5 months ago
የመድፈኞቹ ግስጋሴ እና የሲቲ መንገራገጭ
የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ወደ ሰሜን ለንደን እያመራ ነው?
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ፉክክር አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
በሳንቲያጎ ቤርናቢዮ በፌዴ ቫልቬሬዴ የሃትሪክ ጥቃት የደረሰበት ሀንጎቨር ገና ያልለቀቀው የሚመስለው የፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲ፣ ወደ መዶሻው መንደር (ዌስትሃም) አቅንቶ ሁለት ነጥብ ጥሏል።
በኦሎምፒክ ኤልዛቤት ፓርክ ዌስትሃም ለሲቲ አድፍጦ ነጥብ ማስጣሉ፣ ለአርሰናል የዋንጫ ጉዞ ትልቅ ውለታ ሆኖ ተመዝግቧል።
የአርሰናል የበላይነት እና የታዳጊው ማክስ ዶውማን ታሪክ
ማንችስተር ሲቲ ነጥብ በጣለበት በዚሁ ሳምንት፣ አርሰናል በታዳጊው ማክስ ዶውማን አስገራሚ ታሪክ ታጅቦ ኤቨርተንን በመርታት የነጥብ ልዩነቱን ወደ ዘጠኝ አድርሷል።
አሁን ላይ ለ22 ዓመታት የተናፈቀው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ራዳሩን ወደ ሰሜን ለንደን አቅጣጫ አድርጓል። አርሰናል ከመቼውም ጊዜ በላይ ለድል የፀና እና ጫናን የመቋቋም አቅሙን ያሳደገ ቡድን ሆኖ ቀርቧል።
አርሰናል እንደ ልማዱ ከታህሳስ እና ጥር በኋላ ይንገዳገዳል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ዘንድሮ ግን በአሰልጣኝ ማይክ አርቴታ መሪነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ሆኖ ታይቷል። የቡድኑ ያለመሸነፍ ስነ ልቦና እና በወሳኙ ሰዓት ውጤት ይዞ መውጣቱ፣ አርሰናልን በሊጉ አቻ የሌለው ቡድን አድርጎታል። 31ኛው ሳምንት እንደመሰከረው፣ አርሰናል ወደ መጨረሻው የድል መስመር (Final Lap) በልበ ሙሉነት እየተጠጋ ይገኛል።
በሌላ በኩል፣ የወትሮው ፍጹም የሆነው የፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲ ዘንድሮ ለደጋፊዎቹ ህልም ሆኖባቸዋል።
ሲቲ በእራሱ በአርሰናል ጥሪ የተጋበዘ ቢመስልም፣ አሁን ላይ ግን በመሪው እና በተከታዩ መካከል ያለው የዘጠኝ ነጥብ ልዩነት አርሰናልን ወደ ንግስናው ይበልጥ አቅርቦታል።
#አርሰናል #ማንችስተርሲቲ #ፕሪሚየርሊግ #ማይክአርቴታ #ማክስዶውማን #እንግሊዝ #ስፖርት #ጌጡተመስገን #getutemesgen #arsenal #mancity #premierleague

Comments