Logo
Getu Temesgen
ከ25 ሺህ በላይ ከባድና ቀላል የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ መንስኤ መለየታቸው ተነገረ
#ethiopia | በሀገር አቀፍ ደረጃ የኃይል መቆራረጡንበክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ለዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡

ተቋሙ ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበረከት ማቀዱን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚው፤ ለዚህም ንቅናቄ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ይደርጋል ብለዋል፡፡

የችግኝ ተከላ ንቅናቄው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የተቋሙ ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በዘላቂነት ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኔትዎርክ ኢንፍራስትራከቸር እና ኦፕሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር አቶ ፈሪድ አብዱሰላም ለመገናኛ ብዙሃኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃይል መቆራረጡን ወደ ዜሮ ለማምጣት የ100 ቀን ዕቅድ ተለይቶ ሲሰራ መቆየቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ በጂፒኤስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ አበባ ያሉ 152 የመካከለኛ መስመሮች እና እነዚህን መስመሮች የሚሸከሙ 59 ሺህ 48 ምሰሶዎች ላይ በተደረገ ጥልቅ ፍተሻ ከ25 ሺህ 973 ከባድና ቀላል የኃይል መቋረጥ መንስኤ የሆኑ የግኝት ነጥቦች ተለይተዋል ብለዋል፡፡

የኃይል መቋረጥ ችግሩን ለመቅረፍ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ 28 ሪጅኖች ላይ ከ250 ሺህ በላይ የግኝት ነጥቦች መገኘታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ለኃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑት ግኝቶችም ከመስመሮች ጋር የዛፎች ንክኪ ያለባቸው፣ መቀየር የሚያስፈልጋቸው ምሰሶዎች፣ ከግንባታዎችና እርስ በእርሳቸው የተቀራረቡ መሥመሮች፣ የረገቡ እና የተለያዩ የመስመር ችግር ያለባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ከተገኙ ግኝቶች መካከል እስካሁን 56 በመቶ ወይም ለ14 ሺህ 649 ያህሉ አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጓል፡፡

በክረምቱ ወቅት የኤሌክትሪክ አደጋ ተጋላጭነት የሚጨምር በመሆኑ ህብረተሰቡ በዝናብ አልያም በነፋስ ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ከመንካት እንዲቆጠብ፤ አልያም መሰል ችግሮችን ሲመለከቱ ደግሞ በ905 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል እንዲይሳውቅ ጥሪ ቀርቧል ሲል የዘገበው ዳጉ ጆርናል ነው፡፡

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.