Logo
YenetaTube
በምስራቅ አፍሪካ የታንዛኒያን ያህል ስትራቴጂካዊ አጋር የለኝም ! / ሞስኮ /

‎የረዥም ርቀት የስልጠና ተልእኮ ላይ የምትገኘው የሩስያ ባልቲክ ማሰልጠኛ ንብረት የሆነችዉ ስሞሊ የተባለችው የስልጠና መርከብ የረጅም ርቀት የስልጠና ጉብኝት በማድረግ የመጠጥ ውሃ፣ ነዳጅ እና የምግብ አቅርቦቶችን ለመሙላት ዳሬሰላም ታንዛኒያ መገኘቷ ተሰማ ።

‎የሩሲያ የሥልጠና መርከብ በታንዛኒያ መገኘት በአፍሪካ ትልቅ ቦታ ለመያዝ እየተፎካከሩ ከሚገኙት የአለም ኃያላን አንዷ የሆነችው ሞስኮ ፍላጎቷን ለማሳካት የባህር በር ለሌላቸው ጎረቤቶች ለማግኘትና እግሮቿን ለመትከል ለምታደርገው ጥረት ታንዛኒያን እንደ መተላለፊያ ለመጠቀም ማሰቧን የሚያሳይ ነዉ ተብሏል ።

‎የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለፀው
‎ሩሲያ እና ታንዛኒያ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ ታንዛኒያ የረዥም ርቀት የስልጠና ተልእኮዋ አካል ማድረጓን የገለፀ ሲሆን ከ300 በላይ የባህር ኃይል አባላትን ያሳፈረችዉ ስሞልኒ መርከብ ዳሬሰላም ታንዛኒያ በመገኘት የስልጠና ጉብኝት የመጠጥ ውሃ፣ ነዳጅ እና የምግብ አቅርቦቶችን መሙላት መቻሏንና ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ገልጿል ።

‎የሩስያ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የታንዛንያዉ ጉብኝት የረዥም ርቀት ጉዞው አካል እንደሆነና ከዚህ ቀደም አምስት የአፍሪካ ወደቧችን መጎብኘቷን በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ በመካከለኛው አፍሪካ ደሴት ሀገር፣ በኮንጎ ሪፐብሊክ ፖይንቲ-ኖየር እና በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን"ተመሳሳት ጉብኝት አድርጋለች ሲል ዘግቧል ።

‎በሩሲያ የታንዛኒያ አምባሳደር Andrey Avetisyan በጁን 2024 ሁለቱም ሀገራት በተፈራረሙት የሁለትዮሽ ግኑኝነት መሰረት ንግድን በብሔራዊ ገንዘባቸው ለማሳደግ ቱሪዝም ፣ ንግድ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀው ይህ እርምጃ በአሜሪካ ዶላር ላይ ጥገኛ ላለመሆን እየተደረገ ያለ ተግባር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።

‎ለዘገባው ሞስኮ ታይምስ የታንዛኒያ ኮሚኒኬሽን ኦል አፍሪካን ተጠቅመናል ።

‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ



12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.