Logo
SeledaPost
ለ window 10 ተጠቃሚዎች‼️
ለዊንዶዉስ /Windows/ 10 የሚቀርቡ ወሳኝ ማሻሻያዎች ከ28 ቀናት በኋላ ይቋረጣሉ::

ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከመጪዉ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላ ለዉንዶዉስ-10 ምርቶች የሚያቀርበዉን ወሳኝ የሆኑ ማሻሻያዎች እንደማያቀርብ በድጋሚ ለደንበኖቹ አሳዉቋል።

ለዊንዶውስ-10 የደህንነት ማሻሻያ ሲቋረጥ፤ ከዊንዶዉስ-10 ምርት ከዚህ ቀደም በየወሩ የሚያገኙት ደህንነትን (security)፣ የሲስተም መረጋጋትን (stability) ወይም ከአጠቃቀም ጋር ለሚፈጠሩ ክፍተቶች ጥገናዎችን ወይም ቴክኒካል ድጋፍን መስጠት ያቆማል።

በጥቅምት 4/ 2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላም የዊንዶውስ 10 ስሪት 22H2 (Home፣ Pro፣ Enterprise፣ Education፣ እና IoT Enterprise እትሞች) በሙሉ የአገልግሎታቸዉ እንደሚያበቃ ታዉቋል።

ማይክሮሶፍት እነዚህ የዊንዶዉስ-10 ምርት ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን በቀጣይነት ለማግኘት የዊንዶዉስ ምርታቸዉን ወደ ዊንዶዉስ -11 እንዲያሳድጉ መክሯል።

ነገር ግን የዊንዶዉስ-10 የደህንነት ማሻሻያዎች እንዳይቋረጥ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ለዊንዶዉስ ሆም (Home) ተጠቃሚዎች 30 የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ለኢንተርፕራይዝ ተጠቃሚዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ መሳሪያ በአመት 61 የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ወርሃዊ ዝመናዎችን ማስቀጠል እንደሚችሉ አሳዉቋል።

በመሆኑም የዊንዶዉስ-10 ተጠቃሚዎች ጊዜዉ ከማለፉ በፊት የምትጠቀሙበትን የዊንዶዉስ ምርትን ወደ ዊንዶዉስ-11 ከፍ በማድረግ የደህንነት ማሻሻያዎች መቋረጠቻዉን ተከትሎ በሳይበር ጥቃት ተገላጭነት ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ እንድትከላከሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።ayu

seledadotio
seledadotio
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.