Logo
Getu Temesgen
ኮረኔል ደረስ እንዳለ ~ የብዙዬ ልጅ !
#ethiopia | ሀገርን መውደድ በኃሳብና ቃላት ድርደራ ብቻ ፈፅሞ አይገልፅም ሀገርን የእውነት ከልብ መውደድ ድርጊትን እና ሆኖ መገኘትን ይፈልጋል ዳሩ በወታደር ቤት ለወታደር።

አንደበተ ርዕቱ ፤ ማሰብ ኃይሉ ፤ አዕምሮው ለሕዝቡ ጥቅል የፍቅር ስሜቱን የሚያስብ ለወገኑ ወዶገብ ሀገሩ ከአንደበቱ የማትጠፋው የአየር ላይ ተጓዡ ~ ኮረኔል ደረስ እንዳለ።

ከታሪክና ከመልካሙ ባሕል የሚነጠል ከወግና ልማዱ ጋር ጣውንት ማይሆን ኸያው ወገኑን ፈፅሞ የማይረሳ ጎልማሳ።

ሥመ ገናናው ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ የቀረጸው እንከን አልባው ሥርዓት “Utopia” ተፈፃሚ ቢሆን ዳሩ ዓለም እንከን አልባ ትሆናለች የሚል ግምት ፤ አይኖረኝም ብሎናል በምጥቀቱ።

በሥነ- ማሕበረሰብ ትስስር ውስጥ ራስን በቅጡ መረዳት ዳሩ ለምን ዓላማ ወደዚች ዓለም ፤ እንደ-መጣን መገንዘብ ጠንካራና ደካማ ጎንህን እና እምነትህን መፈተሽ ያለባችሁ ሲል ከዓመታት በፊት አንድ የሰፈራችን የሰርግ ድግስ ላይ ምክሩን ሲለግሥ አደመድጥነው በሱፍ ልብሱ ኮረኔልን።

ሁኔታ መገምገም ፤ ወደፊት ልታሳካው የምትፈልገውን ነገር አስቦ መድረስ ሕልማች ማግኘትን መገንዘብን እኔና ጓደኛዬ እታለማው ታፈሰ ( ሎክ ) አድምተን ኮረኔልን አደመጥነው።

ኮረኔል ደረስ የሚወዳት ሀገሩን ለሥስት አሥርት ዓመታት ገደማ ለተጠጋ ጊዜ በታማኝነት በሞያ እያገለገለ ይገኛል።

መነኩሴ ወላጅ እናቱን ኮረኔል ሁሌም በብዙ እንደሚወዳት ይናገራል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሥርዓተ ቤተ- ክርስቲያን ምንኩሥና ከእምነት የተመረጡ እጅግ ጥቂቶች የሚኖሩበት ክርስቲያናዊ - የሕይወት መንገድ ፤ እንደ ሆነ ይታመናል።

ኮረኔል ደረስ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተቋም በቅርቡ “አንበሶቹ ሰማይ ኢትዮጵያ” መሪ ቃል ላይ ባቀረበው የአየር ትርኢት ላይ ብቃቱን አሥመስክሯል። የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ከሆኑት ከሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ዘንድ የእውቅና ስጦታ እና ምሥጋና ለኮረኔል ደረስ እንዳለ ተችሮታል።

ኮረኔል ደረስ እንዳለ ለአያሌ ወጣቶቻችን መልካም አርአያ መሆን የሚችል ሀገሩን ለ 27 ዓመታት ያለ መታከት አቀበት ቁልቁለት እየወጣ የተሰጠውን ግዳጁ በጀግንነት እየፈፀመ በታማኝነት እሚያገለግል ሥመ- ጥር የጦር መኮንን ነው።

የብዙነሽ ሜይዴይ ልጅ ረጅም እድሜ ከጤና ተመኘውልክ !

ጌታመሳይ ሙሉጌታ

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.