጿል። የእግር ኳስ ባለሙያው ጁሊያን ላውረንስ እንዳሉት፣ የኤዲ ሃው መልቀቅ አንዱ ምክንያት ጊማሬስ በመጨረሻ ወደ አርሰናል እንደሚሸጥ ማወቃቸው ነው።
ላውረንስ ይህንን የዝውውር ሂደት በሁለቱ ክለቦች መካከል የተጀመረ "የቼዝ ጨዋታ" ሲሉ ገልጸውታል። አርሰናል ከተጫዋቹ ግምት በላይ ለመክፈል እንደማይፈልግ እና ኒውካስል በበኩሉ ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጥር ባለሙያው አብራርተዋል። ይሁን እንጂ የኒውካስልን የፋይናንስ ሁኔታ እና የተጫዋቹን ከአርሰናል ጋር ምንም አይነት የግል ችግር አለመኖር መሰረት በማድረግ፣ ዝውውሩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊጠናቀቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
ሚኬል አርቴታ ተጫዋቹን የሚፈልግበት ዋነኛ ምክንያት ጫናን ተቋቁሞ ኳስን የማንሸራሸር ብቃቱ ነው። አርሰናል ተጫዋቹን ማስፈረም ከቻለ፣ ዴክላን ራይስ እና ማርቲን ኦዴጋርድን በሁለት ጎኑ በማድረግ በአማካይ ስፍራ (ቁጥር 6) ላይ እንደሚያሰልፈው ይጠበቃል። ጄይ ቦዝሮይድ በስካይ ስፖርት ትንታኔው ላይ እንደጠቆመው፣ የራይስ እና የጊማሬስ ጥምረት በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የአማካይ ክፍል ይሆናል።

Comments