ኤምባሲው በቱሪስት ቪዛ ሕጻናት ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያንን አሳሰበ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በቱሪስት ቪዛ ሕጻናት ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ማሳሰቢያ አውጥቷል።
በማሳሰቢያውም በርካታ የቱሪስት ቪዛ ያላቸው ወላጆች ለመውለድ ዓላማ ወደ አሜሪካ እንደሚጓዙ የገለጸ ሲሆን፤ በዛም ለሕክምና እንክብካቤ ወጪያቸው የመንግሥትን የገንዘብ ድጋፍ (ሜዲኬይድ) ይጠቀማሉ ብሏል።
እነዚህም ወጪዎች በዋናነት ወደ የአሜሪካን ግብር ከፋዮች እንደሚተላለፋ የገለጸው ኤምባሲው፤ ይህም ዜጎችን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም በዚህ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ዜጎች ለወደ ፊት የአሜሪካ ቪዛ ለማደስ በሚያመለክቱበት ወቅት፤ ቪዛቸው ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይችል አመላክቷል።
በመሆኑም በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ዜጎች፤ ይህንን ማሳሰቢያ በአጽንኦት በመመልከት የቪዛውን ትክክለኛ ዓላማ እንዲያከብሩ እና ለጉዞአቸው ተገቢውን የቪዛ አይነት እንዲጠይቁ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የአሜሪካ መንግሥት ባለፉት በርካታ ወራት የሀገሪቷን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም፤ የሌላ ሀገራት ዜጎችን እንቅስቃሴ ለማጥበቅ ያቀዱ በርካታ ተከታታይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።
ከእነዚህም ጉልህ ለውጦች መካከል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ ከመስከረም 6 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው አዲስ ሕግ አንዱ ሲሆን፤ ይህም ለአጭር ጊዜ የሚያገለግሉ የቪዛ ማመልከቻዎች አመልካች በሚኖሩበት የዜግነት ሀገር መቅረብ እንዳለባቸው የሚያስገድድ ነው።
ሌላው ደግሞ የቱሪስት ቪዛ (B-1/B-2) አመልካቾችን የተመለከተው የቪዛ ፕሮግራም ሲሆን፤ የአሜሪካ ቆንስላ ባለስልጣናት በቀጣይ የቱሪስት ቪዛ በማግኘት ወደ ሀገሪቱ ለሚገቡ ግለሰቦች ተመላሽ የሚሆን የ5 ሺሕ፣ 10 ሺሕ ወይም የ15 ሺሕ ዶላር ማስያዣ ሊጠይቁ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ይህም ተጓዡ የሚቆይበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ካሟላ ብቻ የሚመለስ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለአሁኑ ይህ እርምጃ የማላዊ እና የዛምቢያ ዜጎች ላይ ብቻ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም፣ ምናልባት ከቀጣይ ወር መጀመሪያ አንስቶ የአሜሪካ መንግሥት ለአብዛኛዎቹ የአጭር ጊዜ የቪዛ ማመልከቻዎች 250 ዶላር አዲስ የቪዛ ታማኝነት ክፍያ (visa integrity fee) ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አሐዱ

9 months ago