3 months ago
ለደራሲና ዳይሬክተር ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የቤትና የ3 ሚሊዮን ብር ልዩ ስጦታ ተበረከተ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ላለፉት 40 ዓመታት በድርሰት፣ በዝግጅትና በትወና አሻራውን ያኖረው ድንቅ ባለሙያ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ፣ በሕይወት ሳለ ታላቅ የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደለት።
ሰኞ፣ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተከናወነው በዚህ ዝግጅት፣ አድናቂዎቹና የሙያ ጓደኞቹ በታደሙበት ደማቅ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
የተበረከቱ ልዩ ስጦታዎች
ስሙአተ ነገር 3 በተሰኘው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቀረቡት ዋና ዋና ስጦታዎች፦
ቴምር ሪል ስቴት፦ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ለሱቅ የሚሆን ቤት በስጦታ አበርክቷል።
መስፍን አይፎክሩም፦ ለባለሙያው ያለውን ፍቅር ለመግለጽ የወርቅ ሰዓት ሸልሞታል።
ዘላለም ኩራባቸው፦ መጠኑ ያልተገለጸ የገንዘብ ስጦታ ለታላቁ ባለሙያ አበርክቷል።
ጠንክር ቴኒ የ100,000 ብር እንዲሁም ፍሬዓለም ሺባባው የ50,000 ብር መጽሐፍ በመግዛት አጋርነታቸውን ገልጸዋል።
የዳግማዊ አመለወርቅ አዲስ መጽሐፍ ምርቃት
በዕለቱ በዳግማዊ የተጻፈውና በጃፋር መጻሕፍት መደብር የታተመው "ዝሀ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለምረቃ በቅቷል።
መጽሐፉ 307 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ በ850 ብር ለገበያ ቀርቧል።
የዳግማዊ አመለወርቅ የ40 ዓመታት የጥበብ ጉዞ
ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ በ1960 ዓ.ም አዲስ አበባ አብነት አካባቢ የተወለደ ሲሆን፣ በሙያ ዘመኑ፦
ከ500 በላይ ዶክመንተሪዎችንና 1,000 ማስታወቂያዎችን ሠርቷል።
ዓመል የተሰኘ የቴሌቪዥን ድራማ፣ የቃቄ ውርዶዎትና ከመጋረጃ ጀርባ የተሰኙ ቴአትሮችን ጨምሮ ከ40 በላይ የመድረክ ቴአትሮች ላይ በድርሰትና በዝግጅት ተሳትፏል።
ይህ የምስጋና መርሃ ግብር በሄኖክ የእታገኝ ልጅ (ሄኖክ ፊልም ፕሮዳክሽን) አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴምር ሪል ስቴትና ቢን ምዕራፍ በከፍተኛ ሁኔታ ደግፈውታል።
ባለሙያው ዳግማዊ በተደረገለት ዕውቅና ያለውን ጥልቅ ደስታ ገልጾ፣ በሕይወት ሳሉ መመሰጋገን ሊለመድ የሚገባው መልካም ባሕል መሆኑን ገልጿል።

🎭 አንጋፋው የጥበብ ሰው ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ሊመሰገን ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ላለፉት 40 ዓመታት በድርሰት፣ በዝግጅትና በትወና ዘርፍ የማይተካ አሻራውን ያሳረፈው አንጋፋው ባለሙያ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ፣ የሙያ ባልደረቦቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ታላቅ የምስጋና መርሃ-ግብር ሊደረግለት ነው።
የመርሐ-ግብሩ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የምስጋና ምሽቱ ቀጠሮ
ርዕስ፦ "ስሙ አተ"
ቀን፦ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ
ቦታ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
አዘጋጅ፦ ሔኖክ የእታገኝ ልጅ
ስለ ተመጋስኙ ዳግማዊ አመለወርቅ (ዓመል)
ልደት፦
በ1960 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አብነት (ጠጅ ሳር ሰፈር) ተወለደ።
የሙያ ዘመን፦
40 ዓመታትን በጥበብ ዓለም አሳልፏል።
ስራዎቹ፦
ከ500 በላይ ዶክመንተሪዎችንና ከ1,000 በላይ ማስታወቂያዎችንተ፤ጀ። በመስራት ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል።
"ዓመል" የተሰኘ የቴሌቪዥን ድራማ፣ "የቃቄ ውርዶዎት" እና "ከመጋረጃ ጀርባ" የተሰኙ ዝነኛ ቴአትሮችን ጨምሮ ከ40 በላይ በመድረክ ቴአትሮች ላይ ተሳትፏል።
ለ17 ዓመታት ያህል ስክሪፕት በመጻፍና በፊልም ስራዎች ላይም የራሱን አሻራ አኑሯል።
✨ በምሽቱ ምን ይጠበቃል?
በዚህ የክብር ምሽት ላይ ተመጋኙን የሚመጥኑ ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ዳግማዊ ለኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ እውቅና ይሰጠዋል።
ዛሬም ድረስ ለሙያው ያለውን መሰጠት እያሳየ የሚገኘው ዳግማዊ፣ በብዙ ወጣት ባለሙያዎች ዘንድ እንደ አርአያ የሚጠቀስ ስብዕና ባለቤት ነው።
እንኳን ደስ አለህ ዳግማዊ!
ጥበብ ትክበር!
#ዳግማዊአመለወርቅ #ዓመል #ብሔራዊቴአትር #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ስሙአተ #artethiopia #dagmawiamelework #getu #temesgen #getuts emesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments