Logo
FIDEL POST NEWS
የጋዜጠኞች ማህበር የታሰሩ የሸገር ራዲዮ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ

ሦስት የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ጋዜጠኞች ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 11:00 አካባቢ በስራ ገበታቸው ላይ እንዳሉ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተወስደው መታሰራቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ከባልደረቦቻቸው አረጋግጧል፡፡

ሦስቱ ጋዜጠኞች በፖሊስ የተያዙት ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን ጋዜጠኛ እሽቴ አስፋ በዕለቱ ሲለቀቅ ትዕግሥት ዘሪሁን እና ጋዜጠኛ ምንታምር ፀጋው አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተያያዘ የወጣውን ዘገባ ተከትሎ መሆኑን ባልደረቦቻቸው አረጋግጠዋል። ዘገባውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዘገባው "አድሎአዊ' እና 'አመፅ ቀስቃሽ ነው" በሚል ከጣቢያው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እንዲነሳ ትዕዛዝ መስጠቱን ለማወቅ ችለናል::

ዘገባው ከተጠቀሱት ገፆች የተነሳ ቢሆንም ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም የጸጥታ ሃይሎች ወደ ጣቢያው በኃይል በመግባት የፕሬስ ነፃነት እና የሙያ ደኀንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት በሚፈጥር መልኩ ጋዜጠኞችን አስረዋል። እስከ ዛሬ ማለትም ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ፍርድቤት እንዳልቀረቡም ጋዜጠኞች ሙያዊ ተግባራቸውን በመጣታቸው በወንጀል ሊጠየቁ እንደማይገባ ያምናል፡፡

በኤዲቶሪያል ይዘት ላይ ያሉ ልዩነቶች መፈታት ያለባቸው በህጋዊ እና ግልጽ በሆነ የቁጥጥር ሂደቶች ሊሆን እንደሚገባም ማህበሩ በአፅንኦት ይገልፃል::

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገገውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ተክብረው ጋዜጠኛ ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋው በእስቸኳይ እንዲፈቱ ማህበሩ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኀበር
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.