5 days ago
ደቡብ ኮሪያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ከዓለማችን ግዙፎቹ ሀገራት ከአሜሪካ እና ከቻይና ጋር ተሰልፋ ለመወዳደር እጅግ ግዙፍ እርምጃ መውሰድ ጀመረች።
ሀገሪቱ ለዚህ ዓላማዋ ወደ 900 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ግዙፍ ገንዘብ እየመደበች መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
ይህ የገንዘብ መጠን ለቴክኖሎጂው እድገት ብቻ ሳይሆን የነገውን የዓለም ገበያ ለመቆጣጠር የታለመ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አካል ነው ተብሏል።
ለዚህም ደቡብ ኮሪያ የውጭ ሀገር ባለሙያዎችን ጥገኛ ከመሆን ይልቅ የራሷን የሀገር ውስጥ ብቁ ባለሙያዎች ማፍራት እንዳቀደች ነው የተገለጸው። ይህን ለማሳካት የትምህርት ሥርዓት ለውጥ መሰረት ነው ተብሏል።
ዕድሜያቸው ገና ለጋ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከጅምሩ በሮቦቲክስ (Robotics) እና በኮዲንግ (Coding) ትምህርት እንዲዳብሩ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ልጆች ገና በልጅነታቸው ከቴክኖሎጂ ጋር ተዋውቀው እንዲያድጉ እና የነገ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ጠንካራ መሠረት እየተጣለም ይገኛል ተብሏል።
ይህ የደቡብ ኮሪያ እርምጃ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዓለም ያላትን የበላይነት ከማረጋገጡም በላይ ሌሎች ሀገራት በወደፊቱ የትውልድ ማነጽ ሂደት ላይ ትምህርት የሚወስዱበት አርአያ ሊሆን ይችላል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
10 days ago
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዜጎችን ሕይወት የሚያሻሽል ዘላቂ መሠረት ተጥሏል - በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዜጎችን ሕይወት የሚያሻሽሉ ዘላቂ መሠረቶች እየተጣሉ ይገኛሉ አሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)።
የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የ50 ዓመታት ጉዞንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚዳስስ ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንዳሉት ፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የዜጎችን ሕይወት የሚያሻሽሉና ሀገራዊ የዲጂታል ሽግግርን የሚያፋጥኑ ዓበይት እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡
በዚህም የሀገሪቱ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ17 ሚሊየን ወደ 65 ሚሊየን ማደጉን በማንሳት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መዘርጋቱ፣ ከ50 ሚሊየን በላይ ዜጎች የተመዘገቡበት የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ትግበራ፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ እና የስታርታፕ አዋጅ ሥራ ላይ መዋላቸው የዲጂታል እምነትን አጠናክረዋል ብለዋል።
ቴክኖሎጂን በጤና፣ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ መርሐ ግብር የፓናል ውይይቶች፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ፣ ሮቦቲክስ እና ስማርት ሲስተሞችን ጨምሮ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ለዕይታ ይቀርባሉ።

14 days ago
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።
👉 የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዘመኑንና የወደፊቱን የገበያ ፍላጎት ያማከሉ ናቸው ያላቸውን አዳዲስ የሥልጠና መስኮችን በማካተት የተማሪዎች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ።
ኢንስቲትዩት እነዚህን ተጨማሪ የስልጠና መስኮች ያስተዋወቀው ከመስከረም 14/2019 ዓም ጀምሮ ክፍት የሚሆን የመረጃ ሳምንትን ይፋ ባደረገበት መርሃ ግብር ላይ ነው።
ተቋሙ ላለፉት ከ15 ዓመታት በላይ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብቸኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት
• በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች፣
• በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች እንዲሁም
• በሦስተኛ ዲግሪ (ደረጃ 8 / ፒኤች.ዲ) በ2 ፕሮግራሞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በተለይም በ2018 ዓ.ም ደግሞ የዓለም ገበያ የክህሎት ፍላጎትን ያገናዘቡ ናቸው የተባሉትን 11 መስኮች ማለትም :-
- ባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ፣
- የሳይበር ደህንነት፣
- አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣
- ኢንተለጀንት ሮቦቲክስ፣
- ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ
- ሆርቲካልቸር
- ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ፊኒሺንግ
- ሌዘር ፕሮዳክት
- በTVET ሊደርሺፕ እና ማኔጅመንት
- በማኑፋክቸሪንግ
- ፋሽን ዲዛይን እና በአዳዲስ ኢነርጂ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራና የወደፊት የሥልጠና መስኮች (Emerging Skills) ተቀርጸው ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል።
ሥልጠናው 50 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ ነው የተባለ ሲሆን ተቋሙ በ16 ሳተላይት ካምፓሶችና በ2 ማዕከላት አማካኝነት ከ 10 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።
ኢንስቲትዩቱ ከቻይና እና አልጄሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረት የዲግሪ ፕሮግራሞችን ከመስጠት ባሻገር፣ በየዓመቱ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎች የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የሥልጠና ዕድል እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።
የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

1 month ago
በቻይና ጎዳናዎች ላይ ስራ የጀመረው የሮቦት ትራፊክ ፖሊስ የወደፊቱ የትራፊክ ቁጥጥር አዲሱ ምዕራፍ
በምስራቅ ቻይና ዢጂያንግ ግዛት በምትገኘው ዮንግካንግ ከተማ፣ የትራፊክ ፍሰትን የመቆጣጠር እና የማስተካከል ስራ የሚያግዝ የሮቦት ትራፊክ ፖሊስ የመጀመሪያ የሙከራ ስራውን በይፋ ጀምሯል።
ይህ የቴክኖሎጂ ድንቅ ውጤት የሆነው ሮቦት ለ30 ደቂቃ ብቻ በመብራት ከተሞላ በኋላ ለአራት ሰዓታት ያህል ያለምንም እረፍት በተከታታይ መስራት የሚችል ነው።
የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው የመንገድ መገናኛዎች ላይ የሚከናወኑ መደበኛና ተደጋጋሚ ተግባራትን በብቃት ለማከናወን ተቀርጾ የተሰራ ነው።
ሮቦቱ በተለይም አሽከርካሪዎችንና እግረኞችን በስርዓት የመምራት፣ የመንገድ ላይ ደህንነት ማሳሰቢያዎችን የመስጠትና በትራፊክ መጨናነቅ ወቅት የትራፊክ ፖሊሶችን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የማቃለል ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ውጤት የከተሞችን የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ አስተዳደር ወደ አዲስ የዘመናዊነት ደረጃ የሚያሸጋግር ድንቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
Seledadotio

የኢትዮጵያ ታዳጊዎች በዓለም አቀፉ የሮቦቲክስ ውድድር ሀገራቸውን ለመወከል በዝግጅት ላይ ናቸው
#ethiopia | በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ-ሮቦቲክስ ትምህርትና ውድድር ማዕከል ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየውን የክረምት ወራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ይህ መድረክ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2027 በአሜሪካ ሴንት ሉዊስ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የSTEM ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ታዳጊዎችን ለመምረጥ የተዘጋጀ ነው።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ መንግስት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ባመቻቻቸው ምቹ ሁኔታዎች ምክንያት ወጣቶች የስራው ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።
ወጣቶች የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩና የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮ-ሮቦቲክስ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሰናክሬም መኮንን በበኩላቸው ሰልጣኞች የህብረተሰብ ችግሮችን መፍታት የሚችሉ ባለሙያዎች እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቅርብ მომደመይም ፕሮግራመሮችን፣ ኮደሮችን፣ ዲዛይነሮችንና መሀንዲሶችን ለማፍራት የሚያስችሉ ተግባራዊ የስልጠና መርሃ ግብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
#ኢትዮጵያ #ቴክኖሎጂ #ሮቦቲክስ #ኢኖቬሽን #ታዳጊዎች #ፈጠራ #ትምህርት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የ16 ዓመቱ ወጣት ግዙፉን አፕል ኩባንያ ተቀላቀለ
#ethiopia | የ 16 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ወጣት ቤሉሶቺም በ 'አፕል' ኩባንያ ውስጥ በ AI እና ሮቦቲክስ ዘርፍ መሥራት ጀመረ።
በቴክኖሎጂው ዓለም አዲስ ተስፋ የሆነው የቤት 16 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ቤሉሶቺም በአፕል ኩባንያ ውስጥ በማሽን እና በሮቦቲክስ ዘርፍ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
ወጣቱ በሂሳብ እና በፊዚክስ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ አሸናፊ ለመሆን በመብቃቱ ይህንን ዕድል ሊያገኘ የቻለው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምርምሮች ላይ ከመሳተፉም በላይ የሚንቀሳቀሱ አውቶማቲክ የሮቦቲክስ ተሽከርካሪ ወንበሮችን መስራት መቻሉም ተገልጿል።
ወጣቱ ግዙፉን አፕል ኩባኒያ መቀላቀሉ በቴክኖሎጂው ዓለም ወደፊት ተጽዕኖ ፈጣሪ ተተኪ የአፍሪካ ወጣቾች እንዲመጡ የሚያደርግ ትልቅ ዕድል ነው ተብሏል።
ቤሉሶቺም በዓለም አቀፍ ደረጃ የአፍሪካ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ወክሎ ስሙን እያስጠራ ይገኛል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #nigeria #apple #ai #technology #entrepreneur

በሸገር ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሄደ
#ethiopia | በሸገር ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በሲያትል አካዳሚ መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለአራት ወራት የተሰጠው የቴክኖሎጂ ስልጠና መጠናቀቁን ተክተሎ በኤቨረስት አካዳሚ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሂዷል።
ተማሪዎቹ በስልጠናው ወቅት በኮዲንግ፣ በሮቦቲክስ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮምፒዩቲንግ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዲዛይን እና በፕሮግራሚንግ ዘርፎች የቀሰሙትን የላቀ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ችሎታቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ይህም ስራቸው ለሀገራችን የቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ እና ወደፊት በዘርፉ አዎንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉበትን አቅም ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩ የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለተማሪዎቹ የፈጠራ ስራዎች ልዩ አድናቆት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ተስፋ ሰጪ ለሆኑት እነዚህ ወጣቶች ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ስልጠናውን በማዘጋጀትና በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው የሲያትል አካዳሚ፣ የስልጠናውና የፕሮጀክቱ ሀሳብ አመንጪ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ባለቤትና ማናጀር ለሆኑት ለአቶ መንግስቱ ወዳጄ ልዩ ምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ የከተማው አስተዳደር እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የአድናቆት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የዘርፉ ባለሙያዎችም ተገኝተው ልምዳቸውን አክፍለዋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሀገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ መሰል ድጋፎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም በውድድሩ የላቀ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራቸውን ላቀረቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የእውቅና መስጠት ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ታናናሽ ህፃናትም የወደፊት ራዕያቸውን እንዲቀርጹና ፍላጎት እንዲያዳብሩ የመድረኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል።
#shegercity #seattleacademy #coding #robotics #artificialintelligence #ethiopianews #technologyinethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ደረጃ አገኙ
#ethiopia | በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር የተሳተፉት የኢትዮ ሮቦቲክስ ታዳጊዎች 3ኛ ደረጃን በማግኘት ለኢትዮጵያ አስደማሚ ድል አስመዝግበዋል።
ይህ ውጤት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂና የሮቦቲክስ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ያደረገ ሲሆን፣ የታዳጊዎቹን ተሰጥኦ፣ ጥረትና የቴክኖሎጂ ችሎታ ያሳየ ስኬት ሆኗል።
ከውድድሩ አስቀድሞ በ**“ታዲያስ አዲስ”** ፕሮግራም የአውሮፕላን ትኬትና የሆቴል ወጪ ድጋፍ የተደረገለት ተማሪ በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር በመሳተፍ ለውጤቱ አስተዋፅዖ ማድረጉም ተገልጿል።
የዚህ ድል ሌላው ዋና ተዋናይ ኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ውድድር ማዕከል ሲሆን፣ ተቋሙ ባለፉት 15 ዓመታት ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በኮዲንግ፣ ዲዛይንና ኢንጂነሪንግ በማሰልጠን ለቴክኖሎጂው ዓለም ሲያዘጋጅ ቆይቷል።
በአዲስ አበባ አራት የሥልጠና ማዕከላትን ከፍቶ እየሰራ ያለው ተቋሙ፣ በቀጣይ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ለማደግ በሂደት ላይ መሆኑም ታውቋል።
የዛሬው ድል የነገው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ በዓለም መድረክ ላይ ምን ያህል ሊያበራ እንደሚችል ያሳየ ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው።

🥹በዱባይ ታዋቂው ሮቦት «ቡ ሱናይዳህ» ከ«ሞዛ» ጋር የጋብቻ ስነ-ስርዓት ፈጸመ🤝❤
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ከባህል ጋር አዋህዶ በማቅረብ የመነጋገሪያ ነጥብ መሆን የተለመደ ነው።
አሁንም በዱባይ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው «ቡ ሱናይዳህ» የተሰኘው ሰውን መሰል ሮቦት፣ «ሞዛ» ከተሰኘችው አጋር ሮቦት ጋር በባህላዊ ስነ-ስርዓት ጋብቻ መፈጸማቸውን የሚያሳይ አዝናኝ ይዘት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቀቅ በማድረግ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
* በሰርጉ ሥነ ሥርዓት ላይ ብዙ እንግዶች ተገኝተዋል። ምግብና መጠጥ ቀርቧል፤ ርችትም ወደ ሰማይ ተተኩሷል።"
* የተለቀቀው ቪዲዮ በአጭር ሰዓታት ውስጥ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ እይታዎች፣ አስተያየቶች እና የደገፋ መግለጫዎች (Likes & Shares) አግኝቷል።
* የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ውጤት የሆኑትን እነዚህን ሮቦቶች ባህላዊ የሰርግ አልባሳት አጊጠው በሙሽሮች ወንበር ላይ ማቀመጡ ለተመልካች ልዩና ማራኪ እይታን ፈጥሯል።
* ክስተቱ አዝናኝ ከመሆኑ ባሻገር፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወትና በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ሚና በተመለከተ አዲስ መነጋገሪያ አርዕስት ፈጥሯል።
ዱባይ የላቀ ቴክኖሎጂን ከራስ ባህልና ከህዝብ መዝናኛ ጋር አዋህዶ በማቅረብ ረገድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት ላይ ትገኛለች

3 months ago
የኢትዮጵያውያን ደግነት ህልሜን እውን አደረገው! — ተማሪ ልዑል ብሬነህ
#ethiopia | በዘንድሮው አገራዊ የኢትዮ ሮቦቲክስ ውድድር አሸናፊ ሆኜ፣ በካናዳ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ለመወከል ዕድል ባገኝም፣ ለጉዞው የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈን ለቤተሰቤ ትልቅ ፈተና ሆኖ ነበር።
ነገር ግን በ"ታዲያስ አዲስ" የሬዲዮ ፕሮግራም እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች አማካኝነት ያቀረብኩትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ፣ በጎ ፈቃደኛና ሩኅሩኅ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለጉዞዬ የሚያስፈልገኝን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንዲሟላ አድርጋችሁኛል።
ህልሜ እውን እንዲሆን ከጎኔ ለቆማችሁ ለሁሉም ለጋስ ኢትዮጵያውያን በራሴና በቤተሰቤ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በተለይም ድምፄ ለብዙኃን እንዲደርስ መድረኩን ያለምንም ክፍያ ለከፈተልኝ "ታዲያስ አዲስ" የሬዲዮ ፕሮግራም፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስልጠና በመስጠት እና የካናዳ ጉዞዬን ሙሉ በሙሉ ላመቻቸለልኝ ኢትዮ ሮቦቲክስ ማዕከል፣ እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ላደረጉልኝ ወ/ሮ ኑርያ ከማል እና አቶ ፋሲል ሰለሞን ልዩ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ።
በተጨማሪም መልዕክቴን ያለምንም ክፍያ በገጾቻችሁ በማጋራት ድጋፍ ላደረጋችሁ የማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች፣ እንዲሁም ከአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በገንዘብ፣ በሃሳብ እና በማበረታቻ ከጎኔ ለቆማችሁ ሁሉ ፈጣሪ የደግነታችሁን ዋጋ ይክፈላችሁ።
ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በክብር ለመወከል ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።
ከልብ አመሰግናለሁ!
– ተማሪ ልዑል ብሬነህ

የሰውን ስሜት ተረድቶ ምላሽ የሚሰጠው አዲሱ የቴክኖሎጂ እመርታ
የሰውን ልጅ የድምፅ ቃና፣ የፊት ገጽታና የሰውነት ሁኔታ በመገምገም ስሜትን መረዳትና ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሚችል አዲስ የሮቦቲክስና የሰው ሰራሽ አስተዋፅዖ (AI) ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ።
ይህ በቴክኖሎጂው ዓለም ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው እመርታ፣ ሮቦቶች ከተራ የቤት ውስጥ ረዳትነት ባለፈ የሰዎችን ስሜታዊ ፍላጎት መለየትና እንደየሁኔታው ማጽናናት፣ ማበረታታት እንዲሁም የቅርብ ክትትል ማድረግ የሚያስችላቸውን አቅም ፈጥሯል።
ይህ ቴክኖሎጂ በተለይ ብቻቸውን የሚኖሩ አረጋውያንን፣ የድብርትና የጭንቀት ሰለባ የሆኑ ሰዎችን እንዲሁም የቅርብ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
በቴክኖሎጂ፣ በሳይንስና በፈጠራ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገው የሚዘግቡት ተጽዕኖ ፈጣሪ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሔቶችና የቴክኖሎጂ ሚዲያዎች የዜና ዘገባየው አካል አድርገውታል።
ዘገባው በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማሩ ግንባር ቀደም ተቋማት ያበለጸጓቸውን ስሜት ተገንዛቢ (Emotion-AI) የቤት ውስጥ ረዳት ሮቦቶችና የገበያ ተደራሽነታቸውን አስመልክቶ ካቀረበው ትንታኔ የተወሰደ ነው።

በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተሰናዱ ሁለት የሳይንስና የወደፊት ራዕይ መጻሕፍት ተመረቁ!
#fastmereja :- በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ልጅ ቀጣይ ስልጣኔ ላይ የሚያተኩሩ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት በዛሬዉ እለት በልዩ ስነ-ስርዓት ተመረቁ።
የቴክኖሎጂ ባለሙያውና ተመራማሪው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ያዘጋጇቸዉ «Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization>> እና «Introduction to Astronautics: A Beginner's Guide» የተሰኙት መጻሕፍት፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካዳሚክ ማህበረሰብ፣ ዲፕሎማቶችና የቴክኖሎጂ ዘርፍ አጋሮች በተገኙበት ነው ለንባብ የበቁት።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ደራሲው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ፣ መጻሕፍቱ የተዘጋጁት መረጃ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን አገር በቀል እውቀትን በማሳደግ የወደፊቱን ትውልድ ለታላቅ ስኬት ለማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።
"ሀገራት የሚለወጡትና ከፍ የሚሉት በእውቀት፣ በፈጠራ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ራዕይ ብቻ ነው" ያሉት ደራሲው፣ ሁለቱ መጽሐፍት በይዘታቸው የተለያዩ ቢመስሉም የሚያስተላልፉት መልዕክት ግን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ የሚቀመር መሆኑን አስገንዝበዋል።
የመጀመሪያው መጽሐፍ-«Architecting the Future» -አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ሮቦቲክስ፣ ኳንተም ኮምፒውቲንግ፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ የሰው ልጅን ህይወት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየሩት ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የወደፊቱን ዓለም በሥነ-ምግባር፣ በሰብዓዊ እሴቶችና በፍትሐዊነት እንዴት መምራት እንደሚቻል ስልታዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። መጽሐፉ ለመንግሥታት የፖሊሲ አቅጣጫን፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የምርምር ራዕይን ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል «Introduction to Astronautics>> የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍ የጠፈር ቴክኖሎጂን በቀላል ቋንቋ የሚያስተምር ሲሆን፤ የሮኬት ሳይንስ፣ ሳተላይቶች፣ የጠፈር ህግና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የጠፈር ኢኮኖሚ በተግባራዊ መልኩ የቀረቡበት ነው። በተለይም ኢትዮጵያና አጠቃላይ አፍሪካ በአዲሱ የጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ተገብሮ ተመልካች ሳይሆኑ፣ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፉ በግልጽ እኖደሚያሳይ ተገልጿል።
ዶ/ር ይሹሩን የሁለቱን መጻሕፍት ትስስር ሲያስረዱም፦

የ2018 “ስቴም ፎር ኪድስ” የልጆች ስቴም ውድድር ተካሄደ
#fastmereja | በአሜሪካ የተመሰረተውና በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው "ስቴም ፎር ኪድስ"፣ የህፃናትን የፈጠራ ችሎታ የሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን እየሰጠ ይገኛል። የዚህ የትምህርት ፕሮግራም ዋና ዓላማ ለህፃናት የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን በአዲስና በሚስብ መንገድ ማስተማር ሲሆን፣ በተለይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) ዘርፎች ላይ ያተኩራል።
የትምህርት ፕሮግራሙ በቴክኖሎጂ ላይ ከሚሰሩ ባለሙያዎች እና ከአካዳሚክ ሊቃውንት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ካሪኩለም እንደሚጠቀም ተገልጿል። የትምህርት አሰጣጡም በአካል በመገኘት፣ ከትምህርት ሰዓት ውጪ (After school)፣ በክረምት ካምፕ እና በኦንላይን መንገዶች እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
ይህ የትምህርት አቀራረብ የህፃናትን የፈጠራ ችሎታ፣ በጥልቀት የመረዳት ችሎታ (Critical Thinking) እና በጋራ የመስራት ባህልን ለማሳደግ እንደሚረዳ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ገልጸዋል።
ከ4 እስከ 18 ዓመት የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ህፃናትና ወጣቶች፣ የዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ካሪኩለም በመጠቀም ስልጠናው ይሰጣል።
እስካሁን በስልጠናው ከ5,000 በላይ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፤ በአሁኑ ዓመት ብቻ 1,500 ተማሪዎች በአዲስ አበባ በሚገኙ ማዕከላት እየሰለጠኑ ነው።
ፕሮግራሙ በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የግል ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ቢሆንም፣ ወደፊት ግን ይህን አገልግሎት ለመንግስት ትምህርት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማዳረስ እየተሰራ ነው።
በ2018 ዓ.ም. በየትምህርት ቤቱ እና ስልጠና ማዕከሎች የኮዲንግ፣ ሮቦቲክስ እና ኢንጂነሪንግ ስልጠና የወሰዱ ልጆች የዓመቱ መዝጊያ የስቴም ውድድር (STEM Competetion) ተካሂዷል።

የነገዋ ታዳጊ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለእይታ አቀረቡ
#ethiopia | ነገን በቴክኖሎጂ ለመቀየርና የሀገራቸውን ችግሮች በፈጠራ የሳይንስ ጥበብ ለመፍታት ቆርጠው የተነሱ ህጻናትና ታዳጊዎች፣ ማህበረሰባዊ ፋይዳ ያላቸውንና አስደናቂ የሆኑ የሮቦቲክስ ፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ አብቅተዋል።
እነዚህ ታዳጊዎች በዕድሜ ለጋ ቢሆኑም፣ ያቀረቧቸው የፈጠራ ውጤቶች ግን የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ሆነዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል የ15 ዓመቷ ታዳጊ ሮዳ ፈታ አንዷ ስትሆን፣ አካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ያለምንም ሰው እገዛ በራሱ ጊዜ መመገብ የሚችል ማሽን ሰርታ ለእይታ አቅርባለች። «ኢትስ ኤ ፊደር» (It's a feeder) የሚል ስያሜ የሰጠችው ይሄው ማሽን፣ የብርሃንና የከለር ሴንሰሮችን በመጠቀም በአንድ ጊዜ እስከ አራት ሰዎችን ማብላት የሚያስችል አቅም አለው ብላለች።
ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ዘመዷን ለመጠየቅ በምትሄድበት ወቅት የተቸገሩ ሰዎችን አይታ ይሄንን የፈጠራ ስራ ለመስራት መነሳሳቷን የገለጸችው ታዳጊ ሮዳ፣ ማሽኑ ተንቀሳቃሽ እንዲሆን ከስሩ ጎማዎች የተገጠሙለት መሆኑንና ወደፊትም በትምህርቷ ገፍታ በትውልድ ሀገሯ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ስራዎችን የመስራት ትልቅ ህልም እንዳላት በልበ ሙሉነት ተናግራለች።
በተመሳሳይ መልኩ ናስናፍ ይስሐቅ እና ኢቫን ዘረይ የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች የሀገራቸውን የቡና ምርት ሂደት ለማቃለል የሚያስችል «ኮፊ ቢን ኮሌክተር» የተሰኘ ዘመናዊ የቡና ፍሬ መልቀሚያ ማሽን ይዘው ቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ቡና በእጅ መለቀሙ እንደሆነ በመረዳት ችግሩን ለመፍታት መነሳሳታቸውን የገለጹት ታዳጊዎቹ፣ የሰሩት ማሽን በአራት ሞተሮችና በተለያዩ ፕሬዠር ሴንሰሮች የታገዘ ሲሆን፣ ከሰው ጉልበት በተሻለ በ10 እጥፍ ፍጥነት ቡናን ሰብስቦ በተዘጋጀለት ቅርጫት ውስጥ ማስገባት እንደሚችል በተግባር አስረድተዋል።
የስቴም ፎር ኪድስ ፍራንቻይዝ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ሰለሞን በበኩላቸው፣ የትምህርት ፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ህጻናት እየተጫወቱና እየተደሰቱ ክሬቲቪቲን፣ ኮሙኒኬሽንንና ክሪቲካል ቲንኪንግን እንዲያሳድጉ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ መደበኛ የሆኑ ስራዎች በሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና በማሽን ለርኒንግ እየተተኩ በመሆኑ፣ ልጆችን ከወዲሁ ለዚህ አዲስ ዓለም ማዘጋጀት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ተኩል ጊዜ ውስጥ ወደ 5,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን ማስተማር መቻላቸውን የገለጹት አቶ ኤርሚያስ፣ ወደፊትም ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሳፋሪኮም ጋር በመተባበር ትምህርቱን በኦንላይን በማስፋፋት አቅም ለሌላቸውና በየክፍለ ሀገሩ ለሚገኙ በርካታ የመንግስት ትምህርት ቤት ልጆች ጭምር በስፋት ለማድረስ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው፣ ቴክኖሎጂውን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ያለውን የእቃ አቅርቦትና የፖሊሲ ፈተናዎች መንግስት ተረድቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በጌትነት ተመስገን
📷ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#stemethiopia #stemforkids # #technologyethiopia #ethiopiangenius #digitaltransformationethiopia

4 months ago
ሰላም! እንደምን አደራችሁ?
ኢትዮጵያን ወደ አቪዬሽን ማዕከልነት…
የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለምን ለማስተሳሰር የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያን ከአህጉራዊ የትራንዚት ማዕከልነት ወደ መላው ዓለም ስልታዊ መገናኛ ድልድይነት ያሸጋግራታል፡፡
ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቁልፍ የአቪዬሽን መናኸሪያ ከማድረግ ባለፈ፣ ለቀጣዩ ትውልድ ጭምር ኩራት የሚሆኑ የኢትዮጵያን ዘላቂ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያረጋግጡ በረከቶችን ይዞ እየመጣ ነው፡፡
ለግዙፉ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጦለት፣ በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያው ምዕራፍ የመሬት ማስተካከል ሥራዎች ቀንና ሌሊት በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑለት ይገኛል።
ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 12 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን÷ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ትልቁ የአቪዬሽን ማዕከል ይሆናል።
በአሁኑ ወቅት ለቦታው መሬት ማስተካከል እና የዝግጅት ሥራዎች 610 ሚሊየን ዶላር ተመድቦ ሥራው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
የመጀመሪያው ዙር የመሬት ዝግጅት ሥራ እንደተጠናቀቀ፣ ዋና ዋናዎቹ የግንባታ ተቋራጮች ወደ ስፍራው ገብተው ግንባታቸውን ይጀምራሉ። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በፈረንጆቹ እስከ 2030 ድረስ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ግብ ተቀምጧል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ በዓመት 60 ሚሊዮን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ ግዙፍ አቅም ይኖረዋል። ይህም አሁን ካለው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅም በ4 ነጥብ 4 እጥፍ ይበልጣል። አየውሮፕላን ማረፊያው አራት ዘመናዊ ማኮብኮቢያዎች እና በአንድ ጊዜ እስከ 270 አውሮፕላኖችን ማቆም የሚችል ስፍራም ይኖረዋል።
አቡሴራ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከባሕር ጠለል በላይ በ1 ሺህ 910 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ቦሌ (2 ሺህ 334 ሜትር) በተሻለ ለአውሮፕላኖች መነሳትና ማረፍ እጅግ ምቹ የአየር ሁኔታን ይሰጣል።
የፕሮጀክቱ ዲዛይን በታዋቂው የለንደን ዘሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የተሰራ ሲሆን÷ በውስጡ ዘመናዊ ሆቴሎችን፣ የገበያ ማዕከላትን፣ የንግድና የዕቃ መጋዘን (Cargo) ኮምፕሌክሶችን ያካትታል። አዲሱ አየር ማረፊያ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በፈጣን የኤክስፕረስ መንገድ እና በከፍተኛ ፍጥነት ተንቀሳቃሽ የባቡር መስመር እንደሚገናኝ ይጠበቃል፡፡
ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እድገት ለማሳለጥ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ሀገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ዘላቂ ሞተር ይሆናል። ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ አበርክቶው ከፍተኛ ነው፡፡
በግንባታው ወቅት በሺህ የሚቆጠሩ መሃንዲሶችንና ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ ያለ ሲሆን÷ ሥራ ሲጀምር ደግሞ በአየር መንገዱ፣ በሆቴሎችና በሎጂስቲክስ ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን በማስተናገድ ከትራንዚት፣ ከቀረጥ ነፃ ንግድ እና ከአየር መንገድ አገልግሎቶች የሚገኘውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል። የአካባቢው የዶሮ፣ የወተት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ለግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያና ለሆቴሎቹ ምርቶቻቸውን በስፋት የሚያቀርቡበት ሰፊ የገበያ እድልም ይፈጥርላቸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ምርት እድገት፣ በውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና በውጪ ምንዛሪም ማሳደግን ያስችላል፡፡ ማረፊያው በሚሊየን የሚቆጠሩ መንገደኞችን እና በሚሊየን የሚቆጠር ቶን ጭነት ማስተናገዱ በራሱ ለሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ቀጥተኛ እና ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል።
ምቹ፣ ፈጣን እና ዘመናዊ የአየር ትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማት መኖሩ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎችና ፋብሪካዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ማበረታቻ ይሆናል።
ከአገልግሎቶች፣ ከነዳጅ ሽያጭ፣ ከትራንዚት ሆቴሎች እና ከቀረጥ ነፃ የንግድ ማዕከላት የሚገኘው ገቢ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በዘላቂነት ይቀርፋል።
የወጪ ንግድ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እድገት በማሳለጥ ረገድም የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡ እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልትና ስጋ ያሉ በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ የኢትዮጵያ እና የሌሎች ሀገራት ወጪ ምርቶች ሳይዘገዩ በጥራት ለዓለም ገበያ እንዲቀርቡ በማድረግ የገበሬውንና የላኪውን ገቢ ያሳድጋል።
በአውሮፕላን ማረፊያው አቅራቢያ እና በሀገሪቱ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያመርቷቸውን የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ እና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና እስያ ገበያዎች ለማጓጓዝ ምቹ የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ይፈጥራል።የአህጉሪቱ የንግድና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ ዋና ማስተላለፊያ ማዕከል በመሆን የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ተሰሚነት ያጠናክራል።
የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ደግሞ ሌላኛው ትሩፋቱ ይሆናል፡፡ አውሮፕላን ማረፊያው ከማረፊያነት ባለፈ ዘመናዊ ሆቴሎችን፣ የገበያ ማዕከላትን፣ የኤግዚቢሽን ማዕከላትንና የንግድ ህንጻዎችን የያዘ "የኤርፖርት ከተማ" ወይም አዲስ የኢኮኖሚ ከተማ ሆኖ ይገነባል።
አካባቢው ለቱሪዝም ምቹ በመሆኑም ዓለም አቀፍ ቱሪዝምን ይስባል፡፡ በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ የትራንዚት መንገደኞች ቢያንስ ለጥቂት ቀናት በሀገሪቱ እንዲቆዩ እና የኢትዮጵያን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች እንዲጎበኙ በር ይከፍታል።
የቱሪስቶች ቁጥር መጨመር በሀገር ውስጥ ያሉ ሆቴሎች፣ ሪዞርቶች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች እና የባህል ምርቶች አቅራቢዎች ገቢያቸው እንዲያድግ እና ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ያደርጋል።
የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሰው ኃይል ልማት ላይ የሚኖረው አንድምታም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አውሮፕላን ማረፊያው የሚገነባው እጅግ ዘመናዊ በሆኑ የኤክስሬይ፣ የደህንነት፣ የሮቦቲክስ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች በመሆኑ የሀገር ውስጥ መሃንዲሶች እና ባለሙያዎች ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል።ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የሚስፋፉት የአቪዬሽን ማሰልጠኛዎች እና የምርምር ማዕከላት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የእውቀት ማዕከል ያደርጓታል።
በሌላ መልኩ ደግሞ ኢትዮጵያን ክልላዊ የልማት መናኸሪያ ያደርጋታል፡፡ ፕሮጀክቱ ቢሾፍቱን፣ ሞጆን፣ ዱከምንና አዲስ አበባን የሚያስተሳስር አዲስ የኢኮኖሚ ኮሪደር ይፈጥራል። ይህ ከተሞች፣ የንፁህ ውሃ አቅርቦት፣ የኃይል እና የመገናኛ መሠረተ ልማቶችን በጥራት እንዲያድጉ ያደርጋል።
ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፋዊ ትስስርን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ የመጀመሪያው ሚና የዓለም አቀፍ አየር መንገዶች መዳረሻነት ነው፡፡ በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረው በመሆኑ፣ ከእስያ፣ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እና ከላቲን አሜሪካ የሚነሱ ተያያዥ በረራዎችን በአንድ ማዕከል ያስተናግዳል ፤ ይህም ግዙፍ የመንገደኞች ፍሰትን ይፈጥራል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል የሆነበት ስታር አሊያንስ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች አቡሴራን ዋና የምስራቅ አፍሪካ መሸጋገሪያ መናኸሪያቸው ያደርጉታል። የአሊያንስ ማዕከልነታችንንም የምናረጋግጥበት ይሆናል፡፡
ሁለተኛው ሚና የግሎባል ደቡብ ዋነኛ ትስስር ድልድይን መፍጠር ነው፡፡ አዲሱ ማረፊያ አፍሪካን ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ (በተለይም ከቻይና እና ህንድ) እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር በቀጥታና በአጭር ሰዓት የሚያገናኝ ዋነኛ መስመር ይሆናል። ይህ ሲሆን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ከዓለም ጋር አስተሳሰርን ማለት ነው፡፡
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተፈፃሚነት ለማፋጠን ሰዎችንና የንግድ ዕቃዎችን ከአህጉሪቱ ጥግ እስከ ዓለም ጫፍ በፈጣን የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ያገናኛል። ለአህጉር አቀፍ ንግድ መነቃቃት አበርክቶው ከፍተኛ ይሆናል፡፡
ሦስተኛው የዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ማዕከልነታችንን ማረጋገጥ ነው፡፡ የሚገነባው ግዙፍና ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል የዓለም የንግድ ዕቃዎች እና የህክምና አቅርቦቶች ከአምራች ሀገራት ተነስተው ወደ ተጠቃሚዎች የሚሰራጩበት ዋነኛ የአየር ሎጂስቲክስ ማዕከል እንዲሆን ያደርገዋል። እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ እና ስጋ ያሉ የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት ምርቶች ሳይበላሹ በጥራትና በከፍተኛ ፍጥነት ወደ መላው ዓለም ገበያ እንዲደርሱ ያስችላል።
ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ እና የአቪዬሽን ብቃት ደግሞ ሌላኛው ሚናው ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ካርታ ላይ ያላት ስልታዊ አቀማመጥ (በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ መገናኛ መስመር ላይ መገኘቷ) አቡሴራን ለዓለም አቀፍ በረራዎች አጭርና ተመራጭ የመሸጋገሪያ መስመር ያደርገዋል።
የአቡሴራ ከፍታ ከአዲስ አበባ ቦሌ ያነሰ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ በረራ አውሮፕላኖች ሙሉ ነዳጅና ጭነት ይዘው ረጅም ርቀት በቀጥታ እንዲበሩ ሰፊ የአቪዬሽን ምቹነትን ይሰጣል። የአውሮፕላኖች የመጫን አቅምን ጨመረ ማለት ነው።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ እንደ ዱባይ (DXB) እና ሲንጋፖር (Changi) ያሉ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ማዕከላት ተርታ ያሰልፋታል።
በአጠቃላይ ሲታይ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ስልታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት ከማጠናከሩ ባሻገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ ፍጥነት የሚያሳልጥ ታላቅ ብሔራዊ ትሩፋት ነው።

5 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጩ የቪዲዮ ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ አንድ የቴክሳስ ሮቦቲክስ ኩባንያ "ስቱዊ" (Stewie) የተሰኘውን የሰው ቅርጽ ያለው ሮቦት ከዳላስ ወደ ላስ ቬጋስ ባደረገው መደበኛ በረራ ላይ አሳፍሮት ተጉዟል። ሮቦቱ በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲራመድ እና አውሮፕላን ላይ ሲሳፈር፣ ሌሎች መንገደኞች እና የበረራ አስተናጋጆች በከፍተኛ አግራሞት እና ድንጋጤ ሲመለከቱት ታይተዋል።
ይህንን አስገራሚ ክስተት ተከትሎ በማግስቱ፣ ሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሻንጣ አያያዝ እና የጉዞ ፖሊሲውን በአስቸኳይ በማሻሻል ጥብቅ እገዳ ጥሏል። አየር መንገዱ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት፣ የሰውም ሆነ የእንስሳት ቅርጽ ያላቸው ሮቦቶች መጠናቸውም ሆነ የሚሰጡት አገልግሎት ምንም ይሁን ምን በበረራዎቹ ላይ እንዳይሳፈሩ ሙሉ በሙሉ አግዷል። ይህ ክልከላ ከመንገደኛ ጋር ወደ ውስጥ የሚገቡትንም ሆነ ከሻንጣ ጋር በርቀት የሚጫኑትን ሮቦቶች በሙሉ የሚያጠቃልል ነው።
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጠው አምራቹ የቴክሳስ ሮቦቲክስ ኩባንያ በበኩሉ፣ ሮቦቱ "ስቱዊ" የራሱ የሆነ ሙሉ የመሳፈሪያ ትኬት ተቆርጦለት እንደተጓዘ ገልጿል። በተጨማሪም የሮቦቱ ባትሪ የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደርን (FAA) የደህንነት መስፈርት ያሟላ መሆኑን እና ኩባንያው ጉዞውን ሲያደርግ በወቅቱ የነበሩትን የአየር መንገዱን ህጎች በሙሉ ያከበረ ህጋዊ አሰራርን የተከተለ መሆኑን አስረድቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሮቦት ተሳፋሪ ቢያጋጥመው ምን ይወስን ይሆን? በሮቦት ላይ ያለው ፖሊሲስ ምንድን ነው?

ኢትዮጵያዊያን አዳጊዎች በዓለም አቀፉ የአዳጊዎች ሮቦቲክስ ውድድር በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ አሸነፉ
**********************
የኢትዮጵያ አዳጊዎች ልዑክ በዓለም አቀፉ የአዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና በመሳተፍ በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ 1ኛ በመሆን አሸንፏል።
በሚቺጋን አሜሪካ ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የ2026 የ‘ሮቦፌስት’ ዓለም አቀፍ የአዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪዎች አስደናቂ ድሎችን አስመዝግበዋል።
ልጆቻችን ከ39 የቴክኖሎጂ ኃያላን ሀገራት ከተወጣጡ 738 ቡድኖች ጋር በመፎካከር ነው በተለያዩ ዘርፎች ማሸነፍ የቻሉት።
በውድድሩ በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ ኢትዮጵያውያን አዳጊዎች ቀዳሚ በመሆን ሲያሸንፉ፣ በሕክምና ሮቦቲክስ ዘርፍ 5ኛ እንዲሁም በፈጠራ ማሳያ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያውያን አዳጊዎች 2ኛ ደረጃን በማግኘት የሀገራቸውን ስም ማስጠራታቸው ይታወሳል።
#ebc #ethiopia #robotics #robofest2026 #ai

የኢትዮጵያ ታዳጊዎች በዓለም አቀፉ የሮቦቲክስ ሻምፒዮና ታላቅ ድል ተቀዳጁ
#ethiopia | በአሜሪካ በሚቺጋን ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የ2026 የሮቦፌስት ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ተወካይ ቡድን ደማቅ ስኬት አስመዝግቧል።
ቡድኑ እንደ ታይዋን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ካሉ በቴክኖሎጂ የበለጸጉ 39 አገራት እና በዓለም ዙሪያ ከተወዳደሩ 738 ቡድኖች ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ የሚከተሉትን ከፍተኛ ውጤቶች አግኝቷል።
በሕክምና ሮቦቲክስ የሕዝብ ምርጫ ዘርፍ አንደኛ ደረጃ፣
በሕክምና ሮቦቲክስ ዋናው የውድድር ክፍል አምስተኛ ደረጃ፣
በፈጠራ ሥራዎች ማሳያ ዘርፍ ስድስተኛ ደረጃ፣
ይህ ስኬት ከመመዝገቡ ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሌላው የኢትዮጵያ የታዳጊዎች ቡድን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
እነዚህ ተከታታይ ውጤቶች የታዳጊዎቻችንን ዓለም አቀፍ ብቃት እና ትጋት ከማሳየታቸውም በላይ አገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ብሩህ ተስፋ የሚያረጋግጡ ናቸው።
#robofest2026 #robotics #ai #ethiopianyouth #technology #stem #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት ያከናወኗቸው ተግባራት
በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳይንሳዊ የምርምር ልህቀት፣ በከተማ ልማት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም እና በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።
• የፕሮጀክቶች ምረቃ እና የሥራ ጅማሮ
የመጋቢት ወር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ውስጥ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀዋል። ይህ ማዕከል 40 የላብራቶሪ ክፍሎችን እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮ-ኢኩቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ያካተተ ነው።
በከተማ ልማት ዘርፍ፣ የሚያዝያ ወር በአገልግሎት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ ረገድ ጉልህ እመርታ የታየበት ወር ነበር። የአራዳ ፓርክ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ገጽታ ለውጥ የታየበት ሲሆን፤ ቀደም ሲል ችላ ተብለውና ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቤቶች የሚገኙበትን 40 ሄክታር መሬት ወደ ዘመናዊ ሁለገብ መዳረሻነት ቀይሮታል። ይህ የተቀናጀ የመሠረተ-ልማት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት የታየበት ፕሮጀክት፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ700 በላይ ነባር ቤቶችን የማደስ ስራን አካቷል።
ከዚህም በተጨማሪ በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና የኦሊምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መሠረተ-ልማቶችን፣ የ15 የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎችን ሃውልት እና ለተነሺ ነዋሪዎች ተብለው የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን የያዘው የአዲስ ስፖርት ፓርክ በዚሁ ወር ተመርቋል።
የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት አቅም ለማሳደግ የ100 ሜጋ ዋት የአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተመርቋል። በተጨማሪም በሀዋሳ የቶዮ ምዕራፍ 2፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች ከአዲሱ የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ፋብሪካ ጋር በመሆን በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹህ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቱሪዝም ዘርፍ፦ በገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር የተገነባው የሀሮ ደንዲ ሎጅ በይፋ ተመርቋል። በመጨረሻም፣ እንደ መታወቂያ ምዝገባ እና የሥራ ፈቃድ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የታለመው የመሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት ስራ ጀምሯል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኅብረት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ጤና መሪ ሆነው የተሾሙት በያዝነው የሚያዝያ ነው።
ይህ ኃላፊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአካታች ዕድገት ቁልፍ መሣሪያ የሆኑትን የፈጠራ ሥራዎችን እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማሳደግ ረገድ እያሳዩት ያለውን የአመራር ጥበብ እውቅና የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንቁ አመራር ሰጪነት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያስመዘገበችውን ጉልህ ስራ የሚያሳይ ነው።
• የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአፈጻጸም ግምገማ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሦስተኛውን የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም እና የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ግምገማ መርተዋል። በዚህም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት 9.2 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ የተመዘገበውን ስኬታማ ሽግግር በዝርዝር ያሳየ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ያስመዘግቡ የነበሩ ተቋማት በአሁኑ ወቅት 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ ወደ ማስገባት ተሸጋግረዋል። ለዚህ ውጤት መገኘት ቁልፍ የሆነው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገቱ ዋና መሪ እንዲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው የሪፎርም አጀንዳ ነው።
ይህም እንደ ካፒታል ገበያ ባሉ አዳዲስ የፋይናንስ ሥርዓቶች እና እያደገ በመጣው የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተደገፈ ይገኛል።
• የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና ሮቦቲክስን በመጠቀም ወደ ቺፕስ እና ዳታ (ኢንዱስትሪ 4.0) መሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምርቶችን መተካት የቻለው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የይዞታ መጠን ወደ 88 በመቶ ማድረሱን በስኬትነቱ ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ሰላማዊ የባሕር በር ማግኘት የሀገር የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳትሆን ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እንደሚጨምርባት አስገንዝበዋል።
• ማህበራዊ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ አመራር፦
“ማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በተሰኘው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክክር መድረክ ላይ፣ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ19.8 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን እና ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ሥርዓተ-ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።
በጤናው ዘርፍም በቅደመ መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ መካከል የተሻለ ሚዛን ለመፍጠር ለ30 ዓመታት ያገለገለው ፖሊሲ እንዲሻሻል ተደርጓል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ32 (COP32) ጉባኤን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት የጀመረች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዝግጅቱ ከሀገራዊው የአረንጓዴ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴውን ሰብስበው አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
• ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትስስር፦
ኢትዮጵያ የብሩንዲ፣ የላይቤሪያ፣ የደቡብ ሱዳን እና የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንቶችን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያስተናገደች ሲሆን፤ ይህም በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ በርካታ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር፣ ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት (Afrexim) ባንክ ፕሬዝዳንት፣ እንዲሁም ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትርን በመቀበል በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ ከአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ጋር ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ጤና ረገድ የተሰጣቸውን ሚና ጨምሮ ሰፋ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሀገር ውስጥ ጉዳይ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በመገናኘት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ የፕሬዝዳንቱን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት በይፋ አራዝመዋል።
የሚያዝ ወር የትንሳኤ በዓል የተከበረበት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በማዘጋጀትና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ በማጋራት ተጠናቋል።
#ethiopiadelivers #pmoethiopia

6 months ago
የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ በአዲስ አበባ በድምቀት ተጀመረ
#fastmereja I አዲስ አበባ
በቴክኖሎጂ የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ያለመው የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በይፋ ተጀምሯል። የኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በሮቦቲክስ፣ በኮዲንግ እና በዲዛይኒንግ ዘርፎች የፈጠራ ብቃታቸውን እንደሚያሳዩ ታውቋል።
በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፣ መንግስት ለወጣቶች የፈጠራ ስራ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩንና መሰል ውድድሮች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስጠራት ያላቸውን ሚና ገልጸዋል። የኢትዮ ሮቦቲክስ መስራች አቶ ሰናይክረም መኮንን በበኩላቸው፣ መጪው ዘመን ድህነትና በሽታ በቴክኖሎጂ የሚሸነፉበት መሆኑን በመጥቀስ ታዳጊዎች ለችግር ፈቺነት እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት 15 ዓመታት ወጣቶችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ሲያሳትፍ የቆየው ኢትዮ ሮቦቲክስ፣ የዘንድሮው የፓን አፍሪካ ውድድር ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን የሚያጎለብቱበት ወሳኝ ድልድይ እንደሚሆን ይጠበቃል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በቻይና፣ ካናዳና አሜሪካ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ስኬታማ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወሳል።
#ኹነት

የሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ነገ ይከፈታል!
የዓመቱ "ምርጥ ችግር ፈቺ" ሽልማትን የሚወስደው ማን ይሆን?
የኢትዮ ሮቦቲክስ "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" የፓን አፍሪካ ውድድር ነገ ሐሙስ መጋቢት 24 በሳይንስ ሙዚየም በደመቀ ሁኔታ ይከፈታል!
ምን ይጠብቃችኋል?
*የታዳጊዎች አስደናቂ ሮቦቶች፣ ኮዲንግ እና ዲዛይኒንግ ውጤቶች።
-ለሀገራዊ ችግሮች የሚቀርቡ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች።
የነገ መሃንዲሶቻችንን አብረን እናበረታታ!

የወደፊት መሃንዲሶች መድረክ፦
የሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ነገ በሳይንስ ሙዚየም ይከፈታል!
#ethiopia | የዓመቱ "ምርጥ ችግር ፈቺ" ሽልማትን የሚወስደው ማን ይሆን? የኢትዮ ሮቦቲክስ "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" የፓን አፍሪካ ውድድር ነገ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በደመቀ ሁኔታ ይከፈታል።
በውድድሩ ምን ይጠብቃችኋል?
የታዳጊዎች አስደናቂ ሮቦቶች፣ የኮዲንግ (Coding) እና የዲዛይኒንግ ውጤቶች ለዕይታ ይቀርባሉ።
ለሀገራዊ ችግሮች ምላሽ የሚሰጡ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች የሚቀርቡበት ልዩ መድረክ ነው።
የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ጉዞ የሚመሩ ታዳጊዎችን የምናበረታታበት ታላቅ ክስተት ነው።
በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም
ነገ፣ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
ኑ!
የነገ መሃንዲሶቻችንን አብረን እናበረታታ!
የቴክኖሎጂ አቅማችንን በታዳጊዎቻችን ዓይን እንመልከት።
#getu #ethiorobotics #problemsolver #panafricanrobotics #sciencemuseum #ethiopiatech #codingforkids #stem #futureengineers #addisababa #ሮቦቲክስ #ሳይንስሙዚየም #ቴክኖሎጂ #ታዳጊዎች #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር በመጪው ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም ይካሄዳል
የኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" በሚል መሪ ቃል፣ ከመጋቢት 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የሚቆይ የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር በሳይንስ ሙዚየም እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡ በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በሮቦቲክስ፣ ኮዲንግ እና ዲዛይኒንግ ያላቸውን የፈጠራ ብቃት የሚያሳዩ ሲሆን፣ ዓላማውም በቴክኖሎጂ የታገዘ ማህበራዊና ሃገራዊ ችግሮችን የሚፈታ ወጣት ትውልድ መገንባት ነው።
በዚህ ታላቅ ዓመታዊ ውድድር ላይ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘርፉ ተቋማትና ወላጆች የሚታደሙ ሲሆን፤ የነገዋን ኢትዮጵያ ተረካቢዎች እምቅ አቅም ይመለከት ዘንድ ሁሉም ተጋብዟል፡፡ መርሃ ግብሩ ታዳጊዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓለም ያላቸውን ተሳትፎ ከማበረታታት ባለፈ፣ በወጣቶች መካከል የፈጠራ ፉክክርና የተሞክሮ ልውውጥ እንዲኖር ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
ኢትዮ ሮቦቲክስ ባለፉት 15 ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በቻይና፣ ካናዳና አሜሪካ በሚካሄዱ ዓለማቀፍ ውድድሮች ላይ በማሳተፍ የሃገራቸውን ስም እንዲያስጠሩ ሲያደርግ ቆይቷል። በመጪው ሃሙስና አርብ በሳይንስ ሙዚየም የሚካሄደው ውድድርም ተማሪዎች ያላቸውን ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያጎለብቱበትና ለታላላቅ የፈጠራ ስራዎች የሚዘጋጁበት ወሳኝ መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።

8 months ago
ታዳጊዎችን የሚያሳትፈው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" ይፋ ተደረገ
📌 አሸናፊዎች ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ይሳተፋሉ!
#ethiopia | በዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት አዘጋጅነት የሚካሄደውና ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 18 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎችን የሚያሳትፈው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የሮቦቲክስ ሻምፒዮና የ2026 የውድድር ይፋ ተደርጓል።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ በኤግዚት ሲስተምስ እና ልዩ ዝግጅቶች አስተባባሪነት የሚመራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በሮቦቲክስ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት ተጠቅመው ዓለም አቀፍ ችግሮችን እንዲፈቱ ዕድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጿል።
የዘንድሮው ውድድር ዋና ትኩረቱን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ በሆነው "የምግብ ዋስትና እና ዘመናዊ ግብርና" ላይ ያደረገ ሲሆን ተማሪዎች ክፍት ምንጭ (Open-source) የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለግብርናው ዘርፍ መፍትሄ የሚሰጡ ሮቦቶችን ዲዛይን የማድረግ፣ የመገንባት እና ፕሮግራም የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ይህም ወጣቶች የንድፈ-ሀሳብ እውቀታቸውን ወደ ተግባራዊ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ ውድድር በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ያለውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል። መንግስት ወጣቶች በቴክኖሎጂ ታግዘው ሀገራዊ ችግሮችን እንዲፈቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት ሚኒስትር ዴኤታው፣ እንዲህ ያሉ መድረኮች ለሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች መጎልበት ያላቸውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
የኤግዚት ሲስተምስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሔለን አቢ በበኩላቸው፣ ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ መፍትሔ ፈጣሪነት የምትሸጋገርበት ድልድይ መሆኑን ገልጸው፤ ውድድሩ በክልል ማጣሪያዎች፣ በሜንቶርሺፕ እና በቴክኒክ ስልጠናዎች ታጅቦ ዓመቱን ሙሉ የሚቀጥል የፈጠራ ጉዞ እንደሆነ አስረድተዋል።
ሀገራዊ የማጣሪያ ውድድሩ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ይካሄዳል።
በጁኒየር እና በሲኒየር ምድቦች አሸናፊ የሚሆኑ ሁለት ምርጥ ቡድኖች በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሚካሄደው "AI for Good Global Summit 2026" ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የመሳተፍ ዕድል ያገኛሉ።
ለአሸናፊዎቹ ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ የጉዞ ትኬት፣ የመግቢያ ፓስ እና ምግብ የሚቀርብላቸው ሲሆን፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መሪዎች ጋር የመገናኘት ሰፊ ዕድል ይኖራቸዋል ተብላል።
#roboticsforgood #aiforgood #ethiopiatech2026 #youthinnovation #stemethiopia #foodsecurityai #exitsystems #itu #roboticschallenge #futureleaders #digitalethiopialove

የ"ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የወጣቶች ውድድር በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።
📌 አሸናፊዎች ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ይሳተፋሉ!
#fastmereja I ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 18 ለሆኑ ወጣቶች የተዘጋጀውና በዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት (ITU) የሚመራው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የወጣቶች ሀገራዊ ውድድር በይፋ መጀመሩ ተበሰረ።
በዘንድሮው ዓመት ተወዳዳሪዎች በምግብ ዋስትና እና በግብርና ላይ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሔ የሚሆኑ ሮቦቶችን ይሠራሉ።
ውድድሩ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በጁኒየር እና ሲኒየር ምድብ አሸናፊ የሚሆኑ ሁለት ቡድኖች በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ ጉዞ ይበረከትላቸዋል።
ውድድሩ ወጣቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ (STEM) የታገዘ የችግር አፈታት ክህሎት እንዲያዳብሩና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ እንዲወክሉ ለማስቻል የታለመ ነው።
የውድድሩ አዘጋጅ የኤግዚት ሲስተምስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሰጡት መግለጫ፣ ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ መፍትሔ ፈጣሪ ለማድረግ የሚደረግ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን የመፍትሔ ፈጣሪ እንድትሆን እናስቀምጣት የተባለ ሲሆን በጋራ በመሆን 'ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ' (Robotics for Good)ን ውድድር ብቻ ሳይሆን፣
ሀገራዊ ንቅናቄ እናደርገዋለን ብሏል።

9 months ago
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ሊገነባ ነው
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ዩኒቨርሲቲ ሊገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ታላቅ የምርምርና የትምህርት ተቋም ግንባታ ይፋ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ነው።
ይህ አዲስ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የታመነ ሲሆን በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በዳታ ሳይንስ እና በሮቦቲክስ ዘርፎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ታቅዶ የተቀረጸ ነው።
ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሃገር ሁለት -ሁለት ስኮላርሽፕ እንሰጣለን ብለዋል።
ስራዎቻችን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ እናጠናቅቃለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ የጀመረችው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው መገንባት ለኢትዮጵያ ወጣቶች አዳዲስ የፈጠራ እድሎችን ከመፍጠሩም በላይ ሀገሪቱን በቀጠናው ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ ያፋጥነዋል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ እንዲህ ያሉ ልዩ የትኩረት መስኮች ያላቸው የትምህርት ተቋማት መገንባታቸው ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ Fourth Industrial Revolution ውስጥ ያላትን ድርሻ ከፍ የሚያደርግ ነው።
ዩኒቨርሲቲው ስራ ሲጀምር የምርምር ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ ለተለያዩ የልማት ዘርፎች የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በማፍለቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
seledadotio

10 months ago
ኢሎን ማስክ ገንዘብ መቆጠብ አያስፈልግም፣ AI ድህነትን ታሪክ ያደርገዋል አሉ
ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ እድገት ወደፊት ድህነትን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፋና ሰዎች ለወደፊት ህይወታቸው የሚያደርጉትን የገንዘብ ቁጠባ አስፈላጊነት እንደሚያስቀረው ገለጹ።
ማስክ በቅርቡ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ወደፊት "ሁለንተናዊ ከፍተኛ ገቢ" የሚባል ስርዓት እንደሚመጣ ተንብየዋል። ይህም ማለት በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚመነጨው ሀብትና ምርት ለሰው ልጆች ሁሉ በበቂ ሁኔታ ስለሚተርፍ፣ ባህላዊው የስራ ባህል አስፈላጊነቱ ቀርቶ ስራ በሰዎች ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ምርጫ ይሆናል ብለዋል።
ይህ አስተያየት የተሰጠው ታዋቂው የኢንቨስትመንት ባለሙያ ሬይ ዳሊዮ ለወጣት አሜሪካውያን አዲስ የቁጠባ አካውንት መከፈት አለበት በሚል ላቀረቡት ሃሳብ ምላሽ ነው።
ማስክ የሬይ ዳሊዮ ሃሳብ በጎ ቢሆንም፣ ቴክኖሎጂው ግን ህብረተሰቡ ስለ ገቢ፣ ስለ ስራ እና ስለ ፋይናንስ ዋስትና ያለውን አመለካከት መሰረታዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀይረው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ማስክ ማሽኖች አብዛኛውን ስራ በሚረከቡበት በዚያ ዘመን፣ የሰው ልጅ የህይወት ትርጉሙን እንዴት ሊያገኝ እንደሚችል ትልቅ ጥያቄ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቴክኖሎጂው መሰረታዊ ፍላጎቶችን ከማሟላት ባለፈ ለሁሉም ሰው የተትረፈረፈ ህይወት እንደሚያመጣ ቢገልጹም፣ ተቺዎች ግን ይህ ቴክኖሎጂ የሚያመጣው ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም ስለመድረሱ ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ኮርፖሬሽኑ ኢትዮጵያ በፋርማሲ ዘርፍ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጭ በህንድ እያስተዋወቀ ነው
#ethiopia | የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያ በፋርማሲ ዘርፍ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጭ በህንድ ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች እያስተዋወቀ ነው፡፡
በኮርፖሬሽኑ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ውብሸት ታደለ የተመራዊ ልዑካን ቡድን በ74ኛውን የሕንድ የፋርማሲዩቲካል ኮንግረስ አመታዊ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ ሀገሪቷ ለዘርፍ የምትሰጠውን ማበረታቻ እና ያዘጋጃቸውን መሰረተ ልማት በማስተዋወቅ ላይ ናቸው፡፡
በሀገሪቱ ሶስተኛዋ ትልቋ ከተማ ቤንጋሉር እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ባለሞያዎች ለዘርፉ አምራቾች፣ ሻጮች ፣ ገዢዎች ፣ ምሁራን እና ተማሪዎች ኢትዮጵያ በአፍረካ ብቸኛውን የፋርማሲዩቲካል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ገንብታ ለባለሀብቶች ዝግጁ ማድረጓን አብራርተዋል፡፡
በኤግዚቢሽኑ ህንዳውያን ባለሀብቶችን ጨምሮ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በኤግዚቢሽኑ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን ሴሚናሮች አዳዲስ የፋርማሲቲዩካል ግኝቶች ይፋ የተደረጉበት መድረክ እንዲሁም ለጤናው ዘርፍ አስተዋጽኦ በማበርከት ለይ ያሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ የፈጠራ ውጤቶችም ለእይታ ቀርበዋል።

አስደንጋጭ መረጃ !
ለሰው አስር ጉዳይ የሆነ ሮቦት ተሰራ !
አዲሱ የ ኤሎን መስክ ሀይማኖት "ቴክኖሎጂዝም "
የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤሎን ማስክ ሮቦት አምራች ድርጂት ቴስላ ከሰው ልጅ የእለት ከእለት ኑረት መስተጋብርና የተቀራረበ ሰዎኛ ብቻ የሆኑ ራስን ማስተማር በነፃ ፍቃድ ማሰብ መከወን የሚችሉ ሰው ሰራሽ ሮቦት አምርቻለሁና ። በዚህ አመትም አስር ሚሊዮን ኦፕቲመስ የተባሉ ሰዉ መሰል ሮቦቾንም በመላው አለም አገልግሎት ይሰጣሉ ብሏል ።
ኤሎን ማስክ እንደተናገረው ከሆነ
የቴስላ ኦፕቲመስ አዲስ ሮቦቶች ያለማንም ትዕዛዝ በቅልጥፍና ከማድቤት እስከ ድርጂቶች ከቀዶ ህክምና እስከ ሳይንሳዊ ምርምሮች እስከ ስፖርት በምድሪቱ ላይ የሰዉ ልጅ የሚሰራቸው ስራዎች በሙሉ በሳምንት ሰባት ቀን በቀን 24 ሰአታት ያለመታከት የሚሰሩ ናቸው ብሏል ።
እንደ መስክ ገለፃ ከሆነ እነዚህ እነዚህ የሰዉ አምሳል ያላቸው 5 ጫማ 11 ኢንች ቁመት 160 ፓውንድ የሚመዝኑ ኦፕቲመስ ሮቦቶች አሰልች ተደጋጋሚና ጉልበት የሚጠይቁ ስራዎች ስለሚችሉና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ ከ20,000 እስከ 30,000 ዶላር በመሆኑ ተመራጭ ስለመሆኑ ልክ እንደ ስማርት ስልክ ከገጠር እስከ ከተማ ይለመዳሉ ። ብሏል ።
በቴስላ ባለ አክሲዮኖች አመታዊ ስብሰባ ላይ ስለ ሮቦቶቹ በተሰጠው ማብራርያ
ሮቦቲክስና AI የሚቀጥለው ትውልድ ወሳኝ አጋዥ ናቸዉና ይህ አዲሱ በ2026 መጀመርያ ለገበያ የሚበቃው ምርት ባለቤቱ ቃል ሳያወጣ ትዕዛዝ ሳያስተላልፍ ገፅታዉን አቋቋሙን ፊቱን ስሜቱን አይተዉ ፍላጎቱን ተረድተዉ ያሻዉን የፈለገዉን አገልግሎት እንዲሰጡ "ሲም ቱሪል " የተባለ ቴክኖሎጂ ተገጥሞላቸዋል ተብሏል ።
በቴስላ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ በኤክስ (ቀደም ሲል ትዊተር) በተለጠፈ አጭር ክሊፕ ላብራቶሪ አካባቢ ሮቦቱ ትራንስፖርት አገልግሎት የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን መገጣጠም ፣እቃዎችን ማንሳትን
በጥንቃቄ አያያዝ እና መረጋጋት
ውስብስብ ተግባራትን ሲከዉን ታይቷል ።
ሙሉ የስራ ቀንን ለመደገፍ የተነደፈ 2.3 kWh ባትሪ ላይ ይሰራል የተባለው ኦፕቲመስ ሮቦቶ ልብስ በላውደሪ ማጠብ ቡና በማሽን ማፍላት፣ በቫክዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት ፣ የእቃ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ እቃ ማጠብ ከማቀዝቀዣ ውስጥ የሚጠጣ እንደሚያቀርብ፣ ቢራ መክፈት፣ ቆሻሻ መጣል፣ አትክልቶችን ማጠጣትና የቤት እንስሳትን ማጫወትን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን ይፈጽማል ብለዋል።
ስለአዲሱ ሮቦት መረጃ መውጣቱን ተከትሎ በርካቶች አስተያየት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከባድ ተቃዉሞ እየተሰማም ይገኛል ።
የሰው ተግባራትን መተካት ነዉና አላማው የሰውን አንጎል መስተጋብር ይቀንሳል እና የሰውን ልምድ የማበልጸግ የችሎታ እና የእውቀት ሰንሰለት ያስወግዳል።
ፕሮግራም የተደረጉ ስርዓቶች የበለጠ የላቁ እና ችሎታ ያላቸው ሲሆኑ ሰዎች በእነሱ ላይ ከመጠን በላይ ጥገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ይህ ጥገኝነት እንደ ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ ፈጠራ እና ችግር መፍታት ያሉ አስፈላጊ የሰው ልጅ ችሎታዎች እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ::
ሌሎችም ፦ምንም ጥርጥር የለውም ማሽኖች ከሰዎች በተሻለ መልኩ ተግባራትን ያከናውናሉ:: ነገር ግን ቡድንን የሚያጠናክሩትን የእርስ በርስ ግንኙነቶች መተካት አይችሉም:: AI የሰው ተግባራትን መተካት የሰውን አንጎል መስተጋብር ይቀንሳል እና የሰውን ልምድ የማበልጸግ የችሎታ እና የእውቀት ሰንሰለት ያስወግዳል።ብለዋል ።
ምንም እንኳን ወደ ህብረተሰቡ በአጠቃላይ ሲመጣ፣ የቴክኖሎጂው የተለያዩ የሰው ልጅ አመለካከቶችን እንዲቀበል ከፍተኛ ግፊት ሊኖር ይገባል። የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች Fei-Fei Li እና John Etchemendy "የዚህ ፈጣሪዎች በጎሳ፣ በፆታ፣ በባህል እና በማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ቡድኖች እንዲሁም እንደ ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ህክምና፣ ፍልስፍና፣ ታሪክ፣ ሶሺዮሎጂ፣ ኮሙኒኬሽን ያሉ ሰዎችን ግንዛቤ፣ ልምዶች እና ስጋቶች መፈለግ አለባቸው። ሲሉ ተናግረዋል ።
ጥርጥር የለውም ማሽኖች ከሰዎች በተሻለ መልኩ ተግባራትን ያከናውናሉ በዚህም በሚሊዮን ከስራ ይፈናቀላሉ ያለው ሀረሪ አለማችን አዉቃዉም ይሆን ሳታዉቀዉ አዲስ ቴክኖሎጂዝም የተባለ ሃይማኖት እየፈጠረች ነዉ ። ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ስሜትና ነፃ ሀሳብ ያላቸው ማሽኖች መሰራታቸው ለዘመናት የዘለቀው የአምላክና ፍጥረት ጥልቅ ሚስጥር በመጣስ አዲስ በቴክኖሎጂና በማሽን የሚያምን ቴክኖሎጂዝም የተባለ
ዘመን አመጣሽ ሀይማኖት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ጠንካራ ተቃዉሞ አሰምተዋል ::

11 months ago
የሩሲያ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ( ሮቦት 'አይዶል' ተብሎ የተሰየመው፣ በጥቂት ሰከንዶች ከተራመደ በኋላ በመድረክ ላይ ወድቋል።
1.7 ሜትር ቁመት ያለው ሮቦት ማክሰኞ በሞስኮ በተካሄደ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ ላይ ይፋ ተደርጓል።
ሮቦቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሮቦቲክስ መስክ የሩሲያ ዕድገት ምልክት ተደርጎ እየቀረበ ነበር።
ነገር ግን ትዕይንቱ ከተጀመረ ብዙም ሳይቆይ ሮቦቱ ተሰናክሎ በፊቱ መውደቁ ዝግጅቱ በፍጥነት እንዲቋረጥ አድርጓል።
አዘጋጆቹ ስህተቱን ለመሸፈን ሲሉ የመድረኩን መጋረጃ በፍጥነት ዘግተዋል።
የአይዶል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቭላድሚር ቪቱኪን እንዳሉት፣ አደጋው የተከሰተው በሮቦቱ የእንቅስቃሴና ሚዛን ስልተ ቀመሮች (algorithms) ላይ በደረሰ "የማስተካከያ ስህተት" (calibration error) ምክንያት ነው።
ምንጭ፦ ዘ ኢንዲፔንደንት
Comments