Logo
YenetaTube
በአዲስ ዓመት እና በዋዜማው የ3ሰዎች ህይወት በከሰል ጭስ አለፈ

ከሶስቱ ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ባልና ሚስት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አመት ዋዜማ እና በእለቱ በትራፊክም አደጋ የሞተሰው አለመኖሩን እና የወንጀል አደጋ አለመድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን ከወንጀል ውጭ በከሰል ጭስ መታፈን የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ጣፎ ኮዲሚኒየም እድሜቸው 75 አመት አዛውንት ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አመት ዋዜማ ምሽት በከሰል ጭስ ታፍነው ህይወታቸው አልፏል። በተመሳሳይ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ህዳሴ ትምህርት ቤት ጀርባ በአዲስ አመት መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 6 ሰአት ባለትዳሮች በከሰል ጭስ ታፍነው ሞተው መገኘታቸውን ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል።

ባለትዳሮቹ እሱ የ35 አመት ወጣት የትዳር አጋሩም ደግሞ የ27 አመት ወጣት መሆናን ፖሊስ የገለፀ ሲሆን በከሰል ጭሱ ሁለቱም ሞተው መገኘታቸውን ተነግሯል።

እንደ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ማብራሪያ ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ በበአል ሰሞን የሚደርሱ አደጋዎች አስቀድም ለመከላከል አባላቱን በገበያ ቦታዎች እና ግርግር በሚበዛባቸው በበቂ ማሰማራቱን እና አስቀድሞም ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራቱ በድንገት በከሰል ጭስ ከሞቱት ሰዎች ውጪ በትራፊክም ሆነ በሌሎች የወንጀልም አደጋዎች ሞት አለማጋጠሙን አሰታውቀዋል።

ፖሊስ በቀጣይ በመስከረም ወር በሚከበሩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በአላት ላይ ተመሳሳይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባል።

©️ዳጉ_ጆርናል

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.