Logo
SeledaPost
በኢትዮጵያ ከለከፋ እስከ ግድያ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ

በኢትዩጵያ ህገ መንግስቱ የፆታ እኩልነትን ቢያረጋግጥም፣ የሴቶችን መብት እና ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ የተወሰኑ ህጎች ቢኖሩም፣ በተግባር ግን ከለከፋ እስከ ግድያ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል ሲሉ  የአዲስ ፖወር የጥብቅና ቡድን መሪ ወይዘሪት ሜሮን ደርቤ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የተዛቡ መረጃዎች ጨቋኝ ለሆኑ ስርዓቶች ክፍተትን በመፍጠር የሴቶችን መብት በመጣስ እንዲሁም የስነልቦናዊና አካላዊ ጥቃቶችን በማባባስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የፍትህ ሥርዓት የአፈፃፀም እና የተጠያቂነት ክፍተት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች እንዲበራከቱ እና በሴቶች መብት ተሟጋቾች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ መንገድ ከፍቷል ሲሉም ገልፀዋል።

በሴቶች መብት ላይ የሚሰራው አዲስ ፖወርሃውስ አርቲክል 35 እና ሲሃ ኔትወርክ ከ2ዐ17 ጥቅምት ጀምሮ በጋራ ዘመቻ ከለከፋ እስከ ግድያ የሴቶችን መብት ለማስከበር እና ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተለያዩ የውትወታ ስራዎችንና ውይይቶችን በማድረግ ቆይቷል፡፡ በ2017 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የመንግስት አካላት እና የህግ ባለሙያዎች የተሳተፉባቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ምክክሮች ተካሂደዋል፡፡በተደረገው ምክክር የሃይማኖት መሪዎች በአንድነት በመቆም፣ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ አስተምሮ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን እንደማይደግፍ እና ሃይማኖት ለሴቶች ክብር እኩልነት እና ፍትህ መሰረት ሆኖ ማገልገል እንዳለበት ገልፀዋል።

የሲቪክ ማህበራት እና የህግ ባለሞያዎችና መንግስታዊ ከሆኑ ድርጅቶች የተወጣጡ ተወካዮችም ሴቶች በነፃነት የሚኖሩበት ማኅበረሰብ ለመፍጠር ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ እና በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ፣ እንዲሁም የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመገንባት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የምክክሮቹ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከሰቱ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አንድ ወጥ የሆነ ሀገራዊ ምላሽ በአስቸኳይ መሰጠት እንዳለበት እና የፖሊሲ ማጽደቅ መተግበር ስራዎች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸውን አክለዋል።

seledadotio
seledadotio
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.