3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የቀድሞው የቼልሲ እና አርሰናል ኮከብ ሴስክ ፋብሪጋስ፣ ቼልሲ ወጣቱን ብሩህ አማካይ አንድሬ ሳንቶስን ለቀጥታ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ዩናይትድ በ£50 ሚሊዮን ፓውንድ አሳልፎ መሸጡን አስመልክቶ ጠንከር ያለ ስፖርታዊ ትችቱን ሰንዝሯል። ፋብሪጋስ የቼልሲን የዝውውር ፖሊሲ በጽኑ የተቸበትን ሐሳብ እንደሚከተለው አቅርቦታል፦
"ይህ ውሳኔ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ካሉ እጅግ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣት አማካዮች አንዱን በቀጥታ የፕሪሚየር ሊግ ተቀናቃኛችሁ ለሆነ ክለብ በ£50 ሚሊዮን ፓውንድ አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ፣ ትልቅ የንግድ ስራ እንደሰራችሁ ታስባላችሁ። አንድሬ ሳንቶስ ብዙዎች እንደሚጠብቁት ዓይነት ተጫዋች ሆኖ ከወጣ፣ የቼልሲ ደጋፊዎች ይህንን ዝውውር ለዓመታት በማዘን ያስታውሱታል።
"ነገሩን ይበልጥ ግራ የሚያጋባው ደግሞ፣ ቼልሲዎች በቋሚነት ሜዳ ላይ የማይገኙ ተጫዋቾችን ለማቆየት መወሰናቸው ነው። ሮሜዮ ላቪያ የማይታመን አቅም አለው፣ ይህን ማንም አይጠራጠርም፤ ነገር ግን እግር ኳስ የሚጫወተው ሜዳ ላይ እንጂ በህክምና ክፍል ውስጥ አይደለም። ጉዳት የልጁን አቅም እንድናይ እያገደው ባለበት ሁኔታ፣ አማካይ ክፍልህን በተስፋ ላይ ብቻ ልትገነባ አትችልም።
"አንድ ተጫዋች ጤንነቱን ጠብቆ ለመቆየት እየተቸገረ እና በበርካታ የውድድር ዘመናት ጥቂት ጨዋታዎችን ብቻ በሚያደርግበት ሁኔታ፣ ሌላኛው ወጣት አማካይ በየሳምንቱ ጠንካራ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ሆኖ ሳለ፣ በውሳኔያችሁ ላይ ከባድ ጥያቄ ሊነሳ ይገባል። በእግር ኳስ ውስጥ 'ሁልጊዜ ዝግጁ ሆኖ መገኘት' ከሁሉ የላቀው ብቃት ነው።
"ማንቸስተር ዩናይትዶች ለሚነሳው ትችት ምንም ደንታ አይኖራቸውም። የእንግሊዝን እግር ኳስ ጥንካሬ በሚገባ የተረዳ እና ከፍተኛ አቅም ያለውን ተጫዋች በማስፈረማቸው በደስታ ፈገግ ይላሉ። አንዳንዴ በዝውውር መስኮት ትልቁ ስኬትህ ውድ ተጫዋች ማስፈረምህ ሳይሆን፣ ተቀናቃኝህ በራሱ ፍቃድ የለቀቀውን ዕንቁ ጠልፎ መውሰድ ነው።
"ቼልሲዎች ለዓመታት ስለ 'የወደፊት ቡድን ግንባታ' ሲያወሩ ኖረዋል፤ አሁን ግን ከምርጥ ወጣት አማካዮቻቸው አንዱን በየዓመቱ ከሚፎካከሩት ክለብ ጋር እንዲቀላቀል ፈቅደዋል። ይህ ነው ፈጽሞ ሊገባኝ ያልቻለው።
"አንድሬ ሳንቶስ ወደ ኦልድ ትራፎርድ አቅንቶ ከፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ አማካዮች አንዱ ቢሆን፣ መጥፎ ዕድልን አትውቀሱ፤ ውሳኔያችሁን መለስ ብላችሁ እዩ። አንዳንዴ ክለቦች ድንቅ ተጫዋቾችን የሚያጡት መሸጥ ስላለባቸው ሳይሆን፣ በእጃቸው ያለውን ወርቅ ማወቅ ስለሚሳናቸው ነው።
"ቼልሲዎች ከባድ ቁማር ተጫውተዋል። ማንቸስተር ዩናይትድ ምናልባትም የዚህን አስርት ዓመት ምርጥ ዝውውር በቅናሽ ዋጋ አግኝቶ ይሆናል። ማነው ትክክል የሚለውን ጊዜ ይፈታዋል፤ ነገር ግን ሳንቶስ ብዙዎች እንደሚጠብቁት ብቃቱ ፈንድቶ ከወጣ፣ በስታምፎርድ ብሪጅ የሚነሳው አንድ ጥያቄ ብቻ ይሆናል፤ 'ለምን አሳልፈን ሰጠነው?'"

5 months ago
በጠንካራ መርህ ላይ የተመሰረተ ህይወት ወይም ስነስርአት(Discipline)፦የስኬትና የማደግ ሁሉ መሠረት ነው ::
በጠንካራ መርህ ወይንም ስነስርአት የሰው ልጅ በህይወቱ ሊያሳድገውና ሊያዳብረው የሚገባ እጅግ ኃያል የሆነ መሣሪያ ነው። ተነሣሽነት ይመጣል ይሄዳል ነገር ግን ስነሥርዓት በክፉ ቀንም ቢሆን አንኳ ሰዎች የህይወት ጉዞአቸው ሳይቋረጥ ወደፊት እንዲቀጥል ያግዛል ።
እውነተኛው ስነሥርዓት ማለት መደረግ ያለበትን ነገር- ማድረግ በማንፈልግበት ሰአት እንኳ ቢሆን- ወጥና ቋሚ በሆነ መንገድ መከወን ማለት ነው። ከጊዜያዊ ምቾት ወይም የሚያዘናጉ ነገሮች ይልቅ በረዥም ጊዜ ግቦች ላይ ማተኮር ማለት ነው።
ጤናችንን ማሻሻል ፣ በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ መስራት ፣ ጤናማ አመጋገብ መከተል፣ ጭንቀትን ማስወገድ ፣ ቢዝነሳችንን ማሳደግ፣ ማህበራዊ ግንኙነታችንን መሻሻል ወይንም ከነዚህ የተለየ የግል ግቦቻችንን ማሳካት ሊሆን ይችላል፤ ስነሥርዓት ወይም ጠንካራ የህይወት መርህ እነዚህን ግቦች በማሳካት ሂደት ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል።
ትንንሽ የምንላቸው የየቀን ልማዶች በወጥነት ከተደጋገሙ በጊዜ ሂደት ይህ ነው የማይባል ለውጥ ያመጣሉ። በጥዋት መነሣት፣ በአካል ንቁ ሆኖ መገኘት ፣ በቂ ውሀ መጠጣት፣ ማንበብ፣ መማር፣ ጎጂ ልማዶችን ማስወገድ እና የሰውነታችንን ቅርፅ መጠበቅ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሁሉ በተግባር የሚታዩ የስነሥርዓት ምሳሌዎች ናቸው።
ስነሥርዓት ወይም ጠንካራ የህይወት መርህ ፍፁማዊነት አይደለም። ሁሉም ሰው ፈተናና እንቅፋት ያጋጥመዋል ። ከሁሉም ወሳኙ ነገር ጉዞአችንን በወጥነት፣ በትዕግሥትና ራስን በገዛ መልኩ ወደፊት ማስቀጠል ነው።
በብዙ መልኩ ብናየው ስነሥርዓት ያለው ህይወት ማለት ራስን ስለማክበር ነው። በጥቅሉ ሰዎች ህይወታቸውን ለማሻሻል ፣ ጤናቸውን ለመከላከልና የተሻለ ነገን ለመፍጠር በየቀኑ የሚያደርጓቸው ውሳኔዎ ነፀብራቅ ነው ልንለው እንችላለን።
በዶክተር ሲራክ ኃይሉ-
የካይሮፕራክቲክ ሐኪም
ሚኒሶታ

8 months ago
አውስትራሊያ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዜጎቿን "አልቀበልም" አለች
#ethiopia | የአውስትራሊያ መንግስት በሶሪያ የሚገኙ ዜጎቹን በተመለከተ ያለውን ጠንካራ አቋም ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ እንደተናገሩት፣ ማንኛውም በሶሪያ የሚገኝ አውስትራሊያዊ ከአሸባሪው አይኤስ ጋር ንክኪ ካለው ወደ አውስትራሊያ የመግባት ተስፋው ዝቅተኛ ነው።
የምርመራ ሂደት እና ቅድመ ሁኔታዎች
በቅርቡ ከሶሪያ እስር ቤቶች የተፈቱ 34 አውስትራሊያውያንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
* ጥብቅ ምርመራ፦ ማንኛውም ግለሰብ ከመመለሱ በፊት አስፈላጊው የደህንነት ምርመራ ይደረግበታል።
* ርዕዮተ-ዓለም፦ "የአይኤስን አክራሪ ርዕዮተ-ዓለም የደገፉ ግለሰቦችን በጭራሽ አንቀበልም" ሲሉ አልባኔዝ በግልጽ አስታውቀዋል።
* የሕግ ቅጣት፦ በአውስትራሊያ ሕግ መሠረት የአይኤስ አባል ሆኖ መገኘት እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ተገልጿል።
ውስጣዊ ተቃውሞ
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ቅሬታን ፈጥሯል። አንዳንድ የፓርላማ አባላት የዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ መብት እና መንግስት የወሰደውን ጥብቅ አቋም በመቃወም አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት መንግስት እነዚህን ዜጎች ወደ ሀገር ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት ከከፍተኛ ምርመራ እና ከርዕዮተ-ዓለም ነፃ የመሆን ማረጋገጫ ጋር የተያያዘ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #australia #thiqah #anthonyalbanese #syria #isis #nationalsecurity #globalnews #skynews #ashraqalawusat

የሰውነት ውርደት እና የገበታ ሥር ፍርፋሪ፦ የሃሊማ አብዱራህማን "ከገበታ በታች"
ይህ ዘፈን የሙዚቃ ድርሰት ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በሰውነቱ ሊያገኝ የሚገባው ክብር ተገፍፎ በቁስና በእንስሳት መካከል የወደቀበትን አሰቃቂ የታሪክ ምዕራፍ የሚዘክር "የልቅሶ ሰነድ" ነው። ኑረዲን ዒሳ በግጥሙ፣ ዓለማየሁ ደመቀ በዜማው፣ እና ካሙዙ ካሣ በቅንብሩ የፈጠሩት ይህ ድንቅ ስራ፣ የሰው ልጅን መዋቅራዊ ጭቆና በአስር ጥልቅ አንቀጾች እንደሚከተለው ይተነትነዋል።
የዓለም ታሪክ ምስክርነት፦ ከሮም ባሪያዎች እስከ አሜሪካ ጥቁሮች
ይህ ዘፈን በታሪክ ውስጥ የነበሩ የጭቆና መዋቅሮችን ያስታውሰናል። በጥንቷ ሮም፣ ባሪያዎች እንደ ሰው ሳይሆን "እንደሚናገር መሣሪያ" (Instrumentum Vocale) ይቆጠሩ ነበር። ልክ በዘፈኑ ውስጥ ግለሰቧ "ከገበታ በታች" ሆና እግር እንደምታሽ ሁሉ፣ በሮም መኳንንት ግብዣ ላይ ባሪያዎች እንደ ጠረጴዛ ወይም እንደ ወንበር እንዲያገለግሉ ይገደዱ ነበር።
በ18ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካ የነበረው የባርነት ሥርዓትም፣ ጥቁር ባሪያዎች ከጌቶቻቸው ፈረስና ውሻ ባነሰ ዋጋ የሚታዩበት፣ ልክ እንደ ዘፈኑ "የሹም ዶሮ" ከሰው የምትበልጥበት አሳዛኝ እውነታ ነበር። ይህ ዘፈን ያንን የዘመናት ዓለም አቀፋዊ ቁስል በኢትዮጵያዊ ቅኝት ያከክመዋል።
የቶማስ ሆብስ "የሰው ልጅ ለሰው ልጅ ተኩላ ነው" እይታ
ፈላስፋው ቶማስ ሆብስ በታዋቂው "ሊዋታን" (Leviathan) መጽሐፉ፣ የሰው ልጅ ያለ ጠንካራ የፍትህ መዋቅር "ሰው ለሰው ተኩላ ነው" (Homo Homini Lupus) ይላል።
በዘፈኑ ውስጥ የምናየው ጌታ፣ ለሰውነቷ ግድ የማይለውና ከገበታው በታች ጥሏት የሚረግጣት ተኩላ ነው። ሆብስ እንደሚለው፣ ኃይልና ሥልጣን ብቻ በሚነግሱበት ቦታ "ሕይወት ብቸኛ፣ ድሃ፣ አስቀያሚ፣ ጨካኝና አጭር" ትሆናለች። በግጥሙ ውስጥ የምናየው "ጥቁር አሞራ" እና "ጥቁር ደመና" የዚሁ ጨካኝ የተፈጥሮ ሕግና የፍትህ መጓደል ምልክቶች ናቸው።
የጆን ሎክ "የተፈጥሮ መብት" ጥሰት
በአንጻሩ፣ የእውቀት ብርሃን ፈላስፋው ጆን ሎክ ሰው ሁሉ በተፈጥሮው እኩል ነው፣ ማንም ሊነጥቀው የማይችለው የሕይወት፣ የነፃነትና የንብረት መብት አለው ይላል። "የርሳቸው ሰማይ ለኔም ሰማዬ" የሚለው መስመር የሎክን የሰው ልጅ እኩልነት ፍልስፍና ያንጸባርቃል። ሆኖም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ሎክ ከሚለው የተፈጥሮ መብት በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ "ከእንጨት በታች" የወረደበት ነው።
ይህ ንፅፅር የሰው ልጅ የተፈጥሮ መብቱ ተገፍፎ ወደ ቁስነት መውረዱን በታላቅ ሀዘን ይገልጻል።
የታሪክ ምሳሌ፦ የፊታውራሪ መሸሻ እና የገበሬው ሰቆቃ
በሐዲስ ዓለማየሁ "በፍቅር እስከ መቃብር" ውስጥ፣ ፊታውራሪ መሸሻ ገበሬውን "ከገበታዬ በታች" ብለው ሲጠሩት፣ ያ የዘመናት የፊውዳል ሥርዓት ንቀት መገለጫ ነበር። በ1950ዎቹ በኢትዮጵያ የነበረው የመሬት ሥርዓት ገበሬውን "ጭሰኛ" አድርጎት ነበር። ገበሬው አምርቶ ለጌታው ይገብራል፣ ጌታው ሲጠግብ ገበሬው ግን "ኩርማን እንጀራ" ይናፍቃል። ይህ ዘፈን ያንን የኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ፣ በዜማ የታጀበ የታሪክ መጽሐፍ አድርጎ ያቀርበዋል።
የሚሼል ፉኮ "ሥልጣንና ቁጥጥር"
ዘመናዊው ፈላስፋ ሚሼል ፉኮ ሥልጣን እንዴት የሰውን አካልና መንፈስ እንደሚቆጣጠር ይተነትናል። በዘፈኑ ውስጥ "እግር አሽታ" ሆኖ መገኘት የአካል መገዛት ብቻ ሳይሆን፣ ሥልጣን የሰውን ልጅ ማንነት ሰልቦ "ከገበታ በታች" እንዲኖር የማድረጉ ውጤት ነው። ፉኮ እንደሚለው፣ ጨቋኝ ሥርዓቶች ሰውን ወደ "ታዛዥ አካል" (Docile Bodies) ይቀይሩታል።
እዚህ ጋር ግለሰቧ ከወጋግራውና ከጣራው በታች ብቻ ሳይሆን፣ ከሥልጣን መዋቅሩ በታች ተቀጥቅጣ የቀረች ነፍስ ናት።
የፍሬድሪክ ሄግል "የጌታና የባሪያ" ዲያሌክቲክ
ሄግል እንደሚለው፣ ጌታ ጌታ መሆኑን የሚያውቀው በባሪያው እይታ ውስጥ ነው። ባሪያው ግን ከጌታው በበለጠ ከቁስ ጋር (ከወፍጮው፣ ከእርሻው) ጋር ስለሚገናኝ እውነተኛውን ዓለም ያውቀዋል። በዘፈኑ ውስጥ ወፍጮው ሲያጓራ፣ ጌታው የሚሰማው ድምፅ ብቻ ነው፤ ባሪያዋ ግን የረሃቡንና የድካሙን መራርነት ታውቀዋለች።
ሄግል እንደሚለው፣ መጨረሻ ላይ ነፃ የሚወጣው ድካሙንና መራርነቱን የሚያውቀው ባሪያው እንጂ፣ በቅንጦት የተሸፈነው ጌታ አይደለም። ይህ ዘፈን ያንን የንቃተ ህሊና ጅማሮ በቁጭት ይገልጻል።
የሐና አረንት "የሰው ልጅ ሁኔታ"
ፈላስፋዋ ሐና አረንት የሰው ልጅ ሕልውና በሥራ፣ በፈጠራና በፖለቲካዊ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ ነው ትላለች። በዘፈኑ ውስጥ ግን ግለሰቧ "ከእንቅርጣጩ ልቀሚ" ተብላ ስትገፋ፣ ከአረንት የሰውነት ትርጉም ውጭ ሆናለች። የሰው ልጅ በነፃነት ማውራትና መወሰን ሲያቅተው "ሰዋዊነቱን" ያጣል። "የሹም ዶሮ" ከሰው በላይ የምትከበረው፣ የሰው ልጅ በፖለቲካዊና በማህበራዊ መድረክ ላይ ያለው ድምፅ ስለጠፋና እንደ እንስሳ ስለሚቆጠር ነው።
የታሪክ ምሳሌ፦ የኢንዱስትሪ አብዮትና የልጆች ጉልበት ብዝበዛ
በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ የነበረው የኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት፣ ትናንሽ ልጆች ከማሽኖች በታች ሆነው ለቀናት ይሠሩ ነበር። ልክ በዘፈኑ ውስጥ "መጅና ወፍጮ ጠግቦ እያጓራ" እንደሚባለው፣ ማሽኖቹ በከሰልና በዘይት እየጠገቡ ሕጻናቱ ግን በረሃብ ይረግፉ ነበር። ይህ የዓለም ታሪክ ምሳሌ፣ በሃሊማ ዘፈን ውስጥ ካለው "እንጨት ሲበልጠኝ የት ሄዷል ጌታ?" ከሚለው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ነው። ቁስ ከሰው ሕይወት በላይ ዋጋ የሚሰጠው ሥርዓት ሁሌም አሳዛኝ ነው።
የኢማኑኤል ካንት "ሰው እንደ ዓላማ"
ኢማኑኤል ካንት "ሰውን ሁልጊዜ እንደ ዓላማ እንጂ እንደ መሣሪያ አትጠቀምበት" የሚል የሞራል ሕግ አለው። በዚህ ዘፈን ውስጥ ግን ጌታው ግለሰቧን እንደ "እግር አሽታ" (መሣሪያ) ብቻ ነው የተጠቀመባት። የሰው ልጅ ክብሩ ያለው "ሰው" በመሆኑ ብቻ እንጂ ለጌታው በሚሰጠው አገልግሎት መሆን አልነበረበትም። ካንት ይህን ቢያዳምጥ፣ የሞራል ሕጉ በጌታው ጣራ ሥር እንደፈረሰ ይረዳ ነበር።
መደምደሚያ፦ ከገበታ በታች ያለው የነፃነት ጩኸት
በአጠቃላይ "ከገበታ በታች" የሰው ልጅ በታሪክ ውስጥ ያለፈበትን የባርነት፣ የረሃብና የውርደት መንገድ የሚዘክር የሙዚቃ ሀውልት ነው። ይህ ዘፈን የሚያስተምረን፣ የሰው ልጅ ክብር ከቁስ፣ ከእንስሳትና ከማንኛውም መዋቅር በላይ መሆኑን ነው። ግጥሙ በለቅሶና በጥያቄ ቢደመደምም፣ ለዘመናዊው ትውልድ ግን ትልቅ መልዕክት ያስተላልፋል፦ "ገበታው" ለሁላችንም እኩል ካልሆነ፣ አንዱ በገበታው ላይ ሲበላ ሌላው ከገበታው በታች እግር የሚያሽ ከሆነ፣ ያ ማህበረሰብ በውስጡ የሞተ ነው።
የሰው ልጅ እውነተኛ ነፃነት የሚረጋገጠው ሁሉም ከገበታው በላይ እኩል ሲቀመጡ ብቻ መሆኑን ይህ ዘፈን በሀዘን ተውጦ ይነግረናል።

ኮረኔል ደረስ እንዳለ ~ የብዙዬ ልጅ !
#ethiopia | ሀገርን መውደድ በኃሳብና ቃላት ድርደራ ብቻ ፈፅሞ አይገልፅም ሀገርን የእውነት ከልብ መውደድ ድርጊትን እና ሆኖ መገኘትን ይፈልጋል ዳሩ በወታደር ቤት ለወታደር።
አንደበተ ርዕቱ ፤ ማሰብ ኃይሉ ፤ አዕምሮው ለሕዝቡ ጥቅል የፍቅር ስሜቱን የሚያስብ ለወገኑ ወዶገብ ሀገሩ ከአንደበቱ የማትጠፋው የአየር ላይ ተጓዡ ~ ኮረኔል ደረስ እንዳለ።
ከታሪክና ከመልካሙ ባሕል የሚነጠል ከወግና ልማዱ ጋር ጣውንት ማይሆን ኸያው ወገኑን ፈፅሞ የማይረሳ ጎልማሳ።
ሥመ ገናናው ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ የቀረጸው እንከን አልባው ሥርዓት “Utopia” ተፈፃሚ ቢሆን ዳሩ ዓለም እንከን አልባ ትሆናለች የሚል ግምት ፤ አይኖረኝም ብሎናል በምጥቀቱ።
በሥነ- ማሕበረሰብ ትስስር ውስጥ ራስን በቅጡ መረዳት ዳሩ ለምን ዓላማ ወደዚች ዓለም ፤ እንደ-መጣን መገንዘብ ጠንካራና ደካማ ጎንህን እና እምነትህን መፈተሽ ያለባችሁ ሲል ከዓመታት በፊት አንድ የሰፈራችን የሰርግ ድግስ ላይ ምክሩን ሲለግሥ አደመድጥነው በሱፍ ልብሱ ኮረኔልን።
ሁኔታ መገምገም ፤ ወደፊት ልታሳካው የምትፈልገውን ነገር አስቦ መድረስ ሕልማች ማግኘትን መገንዘብን እኔና ጓደኛዬ እታለማው ታፈሰ ( ሎክ ) አድምተን ኮረኔልን አደመጥነው።
ኮረኔል ደረስ የሚወዳት ሀገሩን ለሥስት አሥርት ዓመታት ገደማ ለተጠጋ ጊዜ በታማኝነት በሞያ እያገለገለ ይገኛል።
መነኩሴ ወላጅ እናቱን ኮረኔል ሁሌም በብዙ እንደሚወዳት ይናገራል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሥርዓተ ቤተ- ክርስቲያን ምንኩሥና ከእምነት የተመረጡ እጅግ ጥቂቶች የሚኖሩበት ክርስቲያናዊ - የሕይወት መንገድ ፤ እንደ ሆነ ይታመናል።
ኮረኔል ደረስ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተቋም በቅርቡ “አንበሶቹ ሰማይ ኢትዮጵያ” መሪ ቃል ላይ ባቀረበው የአየር ትርኢት ላይ ብቃቱን አሥመስክሯል። የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ከሆኑት ከሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ዘንድ የእውቅና ስጦታ እና ምሥጋና ለኮረኔል ደረስ እንዳለ ተችሮታል።
ኮረኔል ደረስ እንዳለ ለአያሌ ወጣቶቻችን መልካም አርአያ መሆን የሚችል ሀገሩን ለ 27 ዓመታት ያለ መታከት አቀበት ቁልቁለት እየወጣ የተሰጠውን ግዳጁ በጀግንነት እየፈፀመ በታማኝነት እሚያገለግል ሥመ- ጥር የጦር መኮንን ነው።
የብዙነሽ ሜይዴይ ልጅ ረጅም እድሜ ከጤና ተመኘውልክ !
ጌታመሳይ ሙሉጌታ

11 months ago
📌 የግብጽ ናሽናል ኢንተረስት ፤ ኢትዮጵያ ናሽናል ኢንተረስት እንዳይኖራት ማድረግ ነው
📌 ኦሮሚያ ውስጥ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ያለፈውን ስርዓት ከሆነ የሚጠይቁት ... ሄደዋል
ጊዜ ግስ ከ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ጋር
ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቲቪ እና በማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን ላይ ይጠብቁን።
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthio...
#nbcethiopia #ሆኖ_መገኘት #ethiopia

1 year ago
የማይናወጥ የሀገር ፍቅር፣ ሰጥቶ የማይረካ ቅን መንፈስ፣ ...
#ethiopia | በርካታ ቅን ሰዎች አሉ። መርዳትን፣ መደገፍን፣ ቸርነትን ማዕከል ያደረጉ። ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚሳካላቸው ግን ጥቂት ናቸው።
ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በቅንነት ማገልገልን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ማቋቋም፣ መምራትና ስኬታማ ማድረግ ብዙዎች የሚታደሉት ጸጋ አይደለም።
የማይናወጥ የሀገር ፍቅር፣ ሰጥቶ የማይረካ ቅን መንፈስ፣ ስለህዝብ በጽናትና ያለመታከት መቆርቆርን እውን ለማድረግ፤ መቻል ብቻ ሳይሆን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል።
ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የዚህ አይነት ሰብእና ከተጎናጸፉ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ማድረግን ስለሚችሉት ብቻ ሳይሆን ከልብ በመነጨ እምነትና ጽናት ማድረግን ሆነው መገኘት ችለዋል።
"ሚድሮኮች" የተጣለባችሁን አደራ በብቃትና በስኬት ተወጥታችሁ በሚቀጥለው ዓመት የሰራተኞችን ቀን ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በተገኙበት በድምቀት እንደምታከብሩ ሙሉ እምነት አለኝ።
ሙሼ ሰሙ

Sponsored by
Surafel
1 year ago
ሙሼ ሰሙ እንደፃፉት!...
መንግስት በአዲሱ የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት ለ160 ቢለየን ብር ተጨማሪ ወጭ እንደሚዳረግ ገልጿል። እስኪ የጭማሪውን ፋይዳ ለመረዳት ቁጥሮችን በአንጻራዊ ስሌት እናጢናቸው።
ቋሚ ደሞዝተኛው ገንዘቡ ኪሱ ከመግባቱ በፊት በገቢ ግብር ምክንያት ዝቅተኛው ተከፋይ 15% ከፍተኛው ደግሞ 35% ይቆረጥበታል። ዝርዝሩ ውስጥ መግባት ስለሚያዳግት አማካዩን ቁጥር እንወሰድ።
አማካዩ (15+35)/2 = 25% ይሆናል። ወደፊት እድሜውና ጤናው ከፈቀደለት የጡረታ ተከፋይ የሚያደርገው ቢሆንም ዛሬ ላይ ለጡረታ 7% ከደሞዙ በቀጥታ ይቆረጥበታል። 25%+7% = 32% ይሆናል።
160,000,000,000*0.32= 51,200,000,000 ይሆናል። ይህ ማለት ሃምሳ አንድ ቢሊየን 200 ሚሊየን ብር የደሞዝ ጭማሪው ተቀጣሪው እጁ ከመድረሱ በፊት ወደ መንግስት ካዝና ይመለሳል። በደሞዝ መልክ የሚከፋፉለው ቀሪም 108,800,000,000 ብር ይሆናል
ደሞዙ እጁ ላይ ከገባ በኋላ ደግሞ በሚሸምተው ቁሳቁስና በሚገዛው አገልግሎት ላይ 15% ቫት ይከፍላል። 108,800,000,000 *0.15 = 16,320,000,000 ይሆናል።
ይህ ማለት ደግሞ ከ160 ቢሊየን ብር ጭማሪ ውስጥ ደሞዝተኛውን ሳያገለግል በገቢ ግብር፣ በጡረታና በቫት ብቻ ወደ መንግስት ካዝና ተመልሶ የሚገባው ብር 67,520,000,000 ሲሆን ጭማሪው ደግሞ 92,480,000,000 ብር ይሆናል።
በመቀጠል ቀሪዎቹን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የግብር ዓይነቶች እናንተው አስሏቸው። ፕሮፐርቲ ታክስ (1%)፣ ተርን ኦቨር ታክስ(2%)፣ ትራንዛክሽን ታክስ (0.1% እስከ 1.5%) ....
ከዚህ ሁሉ ቅንስናሽ በኋላ የሚገኘው የደሞዝ ጭማሪ ኢሚንት ቢሆንም አይጠቅምም ማለት በእግሩ ተጓጉዞ፣ በቀን አንዴ ቀምሶ ከሚያተርፋት "ደሞዙ" ላይ በየእለቱ ለልጆቹ ደረቅ ዳቦ የማቅረብ ግዴታ የተጣለባትን ቋሚ ደሞዝተኛ ፈተናና መከራ በቅጡና በልኩ አለመረዳት ይሆናል።
ተወደደም ተጠላ፣ አነሰም ተከመረ ጭማሪው ጎዳና ለመውጣት እየተንደረደረ የነበረውን ቋሚ የመንግስት ደሞዝተኛ እንደሚደጉምና አንድ ቀዳዳ እንደሚደፍንለት ጥርጥር የለኝም። ደሞዝ መቼም በቂ ሆኖ አያውቅም። በቂ ካልሆነ ደግሞ ጭማሪው ይቅር ለማለት ቋሚ ደሞዝተኛውን ከነ መከራው እሱና ቤተሰቡን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል።

የሚድያ መሪ ሙሉጌታ ገሠሠ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ
#ethiopia | ተወዳጅ የሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል የሚድያ ሰዎችን ታሪክ ይሰንዳል፡፡ በትናንትናው ዕለት ሕይወቱ ያለፈው ሙልጌታ ገሰሰ በሚድያው ዘርፍ አሻራ ካሳረፉት አንዱ ነበር፡፡ ዕዝራ እጅጉ እና ቤርሳቤህ ጌቴ የሕይወት ታሪኩን እንደሚከተለው ሰንደውታል።
ሙሉጌታ ገሰሰ ትውልዱ መቀሌ ላይ በ1951 ዓ.ም ነበር።
በፋና ውስጥ መሥራች ከሚባሉና በአመራርነት ፋናን በከፍታ ካራመዱ መካከል ግንባር ቀደሙ ነው። የፋና ሬድዮ መሥራች፣ የብሪፊንግ ባህል በሌሎች የሚድያ ተቋማትም ጭምር እንደ መልካም ተሞክሮ ከመወሰዱ በፊት በፋና ሬድዮ ላይ ሥራን በግልፅነት በጋራ የመገምገምና ለነገ የተሻለ ሆኖ መገኘት መሠረት የሚጥለውን ሥርአት በማስጀመር ፣ የተቋሙን መሪ ቃሎች በተለያዩ ጊዜያት ከ1987- 1997 የቆየውን መሪ ቃል በማስወጣትና ተቋሙን በይዘትም ሆነ በቴክኖሎጂ ለማዘመን ብልህ አመራርነቱን ያስመሰከረ ጠንካራ የሚድያ መሪ ነው።
በፋና 25ኛ አመት ምሥረታ ላይ በቀለማት የቴሌቪዥን መዝናኛ ላይ የስቱዲዮ እንግዳ ሆኖ በቀረበበት ወቅት ያነሳው አንዱ ሀሳብ የተቋሙ ሥራ ባህልን ይመለከታል።
እንደሚታወቀው ከበረሀ ጀምሮ የነበረ የሬድዮ ጣቢያ እንደመሆኑ ቀዳሚው የሥራ ሀይል በትግል ሜዳ ላይ የነበረው ነው። ታጋዩ በአኗኗሩ የሥራ ሰዓትም ሆነ ደሞዝ የሚያውቅ የንግግር ልምዱም ፊትለፊት ቁጣም ጭምር የተቀላቀለበት የሚመስል እና ሲወጣ ግን አብሮ ሻይ የሚጠጣ ቂምና በቀልን የማያውቅ የነበረ ሲሆን ከዚህ የሰው ሀይል ላይ ተጨማሪ ሆኖ የገባው ሲቪል ደግሞ ይሄንን ባህል ጨርሶ የማያውቅ በአስተዳደራዊ አሰራር የሚመራና መደበኛ የሥራ ሰዓትን የሚጠቀም ቁጭ ብሎ መነጋገር የሚባለውን ነገር የማያውቅ በመሆኑ ሁለት የተለያየ ባህልን በማጣመር ወደ አንድነት ማምጣት ይጠይቅ ነበር። በመሆኑም የጊዜው አመራሮች አስተዳደራዊ ማንዋልን በመዘርጋት ቤቱ መርህ እንዲኖረው ቢደረግም ግን ደግሞ ታጋዩ የለመደው የመነጋገር ባህል ግን ቀጣይ ስራን ለማስተካከል ጠቃሚ ነውና ይሄንን ለማስቀጠል የማለዳ ብሪፍ ተጀመረ። የሥራ ሰዓት በሚል በትግል ሜዳ የነበረው ሰው ከለመደው አኗኗር ውጪ እንዳይታሰር በማለትም ጋዜጠኛው የሰዓት ፊርማ ከሚቀመጥለት ይልቅ ይዞት የሚመጣው ጠቃሚ ሀሳብ ላይ ትኩረት ማድረጉ ተመረጠ፡፡ ስለዚህም ወጥቶ የሚቃርመውን ጠቃሚ ሀሳብ እያመጣ ቤቱን ለማሳደግ ሁሉም በየፊናው ይለፋ ነበር፡፡ ውጤቱም በአንድ ሰው ጥረት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ድምር የመጣ ውጤት መሆኑን ያረጋግጣሉ።
ግዜው ላይ ጠንካራ የቦርድ አመራር መኖሩ ሌላው በጎ ነገር ሲሆን አዳዲስ የሰው ሀይል በመጨመር፣ የአሰራር ማኑዋሎችን በመስራት፣ ደካማና ጠንካራ ጎንን በመለየት ክፍተቱን ለመድፈን አብሮን ያለው የትኛው የህብረተሰብ ክፍል ነው የሚለውን ለማጥራት የጥናት ስራ በመሥራት አሰራሮችን ለማሻሻል ጥረት ተደርጓል ፡፡ይህም እርምጃውን እንዲጨምር ምክንያት ሆኖለት ነበር።
ሰው ላይ የተለየ ትኩረት ይሰጥ እንደነበር የተናገረው ሙልጌታ አንድ ሠራተኛ በሥነምግባር ምክንያት ሳባረር ቤተሰቡ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ሚስትን ወይም ልጅን አምጥተን እስከመቅጠር እና የቤተሰቡ ኑሮ እንዲቀጥል ማድረጋችን የዚሁ ማሳያ ነው ብሏል። በዚህ የቅጥር ሒደት የቤተሰቡ አባል ሙያው ስላለው ብቻ ሳይሆን ባለው አቅም ከፅዳት ጀምሮ በሚችለው እንዲሠራ ነው ሁኔታው የሚመቻችለት።
በፋና ውስጥ ሀሳብ ያለው ሰው ትልቅ ዋጋ ይሰጠው ነበር። ሁሉም በነፃነት የሚያስበውን እንዲያቀርብ ይበረታታል። እቅድም ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ ከጋዜጠኛው ወደ አመራሩ የሚቀርብ መሆኑ ጋዜጠኛው ሀሳቡን እንዲያንሸራሽር እድል ፈጥሮለታል። የሚሰሩ የነበሩት ዝግጅቶች በ3 መልኩ የተዋቀሩ ነበሩ ማለትም ኢንፎርማቲቭ፣ ኤዱኬሽን እና ኢንተርቴይመንት በሚል።
በዚህ መሠረት ህዝቡ ውስጥ የዘለቁ ትላልቅ ፎርማቶችን ይዞ መቅረብ ተችሏል። እነ ዳሰሳ፣ህዝቡ ምን ይላል እና በዜና ደግሞ በአለምነህ ይቀርብ የነበረው ጥበብ የታከለበት የግነት ዜና ተደማምሮ ፋናን ሊያገነው ችሏል። ፋና የሚለው በአንድ ቃል ሁለት ቋንቋን የሚገልፅ ሆኖ የቀረበው ከሰራተኛው በተዋጣ ሀሳብ ሲሆን ብሩክ ከበደ ይዞት የቀረበው ፋና የሚለው ቃል ብርሀንን እና መንገድን የሚገልፅ በመሆኑ አፅድቀነው የተቋሙ መጠሪያ ሊሆን በቅቷል በሚል ሙሉጌታ ጊዜውን አስታውሷል።
የፋናን ቴክኖሎጂ አቅሙ በሚደንቅ ፍጥነት እያደገ መምጣቱን ያስረዳው ሙሉጌታ በግዜው ጋዜጠኞች የጠዋት ዜና ለማቅረብ ለሊት 8 ሰዓት ቢሮ ገብተው መረጃዎችን ማፈላለግ ይጠበቅባቸው ነበር ያለው።
ፋና እራሱን በራሱ እየደጎመ የሚሰራ መሆኑንም በማንሳት በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ 80 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከሜጋ አሳታሚ ድርጅት ነበር የተበደሩት ከዛም በተለያየ ሁኔታ ስቴት ኦዲየንስ የሚሉትን የመድረክና ስፖንሰር የሚያስገኙ ስራዎች ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን ሰርተው ተቋሙን በገንዘብ ለመደገፍ ችለዋል። እሩቅ እያሰበ የራሱን ህንፃ ገንብቶ አቅሙን አግዝፎ እንዲገኝም ይህ አሰራር መሰረት ጥሎለት አልፏል።
ፋና ትምህርት ቤት ነው ተብሎ ሲነገር ይሰማል ምክንያቱ ደግሞ በሙያም ምንም ልምድ ያልነበራቸው ሰዎች ገብተው ዕውቀታቸውን አካብተው የሚወጡበት ቤት በመሆኑ ነው። በየጊዜው የነበሩ አመራሮች ይሄንን በኩራት ይናገሩታል አቶ ሙልጌታ ደግሞ ሠራተኛው በእውቀትም እራሱን ማሳደግ ካልቻለና የትምህርት ደረጃውን ካላሳደገ እርከን በመከልከል ጫና ልንፈጥርበት እንዲማርም ልናበረታታው እንጥር ነበር ብለው ያስታውሳሉ።
አዳዲስ የሚገቡትን ደግሞ በጠንካራ የማጣራት ሥራ ጥራቱን የጠበቀ ሙያተኛ እንዲገኝ ይሠራ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመፃፍ ችሎታ ያላቸው የተለያዩ ሙያተኞች ለምሳሌ ኢኮኖሚስት የሆኑ ወይም የህግ ባለሙያዎች፣ የጤና ባለሙያና መሰል ሙያተኛን በመፈለግ በአንድ ጉዳይ ስፔሻላይዜድ ያደረጉ ጋዜጠኞች እንዲኖሩት ይሠራ ነበር።
ሙሉጌታ በትምህርት እራሱን በማሳደግ ከእንግሊዝ ሀገር ተምሮ ማስተርሱን ለመቀበል የበቃ ሲሆን በመሪነት ብቃቱ የሚያውቁት ሁሉ የሚመሰክሩለት መሪ ነበር። ከሚድያው አለም ወጥተው በኮንስትራክሽን አሶሴሽን ውስጥ በመሥራት ላይ ነበር። ሚድያዎች የሁሉንም ሀሳብ በሚዛናዊነት በአንድ መድረክ እያቀረቡ የማወያየትና ሀሳብ ገዢ ሆኖ እንዲወጣ መስራት ላይ ሊተጉ እንደሚገባቸው ሙሉጌታ በአፅንኦት መምከሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
ሙሉጌታ ገሰሰ በወዳጆቹ አንደበት
ብሩክ ከበደ (የኤንቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ )
ሙሉጌታን ከፋና በፊት ነው የማውቀው። ጓደኛዬና ሚስጥረኛዬ የልብ ወዳጅ ገበና ከታች ነው ሙሉጌታ። ከአለቅነቱ በላይ ወዳጅነቱ ይበልጣል። የፋና ምሥረታ ፕሮጀክት ላይ በ1986 ዓ.ም ነበር የሚያገኘን። መስፍን ዓለማየሁ የሺጥላ ኮከብን የመሰሉ ደራሲዎች ጓደኞቹ ነበሩ። ዘከሪያ መሀመድ መስፍን አሸብርና እኔን ያገኘን ነበር። ሁለገብ፣ ተግባቢ፣ቤተሰባዊነትን መፍጠር የሚችል፣ ሁሉም ሰው ባለው አቅም ልክ መሥራት እንዲችል ዕድል የሚፈጥር፣ ተቋማዊ ባህልን መፍጠር የቻለ ሰው ነው ሙሉጌታ ማለት። እያደረ ሁሉ የሚሠራ ባለሙያ ነው። የሥራ ቦታው ቢሮው ብቻ አልነበረም፤ ተቋማዊ የእኔነት ስሜትን በመፍጠር የማይናጋ መሰረት የጣለውም በዚሁ ምክንያት ነው። የሰብአዊነት ስብእናውም ላቅ ያለ ነው። ፋና ሲመሰረት 24 ሰዓት የሚያሰራን ሰው ነው። ፋና የሚለውን ስም ሳወጣ ወዲያው ነው የቀለባት "እኔ እንኳን አላሰብኩትም" በሚል ነበር
የተቀበለኝ። እድል ይሰጣል እንድንፈጥር እንድናቅድ በእኔነት አቅማችንን እንድናወጣ ያደረገን ነው ሙሉጌታ። ወግ አጥባቂ ሰው ሳይሆን በተሳሳተ መንገድ ሰዎች የሚረዱት ነበሩ።
...በአለቃነቱ አብረውት የሚሠሩትን ያደንቃል ያበረታታል። በአጠገቡ ሆነው በአመለካከትም ሆነ በቅናት ለውድቀቱ የማይመለሱለት ሰዎች መኖራቸውን እያወቀም ቢሆን አብሮ የመኖር አቅም የነበረው ሰው መሆኑን አደንቃለሁ። እኔ በግሌ ከእርሱ ብዙ ተምሬያለሁ "ሰውን በአዎንታዊነት አሳትፈው" የሚለውን የሥራ መርሁን አደንቅለታለሁ ተምሬበታለሁም። ሙሉጌታ በባህሪውም አወንታዊ ነው።የሰዎችን ተሰጥዖ ማውጣትን ያውቅበታል፡፡የኢትዮጵያ ሚድያ ካጣቻቸው ሰዎች አንዱ ሙልጌታ ገሠሠ ነው፡፡
ዮሀንስ ገብረ መድህን
ሙሉጌታ ከበረሀ ሬድዮ ጣቢያው ጀምሮ እስከ ፋና ድረስ አለቃዬ ነበረ። በቀደመው ጊዜ ሙሉጌታ የኢህአዴግ ሬድዮ ውስጥ በ1982 ስገባ ከተቀበሉኝ መካከል አንዱ ነው። ሙሉጌታ በአጋርፋ እርሻ ኮሌጅ ሲሠራ እንደነበር አውቃለሁ። በመቀሌ ወህኒ ቤት ውስጥ ደግሞ ለእስር ተዳርጎ በአጋዚ ኦፕሬሽን ነበር የተፈታው። ሙሉጌታ ገሰሰ በበሀሪው አቀራራቢና ተግባቢ ሰው ነው። ከሚድያ ከወጣ በኋላ በራሱ የሥራ መስመር ውስጥ ገብቶ በንግድና በኢንደስትሪ ትርኢቶችን በኤግዝቢሽን ያካሂድ ነበር።
ኦሀድ ቤንያሚን
ሙሉጌታን የማውቀው በ1988 ሰላምና መቻቻል ኮንፍረንስ ሬድዮ ፋና ሲያዘጋጅ ነበር። በጣም ተግባቢ ቀጥተኛና ቀለል ያለ ስብዕና ያለው ሰው ነው። ፋና ስገባ ከእርሱ ጋር ተነጋግሬና ተደራድሬ ነው የገባሁት።እንደመሪ ከፍተኛ የስሜት ብልህነት ያለው፣ ጥሩ ልብ ያለው ሰው በመሆኑ በቁጣ እንኳን ቢናገረን የማንከፋበት፣ የማይታለፍ መስመር ያለው ብሎም በውሳኔ ሰጪነቱ የሚመሰከርለት መሪ ነው። ያኔ ፋና ሲመሰረት ሲቪሉንና ታጋዩ ሰውን በጋራ አዋህዶ በአንድ አይነት ባህል ሚዛን አስጠብቆ የቆየ ፣ ፋናን ማቆም የቻለ ጎበዝ መሪ ነበር።
ሙልጌታ በእውቀቱ በከተሜነት አስተሳሰቡ ነገሮችን የሚረዳበት መንገድና ፕሮፌሽናልን በማስቀደም ወደ ኋላ የሚሉትን በመግራት የሚታወቅ መሪ ነው። ሙሉጌታ ቢጋጭም እንኳን ማንም ቂም አይዝበትም ምክንያቱም ቁጣው ማንነትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን ሥራው ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰጠው ትችት በመሆኑ የሚናገረው ሰው ራሱ የሙሉጌታ ንግግር ምክንያታዊ መሆኑን ስለሚረዳ ቅሬታ በመሀል ሳይፈጠር ነበር ሥራው የሚሰራው። ሙሉጌታ እጅግ በሳል ሰው ነው። ከማንኛውም ሰው ጋር ሚዛኑን ጠብቆ መኖር የሚችል ነው።
ሙሉጌታ ከባለቤቱ አኸዛ የሦስት ልጆች አባት ሲሆን 'ሚዘር' የተባለችው የመጀመሪያ ልጁ በሚወደው በቀደምት የህወሀት ታጋይ ስም ነው የሰየማት።

Comments