1 month ago
የመንግሥት ኃላፊዎችን አምስት ዓመት የሚያስረው አዋጅ ፀደቀ።
#ethiopia | መረጃን የደበቀ ማንኛውም የመንግሥት ኃላፊ አምስት ዓመት የሚያሳስረው አዋጅ በምክር ቤቱ ጸድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነጻ መረጃ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
የዚህ አዋጅ አላማ ሙስናን፣ ሕገ-ወጥ አሠራርን ወይም የሥራ ብቃት ማነስን ለመሸሸግ ሲሉ መረጃና ሰነድ የሚደብቁ ወይም እንዲጠፉ የሚያደርጉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ነው።
ጥፋቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት የማንኛውም የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ የመረጃ ኃላፊ ወይም ትዕዛዝ ሰጪ አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል።
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት #የነጻመረጃረቂቅአዋጅ #ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

አብረው ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የስፖርትና የቱሪዝም ዘርፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንደሚኖረው በሚጠበቀው የመጀመሪያው ከፍተኛ ደረጃ የMMA (Mixed Martial Arts) ውድድር ላይ ትብብር ለመፍጠር፣ Sweat Box እና Kuriftu Resorts የመግባቢያ ስምምነት (MOU) አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ ዝግጅት የሚካሄደው ግዙፉ የ"MMA" (Mixed Martial Arts) ውድድር፣ ለስኬታማነቱ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።
የMMA ውድድር ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
ውድድሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የመዝናኛ ዘርፍ አቅም ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
በስምምነቱ መሰረት ተወዳዳሪዎች ለ1 ወር በኩሪፍቱ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስምምነቱ ለአንድ አመት እንደሚቆይ ተነግሯል።
ስምምነቱ የMMA ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ ሪዞርቶች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጋራ የጤና እና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገራዊ የጤና ንቅናቄዎችን እና የተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት መንገድ ይከፍታል።
እንደዚሁም ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሥራት በሀገሪቱ የስፖርትና የጤና (Wellness) ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለመፍጠር አቅደዋል።
በዚህም መሠረት የጋራ የጤናና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገር አቀፍ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን እና የተለያዩ የስፖርት ዝግጅቶችን በጋራ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#kurifturesort #sweatbox #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

የፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል የISO 15189 የብቃት ማረጋገጫ አገኘ
#ethiopia | ከተመሠረተ 25 ዓመታትን ያስቆጠረው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ISO 15189:2022 የህክምና ላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።
የሆስፒታሉ መስራች እና ባለቤት እንዲሁም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ደ/ር ፍቅረማሪያም ጉድታ እንደተናገሩት ይህ ምዕራፍ ሆስፒታሉ ከ250 በላይ አለም አቀፍ የላቦራቶሪ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ለታካሚዎች የላቀውን እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሉ ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
የላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርዓት በሆስፒታል ላቦራቶሪ ውስጥ ሁሉንም ሂደቶች መደበኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ የተዋቀረ ነውም ብለዋል።
ሆስፒታሉ ያሟላቸው ቁልፋ የጥራት መስፈርቶች የላቦራቶሪው የጥራት ቁርጠኝነት ፣ሰነድ አስተዳደር የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ብቃት እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት ሬጉላተሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ያደረገው ተቋማዊ ግንባታ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው ለተወዳዳሪነት አክሪዲቴሽን መሠረታዊ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ዲኤታው ገለፃ ኢኖቬሽን በዛሬ ዘመን ዋና ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ተቋማትም በቴክኖሎጂ ታግዘው ሥራቸውን በጥራትና በተወዳዳሪነት መሥራት አለባቸው ብለዋል።
ተቋሙ በአለም ለ19ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የአለም የአክሪዲቴሽን ቀን ዘንድሮ ሰኔ 15 2018 "አክሪዲቴሽን ለፈጠራ እምነት እና ዘላቂነት በሚል ቃል በዓሉን አክብሯል።
በዕለቱም ፍቅረሰላም ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትም የምዘና ብቃት ማረጋገጫ እንዳገኙ ታውቋል።
"ወርቃማ ልቦች ፣ አገልጋይ እጆች !" በሚል መርህ ከክሊኒክ አንስቶ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታል 25 ዓመታት የዘለቀው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ፍቅረሰላምሆስፒታልሆስፒታል #የንግድናቀጠናዊትስስርሚኒስትር #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

2 months ago
ከስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
#ethiopia | አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ከስምምነት የደረሱባቸው የመግባቢያ ነጥቦች ይፋ ሆኑ።
አሜሪካ እና ኢራን ከሦስት ወራት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ብሎም በመላው ዓለም ከባድ ቀውስን አስከትሎ የቆየውን ጦርነት ለማስቆም ለወራት ሲደረግ የነበረው ድርድረ አርብ ዕለት ስዊትዘርላንድ ውስጥ በሚካሄድ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ይቋጫል ተብሏል።
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱ እንዲቆም በደረሱት የመግባቢያ ስምምነት ላይ ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ጦርነቱ እንደሚቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ተዘግቧል።
የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል ጦርነቱን ለማስቆም ስምምነት በተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ነጥቦችን ይፋ አድረገዋል።
የመገናኛ ብዙኃኑ ባቀረቧቸው ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች በሁለቱም ወገን ማረጋገጫ አልተሰጠባቸውም።
ሜህር የዜና ወኪል ከዘረዘራቸው ነጥቦች መካከል፦
* በሁሉም ግንባሮች ሊባኖስን ጨምሮ በቋሚነት ተኩስ ይቆማል
* አሜሪካ በኢራን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም
* በ30 ቀናት ውስጥ የአሜሪካ የባሕር ዕገዳ ይነሳል
* የአሜሪካ ጦር ከኢራን ለቅቆ ይወጣል
* የሆርሙዝ ወሽመጥ “በኢራናውያን ቁጥጥር” በ30 ቀናት ውስጥ ዳግም ይከፈታል
* አሜሪካ እና አጋሮቿ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ያቀርባሉ
* በኢራን የነዳጅ ዘይት እና ኢነርጂ ምርቶች ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት
* ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ላለማምረት ዳግም ታረጋግጣለች
አሜሪካ በቀጣናው ያላትን ጦር አትጨምርም እና አዲስ ማዕቀብም አትጥልም።
* ሜህር አክሎም የስምምነቱ መጨረሻ የኢራን እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ግማሽ ሃብቷ እስኪለቀቅ፣ የኢራን ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የባሕር ላይ ዕገዳው እስኪነሳ ድረስ የመጨረሻው ድርድር አይጀመርም ሲል ዘግቧል።
እንዲሁም የመጨረሻው ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ እንደሚጸድቅ ዘግቧል።
#አሜሪካ #ኢራን #ጦርነት #ስምምነት #bbc #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemsgen #mediacommunication

Sponsored by
Surafel
Comments