2 months ago
ከወንበር በላይ ሀገር !
የምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ሀገራዊ ምርጫ ውጤት ይፋ ውጤት የሀገሪቱን የፖለቲካ ካርታ ግልጽ አድርጎታል። ገዥው ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን ወንበር ወስዷል፤ ሀገራችንም ወደ ሌላ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ተሻግራለች።
ኢዜማ የለፋውን እና የደከመበትን ያህል ባይሆንም 86 ወንበሮችን አሸንፏል (13ቱ በፌደራል ፓርላማ፣ 73ቱ በክልል ምክር ቤቶች) በዚህ ውጤቱ ኢዜማ በፓርላማው ውስጥ ዋነኛው ተፎካካሪና አማራጭ ድምፅ ሆኖ ወጥቷል። ለመሆኑ ይህ ውጤት የለፋንለትና የተመኘነው ያህል ነው? ፈጽሞ አይደለም። ታዲያ በቀላሉ የምናጣጥለው እና ፋይዳቢስ የሚባልስ ነው? በፍጹም!
ፖለቲካ እንደ ሎተሪ ዕጣ በአንድ ጀምበር ሁሉንም እድል ጠራርጎ የሚወሰድበት ወይንም በተቃራኒው ሁሉንም ተበልቶ በባዶ እጅ እየቆዘሙ አንገት ደፍቶ ወደቤት የሚኬድበት የዕድል ጨዋታ አይደለም። ለኢዜማ 86 ወንበሮች በማሸነፍ፣ ጠንካራ መዋቅርን ለመሥራት እና ቀጣዩ ምርጫ እስኪደርስ መላውን አባላት በንቃት የሚያሳትፍ በርካታ የቤት ሥራ ይዞ መውጣትም በፖለቲካ ዐይን ተጨማሪ የዴሞክራሲ እርምጃ ነው።
ከእኛ ጋር ተፎካካሪ የነበሩ፤ የሕዝብ አመኔታ እና ድምጽ ሲያጡ እና እንዳለሙት ውጤት ሳይቀናቸው ሲቀር፣ የሌላውን ድካምና ውጤት ለማጣጣል እና ስም ለመለጠፍ የሚሮጡትን "አንዳንድ የተቃውሞ ነዋሪዎች" ስናይ... "ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል" ከሚለው ነባር የሀገራችን ብሂል የተሻለ ምን ማስተማሪያ ሊገኝላቸው ይችላል?
ሌሎች ደግሞ አሉ። ዓላማቸው ከዓላማችን፤ መንገዳቸውም ከመንገዳችን ስላልገጠመ ብቻ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጥደው ሲረግሙን ውለው ሲረግሙን በማደራቸው ፖለቲካ የተነተኑ የሚመስላቸው የቁራ ጯሂዎች! የተለመደው ቁርጥ ያለ መልሳቸን “ያዋጣል በምትሉት መንገድ ሂዱ! የእኛን መንገድ ለእኛ ተዉልን” የሚል ይሆናል። ዳር ቆመው ሰባራ ሳንቲም ሳያዋጡ ተዓምር ለሚናፍቁ የሰነፍ ቅምጥሎችና ‘የሶሻል ሚዲያ አርበኞች’ መልካም የምኞት ጊዜ ይሁንላቸው ከማለት ውጪስ ምን ይባላል?
እኛ ኢዜማውያን ግን ዲሞክራሲ የሚገነባው እጅጌን ሰብስቦ እና ቆፍጠን ብሎ መሬት ላይ ሥራ በመሥራት መሆኑን ስለምናምን ከባለፈው የምርጫ ተሳትፎአችን በብዙ እጥፍ የጨመረውን ውጤት በጸጋ ተቀብለን እና የሕዝብ ድምጽ አክብረን በጨዋነት እና በስለጠነ ዘመናዊ ፖለቲካ ተሳትፎ ወደፊት እንራመዳለን። በውድድር ውስጥ ማሸነፍን ብቻ ሳይሆን፣ ተሸንፎም ትልቁን ሀገራዊ ስዕል ማየት መቻል የፖለቲካ ብስለት መለኪያ ነውና።
አሁን የምርጫው አጀንዳ ከሞላ ጎደል ተጠናቅቋል፤ አሸናፊዎች ወደየምክር ቤቶቻቸው፤ የተቀረነውም ወደየ እለታዊ ተግባራችን እንመለሳለን። ሀገርን ማገልገል በምክር ቤቶች ተሳትፎ ብቻ አይወሰንም። የሀገር ግንባታ በምርምር ማዕከላት፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በሙያ ማኅበራት፤ በሲቪክ መድረኮች፣ በልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ከገልግሎቶች ውስጥ ይቀጥላል።
… እንዲያውም ሁሉም ሰው በድንገት የሕገ-መንግስት ተንታኝ፣ የጂኦፖለቲካው ነብይ፣ የፌደራሊዝም ሐዋርያ በሚሆንበት በዚያ ድራማዊ የቡና ጠረጴዛ ውይይት ውስጥ ጭምር ሕይወት እንደወትሮው ይቀጥላል።
እስካሁን የተጓዝንበትን ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም የፖለቲካ ተሳትፎን በኩራት እያከበርን፤ አሁን ደግሞ የፓርቲ ማሊያችንን አውልቀን፣ የሙያ ጃኬታችንን ለብሰን ወደ ዋናው ሥራችን ብንመለስ ምን ይለናል? የሽሚዞቻችን እጅጌ ስብስበን "ዳዬ ወደሥራ!" ብለናል።
እግረመንገድም ከአድካሚው እና እንደ ልቅሶ ቤት አግዳሚ ወንበር ከሊቅ እስከ ደቂቅ አኩል ተኮልኩሎ ከፊሉ ሲራገም ከፊሉ ሲመርቅ ከሚውልበት የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክም እስከውዲያኛውም ባይሆንም እረፍት መውጣት ተገቢ አይደለም ትላላቸሁ?
መልክም ጊዜ !
(አርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን የኢዜማ ከፍተኛ አመራር)
#ኢትዮጵያ #ኢዜማ #ሀገርግንባታ #ምርጫ2018 #ዲሞክራሲ

5 months ago
🇪🇹 "እንጠብቅሻለን አለብን አደራ"
የመገናኛ ብዙኃን ሚና በብሔራዊ ጥቅም ላይ
#ethiopia | የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በመገናኛ ብዙኃን ሚና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ "እንጠብቅሻለን አለብን አደራ" የሚለው መርህ የሚዲያ ተቋማት ዋነኛ መመሪያ ሊሆን እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
መገናኛ ብዙኃን መረጃ ከመስጠት ባለፈ የሀገርን የዲፕሎማሲ አቅም የመገንባትና ብሔራዊ ጥቅምን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማስተዋወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል።
የሀገርን ገጽታ የሚያጠለሹ የውስጥና የውጭ ተጽዕኖዎችን በሙያዊ ብቃት መመከትና የኢትዮጵያን እውነተኛ ታሪክ ለዓለም ማሳወቅ እንደሚገባ ተገልጿል።
የጋራ እሴቶችን ማጎልበት፦ የሕዝብን የጋራ እሴቶች በማጠናከር ለሀገራዊ ብልጽግና በትኩረት መሥራት የሚዲያው ድርሻ መሆኑ ተጠቅሷል።
ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ)፦
"የሀገርን ገጽታ የሚያጠለሹ ተጽዕኖዎችን በመመከት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በአለም አቀፍ መድረክ ማስከበር የሚዲያው ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።"
ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ (የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር)፦"መገናኛ ብዙሃን ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ ለሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው።"
"እንጠብቅሻለን አለብን አደራ" ማለት ምን ማለት ነው?
ይህ መርህ መገናኛ ብዙኃን ከዘገባ ባለፈ ለሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ዘብ የመቆም የሞራልና የሙያ ግዴታ እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው። ይህም፦ ሀገራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ መረጃዎችን መከላከል፤ በዓለም አቀፍ መድረክ የሀገርን ተሰሚነት ማሳደግ፤ ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅርና የባለቤትነት ስሜት ማጎልበትን ያጠቃልላል።
#ኢትዮጵያ #መገናኛብዙኃን #ብሔራዊጥቅም #ዳንኤልክብረት #የሀገርግንባታ #ethiopia #mediaethics #nationalinterest #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments