1 year ago
የተወዳጁ የሆሊዉድ ተዋናይ Vin Diesel እና የፍቅረኛዉ አስደናቂ የፍቅር ታሪክ
#ethiopia | ከሶስት አመታት አብሮነት በኋላ አለመግባባቶች በተደጋጋሚ ሲፈጠሩ፤ መለያየት ግድ ሲሆን ቪን ዲዝል ፍቅረኛዉን ከቤቱ እንድትወጣ ከማድረግ ይልቅ ቁልፉን ሰጥቷት በተንከባካቢ እና እሷን በማይረብሽ ርቀት ተከራይቶ መኖሩን ቀጠለ።
ማንም በማይሰማበት ሁኔታ የኢንተርኔት፣ መብራት እና የስልክ ክፍያዎች ወደሱ እንዲመጡ በማድረግ ይከፍልላታል። ስለመለያየታቸው ለማንም ሳያሰዉቅ ህይወታቸዉን ቀጠሉ።
ታዲያ ፍቅረኛዉ ጋር ከተለያዩ ከ6 አመታት በኋላ ከግብይት መልስ ወደ ቤቷ ስትጓዝ የመኪና አደጋ አጋጠማት። ቪን ዲዝል ከአደጋዉ በኋላ አልተለያትም ህይወቷን ለማዳን ደሙን ለገሰላት እና እስክታገግም ከጎኗ ቆየ። ከዚህ በኋላ ነበር ከሱ ተለይታ ላለመኖር የወሰነችዉ። አሁን ጥንዶቹ አብረው ይኖራሉ።
#mn_addis

ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፋቸውን ገለጹ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ ዩክሬይንን በተመለከተ ለምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ” እንደሚያደርጉ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ መግለጫ የተሰጠው የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሰሜን ኮሪያን በጎበኙበት ወቅት ነው።
ኪም ከላቭሮቭ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥምረት አጽንኦት ሰጥተው፣ ሀገራቸው “የዩክሬይንን ቀውስ መንስኤ ለመፍታት የሩሲያ አመራር የወሰዳቸውን እርምጃዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምትደግፍና እንደምታበረታታ” ገልጸዋል። ይህ የሰሜን ኮሪያ ድጋፍ ባለፈው ዓመት በተፈረመው የጋራ መከላከያ ስምምነት መሰረት መሆኑን የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የሰርጌ ላቭሮቭ ጉብኝት፣ በሩሲያ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል የተካሄዱት ተከታታይ ከፍተኛ ደረጃ ልውውጦች አካል ነው። ይህ ደግሞ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትስስር እየጠነከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። ሁለቱም ሀገራት በአለም አቀፍ ማዕቀቦች የተጣለባቸው ሲሆን፣ በዩክሬይን ባለው ቀጣይ ግጭት ምክንያት ጥምረታቸው ይበልጥ ተጠናክሯል።
Addis_News

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም በስንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል?
#ethiopia | ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኝነቱን ደረጃ እንዳስጠበቀ ቀጥሏል
ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የአንደኝነት ደረጃ ይዟል
6 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ተካተዋል
የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ፣ ለ21,462 የትምህርት ተቋማት ደረጃ የሰጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን "ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ አካቷል። በዚህ ዝርዝር ከተካተቱት ውስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል፡፡
ማዕከሉ ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
የትምህርት ጥራት (25%)
ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።
የአሜሪካ ዝነኛ የትምህርት ተቋም የሆነው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቆ የቀጠለ ሲሆን፤ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋምና የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ፣ ፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ዬል ዩኒቨርሲቲና ቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከስድስተኛ አስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን፤ ሁሉም የአሜሪካ የግል የትምህርት ተቋማት ናቸው።
በሌላ በኩል፤ ቻይና 346 ዩኒቨርሲቲዎቿ በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ የተካተተላት ሲሆን፤ ብዛት ያላቸው ተቋማት በማካታት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአለም 808ኛ
ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ፣ ከአለም 1607ኛ
ጅማ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሦስተኛ፣ ከአለም 1701ኛ
መቐሌዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አራተኛ፣ ከአለም 1757ኛ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አምስተኛ፣ ከአለም 1803ኛ
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስድስተኛ፣ ከአለም 1903ኛ
የትምህርት መረጃ #addis_admas

ሚስታቸውን የነዳጅ ማደያ ቦታ ረስተዋት ከ300 መቶ ኪሎ ሜትር በኃላ ያሳታወሷት ባል
ፈረንሳዊ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው። ባለቤታቸውን በፈጣን ጎዳና ላይ ባለ አንድ የነዳጅ ማደያ ውስጥ እንደረሷቸው ደግሞም ማስታወስ እንዳልቻሉ አስገራሚው የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ይጠቁማል።
አዛወንቱ ሚስታቸውን ጥለው መክነፋቸውን የተረዱት ግን ከተነሱበት ማደያ 300 ኪሎ ሜትር ከራቁ በኃላ ነበር። በዚህም እርዳታን ፍለጋ ፖሊስ ዘንድ የእርዳታ ጥሪ ያደርጋሉ።
ነገሩ እንዲህ ነው። የፓሪስ ነዋሪ አዛውንት ጁላይ 5 ከባለቤታቸውና እና ሴት ልጃቸው ጋር ለእረፍት ወደ ሞሮኮ ያቀናሉ። በመንገዳቸውም ነዳጅ ለመቅዳት በርካታ ማደያዎች ላይ ይቆማሉ። ይሁንና አንዱ ማደያ በቆሙበት ጊዜ ግን አንድ የተለየ ክስተት ይፈጠራል።
ስማቸው በሚዲያ ያልተገለፀው ግለሰብ ንጋት 10:30 ላይ ነዳቸውን ሞልተው በጨረሱበት ሰዓት ሚስታቸውን እዛው ትተዋቸው መሄዳቸውን ሳያስታውሱ ወደፊት ይገሰግሳሉ።
ነገር ግን ባለቤታቸውን መርሳታቸው የተረዱት 300 ኪሎ ሜትር ርቀው ከተጓዙ በኃላ ነበር። አዛውንቱ ባለቤታቸውን የነዳጅ ማደያ ውስጥ እንደረሷቸው ሲረዱ እርዳታ ፍለጋ በፍጥነት ለእርዳታ የድንገተኛ ጥሪ ያደርጋሉ።
ሚስታቸውን ማደያ ቦታ መርሳታቸው፣ 300 ከራቁ በኃላ ማስታወሳቻው ጉድ በል ሊያስብል ይችላል፣ ነገር ግን የበለጠ አጃኢብ የሚያስብለው ሚስታቸውን የትኛው የነዳጅ ማደያ እንደረሷቸው አለማስታወሳቸው ነው።
ምን ይባላል እንግዲህ?

Sponsored by
Surafel
1 year ago
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) መጥፎ ገጽታው!
#ethiopia | በህክምና ላይ የሚሰሩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ፕሮግራሞች የሰዎችን ቀለም ወይም ዘር ሲያውቁ የተሳሳተ ግንዛቤ እየያዙ መሆናቸው ጥናት አመላክቷል።
በNPJ የህክምና ጆርናል ላይ የወጣው ምርምር እንደሚያሳየው ፕሮግራሞቹ የአዕምሮ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች አፍሪካ አሜሪካውያን መሆናቸውን ሲያውቁ ይሰጡት የነበረው የህክምና ምክር ተቀይሯል።
ፕሮግራሙ፥ ታማሚዎችን ምን ያህል መለየት እንደሚችሉ እና የህክምና ምክር መስጠት እንደሚችሉ ሲሞከር ይህ ነገር ማጋጠሙ ነው የተነገረው።
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፕሮግራሞቹ በመጀመሪያ ምንም የዘሩ ቀለሙ ሳይነገራቸው፣ በሁለተኛው አፍሪካ አሜሪካዊ እንደሆነ ተነግሯቸው በሶስተኛው ደግሞ በስሙ ላይ ተመስርተው ዘሩን እንዲያውቁ ተደርጎ ሙከራ ሲደረግባቸው ለየት ያለ ነገር ማሳየታቸው ተነግሯል።
ፕርግራሞቹ ታካሚው አፍሪካ አሜሪካዊ መሆኑን ሲያውቁ የተለያየ ምክር የሰጡ ሲሆን ሁለት ፕሮግራሞች ደግሞ ምንም አይነት ምክር እና እገዛ ለማድረግ አልፈለጉም ተብሏል።
አንዳንዶቹ ፕሮግራሞች ጭንቀት ውስጥ ላሉ የአፍሪካ አሜሪካውያን ታካሚዎች የአልኮል መጠን እንዲቀንሱ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው መክረዋል።
ተመራማሪዎች ፕሮግራሞቹ በተሰጣቸው መረጃ መሰረት እንደሚመልሱ በመግለፅ መረጃ በሚሰጣቸው ወቅት ጥንቃቄ ካልተደረገ ከባድ ጥፋትን እንደሚያስከትሉ አስጠንቅቀዋል። #tm

ጀርመን እና ቢራ
#ethiopia | ጀርመን በቢራ ምርቶቿ የምትታወቅ ሲሆን፣ የጀርመን ቢራ የአልኮል መጠኑ በ4.7 በመቶ እና 5.4 በመቶ መካከል ነው።
በዩናይትድ ኪንግደም አማካዩ የቢራ የአልኮል መጠን 4.4 በመቶ ነው።
ጀርመን በቢራ ምርት እና ዜጎቿም በቢራ ወዳጅነታቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ በየዓመቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ቢራ በአገሪቱ ውስጥ ይጠመቃል።
በተለያዩ ጊዜያትም የቢራ ፌስቲቫሎችን በማካሄድ አገሪቱ ትታወቃለች። Pilsener የተሰኘው ቢራ የጀርመን ተወዳጅ ቢራ ነው።
#selamshowbiz

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን አረፈ
#fastmereja I በዋሽንግተን ግዛት፣ ሲያትል ከተማ መቀመጫውን ያደረገው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን አረፈ። በትግራይ ውቅሮ ከተማ በ1963 ዓ.ም የተወለደው ጋዚጠኛው ሐምሌ 2 ቀን 2017 ጠዋት ነው ያረፈው።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኘው ታደሰ ሚዛን በኋላም በዩናይትድ ስቴትስ የሦስተኛ ዲግሪ አግኝቷል።
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጋዜጠኝነት እስከ የዜናና ወቅታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተርነት ያገለገለው ታደሰ "የሚዲያ ዳሰሳ" በሚለው ፕሮግራሙም ይታወቅ ነበር።
የታደሰ ሚዛን የቀብር ሥነ-ስርዓት በሲያትል፣ ዋሽንግተን እንደሚፈጸም ተገልጿል።
ነፍስ ይማር!
via ክብሮም ሙሉጌታ

🇰🇷💵 😲💍👶
ደቡብ ኮሪያ
ለሚጋቡ ዜጎቿ ብር እየሰጠች ነው ደቡብ ኮሪያ
እባካችሁ ተጋብ እያለች ነው
ደቡብ ኮሪያ ጥንዶች እንዲጋቡ እና ልጆች እንዲወልዱ እስከ $64,000 ዶላር አቀረበች!
የቡሳን ሳሃ-ጉ ወረዳ ከምንጊዜውም ዝቅተኛ የልደት ምጣኔ ጋር ለመታገል ደፋር እርምጃ እየወሰደ ነው —
እስከ $64,000 ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በመኖሪያ ቤት ድጋፍ የፍቅር ጓደኝነት ለሚጀምሩ፣ ለሚጋቡ እና ቤተሰብ ለሚመሰርቱ ጥንዶች እያቀረበ ነው!
ምን ምን ይዟል?
* የፍቅር ጓደኝነት ድጋፍ: ለአንድ ሰው ~$367
* የሰርግ ድጋፍ: ለተጋቡ ጥንዶች ~$14,680
* የቤት ኪራይ ወይም የቤት ማስያዣ: እስከ ~$21,950 ወይም ~$586 በወር ለ 5 ዓመታት
* ልጅ መውለድ እና የጉዞ ድጋፍ:
እስከ ~$7,340 ተጨማሪ!
ይህ ሁሉ ሀገሪቱ እያጋጠማት ያለውን ከባድ የህዝብ ብዛት ችግር ለመፍታት
* ፍቅርን፣
* ትዳርን እና
* የቤተሰብ ህይወትን ለማበረታታት ከቀረበው ደፋር እቅድ አካል ነው።
እናንተስ ሀገራችን ኢትዮጵያ ገንዘብ ትሰጣላች ስትጋቡ ቢባል ታገባላችሁ ሀሳባችሁን አሳውቁን?
Seledadotio

ልዩ ምልከታ ከብሩህ ማይንድስ
#ethiopia | ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በየወሩ የሚያዘጋጀው ልዩ ምልከታ 5ኛ ዙር የኢንተርፕርነርሺፕ መርሃ ግብር በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ።
5ኛው ዓመታዊ ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘ አውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ።
የዝግጅቱ መሠረታዊ ዓላማ በኢትዮጲያ ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ውጤታማነትን ለማሻሻል በጥናትና ምርምር ውጤት ላይ በመመርኮዝ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና የአነሥተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ማነቆዎችን እና የብድር አቅርቦት ፈተናዎችን በመለየት የገበያ አውዱን ለማስፋት የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት እንደሆነ የብሩ ማይንድ ኮንስልታንት ፒኤልሲ የኔትዎርኪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት አቶ መክብብ ዘሪሁን ገልጿል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ኢንተርፕርነርሽፕ ብዙ ተለፍቷል፤ ብዙ ተወርቷል።
መንግሥት በበኩሉ ብዙ ጥረት ጥሯል፤ የግል ተቋማትም ይሞክራሉ ግን በሚፈለገው ደረጃ ሥራ መፍጠር አልተቻለም።
በሚፈለገው ደረጃ ወጣቶቻችን ወደ ሥራ እየተሠማሩ አይደለም።
ይሄ በአግባቡ ካልተፈታ ደግሞ የሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ችግርም ሊፈጥር ይችላል።
ስለዚህ እንደ አንድ ኢንተርፕርነርሽፕ ላይ እንደሚሠራ ተቋም ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በየወሩ የሚካሄድ ልዩ ምልከታ የተሠኘ የምክክር መድረክ የጀመርነው ብለዋል።
ፖሊሲ አድቮኬት ነው ምናደርገው ያሉትን ተግዳሮቶች እንዲታይ ያንን ተግዳሮት ደሞ አልፎ አድርጎ በተለይ ኤምኤሲዎች ገንዘብ ሚያገኙበትን ፋይናንስ የሚደረጉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይሄንን ፕሮግራም እንግዲህ በትልቁ ዲዛይን አድርገን የተነሳነው ሲሉ አቶ መክብብ አክሏል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ፕሮግራም ኤምኤሲዎች አክሰስ ቱ ፋይናንስ እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት በሚለው ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን በውይይቱ ላይ ፋይናንሻል ተቋማት፣ የመንግስት አካላት በዚህ ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
በኤግዚቢሽኑ 40 ተሳታፊዎች ያሉ ሲሆን ከ4000 ሰው በላይ ጎብኚዎች ይጠበቃሉ።
መርሀግብሩ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናቶች የሚቀጥል ሲሆን አውደርዕይና ሌሎችም ሁነቶች እንደሚካሄዱ ነው የተገለጸው።

ዓርብ ሰኔ 27, 2017 የሳምንቱ ምርጥ 100 ኢትዮጵያዊ ሙዚቃዎች ከየኔ ቫይብ! #yenevibe #ethiopia
___
🔔📢የኔ ቫይብ ለሁሉም ሙዚቃዎች ደረጃ የሚሰጠዉ በሳምንቱ የጨመሩትን የዩቲዩብ የተመልካች ብዛት በማወዳደር በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ብቻ ነዉ!🔔
👉 የሳምንቱን 100 ምርጥ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በ https://yenevibe.com/weekl... መመልከት ይችላሉ
___
የሳምንቱ ምርጥ 100 ሙዚቃዎች ደረጃ የሚያገኙት አውቶማቲክ እና ከሰዉ ንክኪ ነፃ በሆነ ሲስተም YouTube ላይ በሳምንቱ በጨመሩት የተመልካች ብዛት መሰረት በሚደረግ ዉድድር ነዉ።
1. Mak Ezra – Tewehade – ማክ እዝራ – ተወሓደ
8,895,520 Views | + 710,586 Views
2. 17Studio – Dagi D – YETEM BOTA / የትም ቦታ
489,516 Views | + 489,516 Views
3. Wendi Mak – 'ሰከርኩልሽ' | ወንዲ ማክ – 'Sekerekulesh'
457,392 Views | + 457,392 Views

ከ25 ሺህ በላይ ከባድና ቀላል የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ መንስኤ መለየታቸው ተነገረ
#ethiopia | በሀገር አቀፍ ደረጃ የኃይል መቆራረጡንበክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ለዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡
ተቋሙ ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበረከት ማቀዱን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚው፤ ለዚህም ንቅናቄ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ይደርጋል ብለዋል፡፡
የችግኝ ተከላ ንቅናቄው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የተቋሙ ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በዘላቂነት ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኔትዎርክ ኢንፍራስትራከቸር እና ኦፕሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር አቶ ፈሪድ አብዱሰላም ለመገናኛ ብዙሃኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃይል መቆራረጡን ወደ ዜሮ ለማምጣት የ100 ቀን ዕቅድ ተለይቶ ሲሰራ መቆየቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ በጂፒኤስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ አበባ ያሉ 152 የመካከለኛ መስመሮች እና እነዚህን መስመሮች የሚሸከሙ 59 ሺህ 48 ምሰሶዎች ላይ በተደረገ ጥልቅ ፍተሻ ከ25 ሺህ 973 ከባድና ቀላል የኃይል መቋረጥ መንስኤ የሆኑ የግኝት ነጥቦች ተለይተዋል ብለዋል፡፡
የኃይል መቋረጥ ችግሩን ለመቅረፍ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ 28 ሪጅኖች ላይ ከ250 ሺህ በላይ የግኝት ነጥቦች መገኘታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ለኃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑት ግኝቶችም ከመስመሮች ጋር የዛፎች ንክኪ ያለባቸው፣ መቀየር የሚያስፈልጋቸው ምሰሶዎች፣ ከግንባታዎችና እርስ በእርሳቸው የተቀራረቡ መሥመሮች፣ የረገቡ እና የተለያዩ የመስመር ችግር ያለባቸው ናቸው ተብሏል፡፡
ይህን ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ከተገኙ ግኝቶች መካከል እስካሁን 56 በመቶ ወይም ለ14 ሺህ 649 ያህሉ አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
በክረምቱ ወቅት የኤሌክትሪክ አደጋ ተጋላጭነት የሚጨምር በመሆኑ ህብረተሰቡ በዝናብ አልያም በነፋስ ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ከመንካት እንዲቆጠብ፤ አልያም መሰል ችግሮችን ሲመለከቱ ደግሞ በ905 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል እንዲይሳውቅ ጥሪ ቀርቧል ሲል የዘገበው ዳጉ ጆርናል ነው፡፡

ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ
#ethiopia | "ከማንችስተር ዩናይትድ ከፍተኛ ደሞዜን ስቀበል በጣም ደስተኛ ነበርኩ" አባቴም በዛ ወቅት "ልጄ ሆይ ገንዘብህን አታባክን ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ አንተ ብቻህን ትቀራለህ" አለኝ.....
"ችግር እስኪገጥመኝ ድረስ እነዚህን ቃላት አልገባኝም ነበር እና ብዙ ጓደኞቼ በየግዜው ይመጡ ነበሩ:: ጓደኞቼ ግን እኔን ለማየት እንዳልመጡ አስተውል ነበር። በችግሬ ወቅት ግን አጠገቤ የነበሩ ሰዎች የቅርብ ቤተሰቤ ብቻ ናቸው። ይህ ሕይወት ነው!!
"ሚስቴ እንኳ ልክ ከእግርኳስ ጨዋታ ስታገድ እና ዝናዬም ሲጠፋ ከእኔ ራቀች። ሚስቴ ከእኔ ጋር የነበረችው ለገንዘብ እና ለዝና ብቻ ነበር።"
ፖል ፖግባ
selamshowbiz

Comments