9 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኦገስት 1 ቀን 2026 ጀምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ 25 የአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች የሚሰጠውን መደበኛ የቪዛ ማስተናገጃ አገልግሎት ማቋረጡን አስታውቋል። የትራምፕ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ በቅርብ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ የቪዛ አገልግሎቶች ትልቁ የማሻሻያ መርሃ ግብር ሲል ገልጾታል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት የቪዛ አመልካቾች ከዚህ በኋላ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቀጠሮ መያዝም ሆነ የቪዛ ሂደታቸውን ማጠናቀቅ አይችሉም። ከዚህ ይልቅ በአህጉሪቱ ወደተመደቡ 20 ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት እንዲያቀኑ ይደረጋል።
የቪዛ አገልግሎታቸው የተቋረጠባቸው 25ቱ ሚሲዮኖች አቡጃ (ናይጄሪያ)፣ አንታናናሪቮ (ማዳጋስካር)፣ አስመራ (ኤርትራ)፣ ባማኮ (ማሊ)፣ ባንጁል (ጋምቢያ)፣ ብራዛቪል (የኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ቡጁምቡራ (ብሩንዲ)፣ ኮናክሪ (ጊኒ)፣ ኮቶኑ (ቤኒን)፣ ደርባን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ፍሪታውን (ሴራሊዮን)፣ ጋቦሮኔ (ቦትስዋና)፣ ሃራሬ (ዚምባብዌ)፣ ጁባ (ደቡብ ሱዳን)፣ ሊብረቪል (ጋቦን)፣ ሊሎንግዌ (ማላዊ)፣ ሉሳካ (ዛምቢያ)፣ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)፣ ማሴሩ (ሌሴቶ)፣ ምባባኔ (ኤስዋቲኒ)፣ ንጃሜና (ቻድ)፣ ኒያሜይ (ኒጀር)፣ ኑዋክሾት (ሞሪታኒያ)፣ ዋጋዱጉ (ቡርኪና ፋሶ) እና ዊንድሆክ (ናሚቢያ) ናቸው። በደቡብ አፍሪካ ደርባን የሚገኘው የቪዛ ማዕከል ቢዘጋም፣ በኬፕታውን የሚሰጠው ተመሳሳይ አገልግሎት ግን ሳይቋረጥ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
20ዎቹ አዳዲስ ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት በአቢጃን፣ አክራ፣ አዲስ አበባ፣ ኬፕታውን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ዳካር፣ ዳሬሰላም፣ ጅቡቲ፣ ጆሃንስበርግ፣ ካምፓላ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሌጎስ፣ ሎሜ፣ ሉዋንዳ፣ ማላቦ፣ ሞንሮቪያ፣ ናይሮቢ፣ ፖርት ሉዊስ፣ ፕራያ እና ያውንዴ የሚገኙ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ማዕከል በርካታ ጎረቤት ሀገራትን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ለምሳሌ ከማሊ የሚመጡ አመልካቾች በዳካር (ሴኔጋል)፣ እንዲሁም ከቤኒን እና ኒጀር የሚመጡት ደግሞ በሎሜ (ቶጎ) የቪዛ ሂደታቸውን እንዲያከናውኑ ይመራሉ።
ሚኒስቴሩ ውሳኔውን የትራምፕ አስተዳደር ብሔራዊ ደህንነትን ለማጠናከር፣ የማጣራት ሂደቶችን ወጥ ለማድረግ፣ የመንግስት ወጪን ለመቀነስ እና የአሰራር ቅልጥፍናን ለማሻሻል ከሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን አብራርቷል። ተመሳሳይ የውህደት ስራዎች በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና በአውሮፓ ክፍሎች ቀደም ሲል መከናወናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ብሔራዊ ደህንነትን በማጠናከር እና የመንግስትን ብክነት በመቀነስ አሜሪካን እና አሜሪካውያንን እያስቀደሙ ነው ብሏል።
ይህ ማሻሻያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የቪዛ ማመልከቻዎችን የሚያስተናግዱ የአሜሪካ ሚሲዮኖችን ቁጥር ከ50 ገደማ ወደ 20 ዝቅ ያደርገዋል። ይህ በአመልካቾች ላይ ጉልህ የሆነ ተግባራዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን፣ የአገር ውስጥ የቪዛ አገልግሎት በተቋረጠባቸው ሀገራት የሚገኙ ዜጎች በአካል ለሚደረግ ቃለ ምልልስ እና የጣት አሻራ (ባዮሜትሪክ) ምዝገባ አለም አቀፍ ድንበሮችን አቋርጠው ለመጓዝ ስለሚገደዱ ለተጨማሪ የትራንስፖርት እና የማረፊያ ወጪዎች ይዳረጋሉ።

2 months ago
የአሜሪካ መንግሥት ከአፍሪካ ቪዛ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን መካከል ኢትዮጵያን አልቀነሳትም
#ethiopia | የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ አህጉሉአንዳ የሚሰጠውን የቪዛ አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እየተዘጋጀ ነው።
በዚህ መሠረት በአፍሪካ ውስጥ የቪዛ አገልግሎት የሚሰጡ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ቁጥር ከ50 ወደ 20 ብቻ ለመቀነስ ወስኗል። ይህ ለውጥ በቅርብ ጊዜያት ይጀመራል ተብሏል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ያጸደቁት ይህ አዲስ እቅድ፣ በአፍሪካ 20 ዋና የክልል ማዕከላት (Regional Hubs) በመሾም፣ ሌሎች ቦታዎችን የቪዛ ሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ለመዝጋት ያቀደ ነው።
እነዚህ የ20 ዋና ማዕከላት የትኞቹ ናቸው ፦
° አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 🇪🇹
° አክራ (ጋና) 🇬🇭
° ዳካር (ሴኔጋል) 🇸🇳
° ጅቡቲ (ጅቡቲ) 🇩🇯
° ካምፓላ (ኡጋንዳ) 🇺🇬
° ኪጋሊ (ሩዋንዳ) 🇷🇼
° ኪንሻሳ (ኮንጎ) 🇨🇩
° ላጎስ (ናይጄሪያ) 🇳🇬
° ናይሮቢ (ኬንያ) 🇰🇪
° አቢጃን (አይቮሪ ኮስት) 🇨🇮
° ዳሬሰላም (ታንዛኒያ) 🇹🇿
° ሎሜ (ቶጎ) 🇹🇬
° ሉዋአንዳ (አንጎላ) 🇦🇴
° ማላቦ (ኢኳቶሪያል ጊኒ) 🇬🇶
° ሞንሮቪያ (ላይቤሪያ) 🇱🇷
° ፖርት ሉዊስ (ሞሪሸስ) 🇲🇺
° ፕራያ (ኬፕ ቨርዴ) 🇻🇪
° ያውንዴ (ካሜሩን) 🇨🇲
° ኬፕ ታውን (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
° ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
ከእንግዲህ ወዲያ በእነዚህ 20 ማዕከላት ያልተካተቱ ሀገራት ዜጎች የቪዛ ቃለ መጠይቅ፣ የጣት አሻራ እና ሌሎች ሂደቶችን ለማጠናቀቅ በራሳቸው ወጪ ወደ ቅርብ ማዕከል መጓዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል ያለው ቲክቫህ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

7 months ago
ኢኳቶሪያል ጊኒ ከተማዬ ጠበበችኝ አለች
📌ማላቦ በ"ኪዩዳድ ዴ ላ ፓዝ" ተተካች
#ethiopia | የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት ዋና ከተማውን ከደሴቷ ማላቦ ወደ ዋናው ምድር (Mainland) በማዛወር በታሪኩ አዲስ ምዕራፍ መጀመሩን አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ በፈረሙት ፕሬዝዳንታዊ መመሪያ መሰረት፣ "ኪዩዳድ ዴ ላ ፓዝ" (Ciudad de la Paz) የሃገሪቱ አዲሷ ይፋዊ ዋና ከተማ ሆናለች።
🏗️ ለለውጡ ያበቁ ዋና ዋና ምክንያቶች
ይህ ውሳኔ ለሃያ ዓመታት ሲታቀድ የቆየና ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ያለው ሲሆን፣ ለውጡ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* የመልክዓ ምድር መገለል፦ የቀድሞዋ ዋና ከተማ ማላቦ ከሃገሪቱ ዋና ምድር ተነጥላ በቢዮኮ ደሴት ላይ የምትገኝ በመሆኗ፣ አስተዳደራዊ ትስስርን ፈታኝ አድርጎት ቆይቷል።
* የሕዝብ መጨናነቅ፦ በማላቦ ከተማ ያለው ፈጣን የሕዝብ ቁጥር እድገትና የከተማዋ መስፋፋት ለአስተዳደር ስራዎች አስቸጋሪ ሁኔታን መፍጠሩ ተገልጿል።
🕒 የአንድ ዓመት የሽግግር ጊዜ
በፕሬዝዳንቱ መመሪያ መሰረት፣ ሁሉም የመንግስት ተቋማት እና መስሪያ ቤቶች በሚቀጥለው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ አዲሷ ዋና ከተማ ሙሉ በሙሉ ተዛውረው ስራ መጀመር ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጂ በከተማዋ የሚገኙ የውጭ ሃገራት ኤምባሲዎች ስለሚዘዋወሩበት ሁኔታ እስካሁን በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም።
"ኪዩዳድ ዴ ላ ፓዝ" ትርጉሙ "የሰላም ከተማ" ማለት ሲሆን፣ ከተማዋ የተገነባችው በሃገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኝ ጫካ ውስጥ ታቅዶ መሆኑ ይታወቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢኳቶሪያልጊኒ #አፍሪካ #ዋናከተማ #ማላቦ #ኪዩዳድዴላፓዝ #ፖለቲካ #equatorialguinea #newcapital #ciudaddelapaz

ኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማዋን ወደ ሲውዳድ ዴ ላ ፓዝ አዛወረች
በፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ምባሶጎ የወጣ አዋጅ፣ ዋና ከተማዋን በደሴት ላይ ከምትገኘው ማላቦ በመነሳት በሀገሪቱ ዋናው የየብስ ክፍል ላይ ወደምትገኘው ሲውዳድ ዴ ላ ፓዝ ቀይሯታል።
ቀደም ሲል የዚች በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝና ስፓኒሽ ቋንቋን ብቸኛ ብሔራዊ ቋንቋዋ አድርጋ የምትጠቀም ሀገር ማእከል ማላቦ ነበረች።
እንደ አዋጁ ገለጻ፣ ይህ ያልተጠበቀ እርምጃ የታለመው የሥልጣንና የአገልግሎት ክፍፍልን ለማስፋፋት ነው።
ትልልቅ ከተሞች የሆኑት ማላቦ እና ባታ "ቁጥጥር ካልተደረገበት የሕዝብ ቁጥር ዕድገት" ጋር እየታገሉ ሲሆን፣ ይህም ለከተማ ፕላን ችግር፣ ለመሠረተ ልማት አቅርቦት መብዛት እና ለክልላዊ አለመመጣጠን ምክንያት ሆኗል።
በአንጻሩ ሲውዳድ ዴ ላ ፓዝ ለዘመናዊ ዕድገት ሰፊ ቦታ የምትሰጥና ከሌሎች ክልሎች ጋር የተሻለ ግንኙነት ያላት ከተማ ናት። ከተማዋ ከኦቢያንግ የትውልድ ክልል 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

12 months ago
የወሲብ ቪድዮዎች ሾልከው የወጡበት ባልታዛር የስምንት ዓመት እስር ተፈረደበት
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ዘመድ የሆነው እና ከወራት በፊት ሾልኮ የወጣ የወሲብ ቪዲዮን ተከትሎ መነጋገሪያ የነበረው ባልታዛር በገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል የስምንት ዓመት እስር ተፈረደበት።
የቀድሞው የብሔራዊ ፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ኃላፊ የነበረው ባልታዛር ኢባንግ ኢንጎንጋ የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅሙ አውሏል ሲል ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።
መልከ መልካም መሆኑን ተከትሎ "ቤሎ" በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ባልታዛር፣ ባለፈው ዓመት ከተለያዩ ሴቶች ጋር ወሲብ ሲፈጽም የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎች ይፋ ከሆኑ በኋላ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ከባልታዛር ጋር ወሲብ ሲፈጽሙ የሚታዩት ሴቶች ባለትዳር እና የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሚስቶች እና ዘመዶች የሆኑ ሴቶች መሆናቸው በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ቪዲዮዎቹ ሾልከው የወጡት ባልታዛር በእስር ላይ እያለ ሲሆን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የተጭበረበረ ገንዘብ በካይማን ደሴቶች ውስጥ በተከፈተ በምሥጢራዊ አካውንት አስቀምጧል በሚል ተወንጅሏል።
ባልታዛር ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ገንዘቡ ለጉዞ አበል የተፈቀደ ነው ካሉ ሌሎች አምስት ባለሥልጣናት ጋር ሲሆን፣ የገንዘብ መጠኑም ከ9,000 እስከ 220 ሺህ ዶላር የሚደርስ ነው ተብሏል።
ባልታዛር በቁጥጥር ሥር የዋለው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሲሆን፣ የቀረበበት ክስ ደግሞ ዳጎስ ያለ ገንዘብ በመመዝበር ካይማን ደሴቶች ላይ ወዳለ አካውንት አዛውሯል የሚል ነው።
ባልታዛር ከበርካታ ሴቶች ጋር ወሲብ ሲፈጽም የሚያሳዩ ቪድዮዎች ይፋ የሆነበት በነዳጅ ዘይት የበለፀገችው ማዕከላዊ አፍሪካ አገር ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቀውን ሰው ለማጣጣል ነው የሚሉ ማላምቶችም ይሰጣሉ።
አገሪቷን በአውሮፓውያኑ ከ1979 ጀምሮ የመሩት ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ የባልታዛር አጎት ሲሆኑ፣ ፕሬዝዳንቱን ወደፊት ይተካሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሰዎች መካከልም ባልታዛር አንዱ ነበር።
ባልታዛር ብላክ ቢች ወደ ተባለው በዋና ከተማዋ ማላቦ ወደሚገኝ ስሙ የጠለሸ እስር ቤት የተላከ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ከፍተኛ ስቃይ የሚደርስባቸው እዚህ እስር ቤት እንደሆነ ይነገራል።
የባልታዛር ስልኮች እና ኮምፒውተሮች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው የወሲብ ቪድዮዎቹ በይነ መረብ ላይ በስፋት መሠራጨት የጀመሩት።
ቪድዮዎቹ አንድ በአንድ የተለቀቁት በቴሌግራም ላይ ወሲባዊ ምሥሎችን በሚለጥፍ ገጽ አማካይነት ነበር።
ኢኳቶሪያል ጊኒ ውስጥ ደግሞ በስፋት የተሠራጩት በዋትስአፕ ገፆች ሲሆን የቪዲዮዎቹ ትክክለኛነት ግን እስካሁን አልተረጋገጠም።
ፍርድ ቤቱ በባልታዛር ላይ የእስራት ቅጣት ከማስተላለፉ በተጨማሪ የ220 ሺህ ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደጣለበት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬስ ዳይሬክተር የሆኑት ሂላሪዮ ሚቶጎ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ዘግቧል።
BBC

በምስራቅ አፍሪካ የታንዛኒያን ያህል ስትራቴጂካዊ አጋር የለኝም ! / ሞስኮ /
የረዥም ርቀት የስልጠና ተልእኮ ላይ የምትገኘው የሩስያ ባልቲክ ማሰልጠኛ ንብረት የሆነችዉ ስሞሊ የተባለችው የስልጠና መርከብ የረጅም ርቀት የስልጠና ጉብኝት በማድረግ የመጠጥ ውሃ፣ ነዳጅ እና የምግብ አቅርቦቶችን ለመሙላት ዳሬሰላም ታንዛኒያ መገኘቷ ተሰማ ።
የሩሲያ የሥልጠና መርከብ በታንዛኒያ መገኘት በአፍሪካ ትልቅ ቦታ ለመያዝ እየተፎካከሩ ከሚገኙት የአለም ኃያላን አንዷ የሆነችው ሞስኮ ፍላጎቷን ለማሳካት የባህር በር ለሌላቸው ጎረቤቶች ለማግኘትና እግሮቿን ለመትከል ለምታደርገው ጥረት ታንዛኒያን እንደ መተላለፊያ ለመጠቀም ማሰቧን የሚያሳይ ነዉ ተብሏል ።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለፀው
ሩሲያ እና ታንዛኒያ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ ታንዛኒያ የረዥም ርቀት የስልጠና ተልእኮዋ አካል ማድረጓን የገለፀ ሲሆን ከ300 በላይ የባህር ኃይል አባላትን ያሳፈረችዉ ስሞልኒ መርከብ ዳሬሰላም ታንዛኒያ በመገኘት የስልጠና ጉብኝት የመጠጥ ውሃ፣ ነዳጅ እና የምግብ አቅርቦቶችን መሙላት መቻሏንና ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ገልጿል ።
የሩስያ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የታንዛንያዉ ጉብኝት የረዥም ርቀት ጉዞው አካል እንደሆነና ከዚህ ቀደም አምስት የአፍሪካ ወደቧችን መጎብኘቷን በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ በመካከለኛው አፍሪካ ደሴት ሀገር፣ በኮንጎ ሪፐብሊክ ፖይንቲ-ኖየር እና በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን"ተመሳሳት ጉብኝት አድርጋለች ሲል ዘግቧል ።
በሩሲያ የታንዛኒያ አምባሳደር Andrey Avetisyan በጁን 2024 ሁለቱም ሀገራት በተፈራረሙት የሁለትዮሽ ግኑኝነት መሰረት ንግድን በብሔራዊ ገንዘባቸው ለማሳደግ ቱሪዝም ፣ ንግድ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀው ይህ እርምጃ በአሜሪካ ዶላር ላይ ጥገኛ ላለመሆን እየተደረገ ያለ ተግባር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።
ለዘገባው ሞስኮ ታይምስ የታንዛኒያ ኮሚኒኬሽን ኦል አፍሪካን ተጠቅመናል ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Sponsored by
Surafel
Comments