Logo
Getu Temesgen
ልዩ ምልከታ ከብሩህ ማይንድስ
#ethiopia | ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በየወሩ የሚያዘጋጀው ልዩ ምልከታ 5ኛ ዙር የኢንተርፕርነርሺፕ መርሃ ግብር በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ።

5ኛው ዓመታዊ ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘ አውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ።

የዝግጅቱ መሠረታዊ ዓላማ በኢትዮጲያ ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ውጤታማነትን ለማሻሻል በጥናትና ምርምር ውጤት ላይ በመመርኮዝ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና የአነሥተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ማነቆዎችን እና የብድር አቅርቦት ፈተናዎችን በመለየት የገበያ አውዱን ለማስፋት የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት እንደሆነ የብሩ ማይንድ ኮንስልታንት ፒኤልሲ የኔትዎርኪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት አቶ መክብብ ዘሪሁን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ኢንተርፕርነርሽፕ ብዙ ተለፍቷል፤ ብዙ ተወርቷል።

መንግሥት በበኩሉ ብዙ ጥረት ጥሯል፤ የግል ተቋማትም ይሞክራሉ ግን በሚፈለገው ደረጃ ሥራ መፍጠር አልተቻለም።

በሚፈለገው ደረጃ ወጣቶቻችን ወደ ሥራ እየተሠማሩ አይደለም።

ይሄ በአግባቡ ካልተፈታ ደግሞ የሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ችግርም ሊፈጥር ይችላል።

ስለዚህ እንደ አንድ ኢንተርፕርነርሽፕ ላይ እንደሚሠራ ተቋም ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት በየወሩ የሚካሄድ ልዩ ምልከታ የተሠኘ የምክክር መድረክ የጀመርነው ብለዋል።

ፖሊሲ አድቮኬት ነው ምናደርገው ያሉትን ተግዳሮቶች እንዲታይ ያንን ተግዳሮት ደሞ አልፎ አድርጎ በተለይ ኤምኤሲዎች ገንዘብ ሚያገኙበትን ፋይናንስ የሚደረጉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይሄንን ፕሮግራም እንግዲህ በትልቁ ዲዛይን አድርገን የተነሳነው ሲሉ አቶ መክብብ አክሏል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ፕሮግራም ኤምኤሲዎች አክሰስ ቱ ፋይናንስ እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት በሚለው ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን በውይይቱ ላይ ፋይናንሻል ተቋማት፣ የመንግስት አካላት በዚህ ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

በኤግዚቢሽኑ 40 ተሳታፊዎች ያሉ ሲሆን ከ4000 ሰው በላይ ጎብኚዎች ይጠበቃሉ።

መርሀግብሩ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናቶች የሚቀጥል ሲሆን አውደርዕይና ሌሎችም ሁነቶች እንደሚካሄዱ ነው የተገለጸው።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.