Logo
Getu Temesgen
የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ ሽልማት ይፋ ተደረገ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር የዲጂታል ሎተሪ ሽያጭን ለማበረታታት ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ድረስ ለገዙ ደንበኞች የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ ሽልማት እድለኛ የሆኑት በዕጣ ተለዩ።

በዚህም መሠረት

1ኛ እጣ የማኘ ቁጥር 7477716 የእድለኛው ቁጥር 30006063 ሲሆን ቢዋይዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሲሆን ፤

2ኛ እጣ የማኘ ቁጥር 7267109 የእድለኛው ቁጥር 2482333 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ባጃጅ
በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እድል ማውጫ በዛሬው እለት ወጥቷል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዚህ በፊት እንደተለመደው ብዙ ሰዎችን ሚሊየነሮች እንዳደረገ እና አሁን ደግሞ በዲጂታል ሽግግር ሂደት ተጨማሪ እድሎች መፈጠራቸው በእጣ አወጣጥ መርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የእጣ አወጣጥ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ያለም ተስፋንጋት፥ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እኩል በመራመድ ደንበኞቹን በየትኛውም ስፍራና በማናቸውም ጊዜ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ http://xn--ethiolottery-xt... እና በቴሌብር፣ በሲቢኢ ብር እና በሌሎች አማራጮች ሎተሪን በዲጂታል መንገድ የሚገዙበት ልዩ አሰራር አመቻችተናል ብለዋል።

የብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መድረኩ
በአሁኑ ጊዜ፣ ዋናው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በገበያ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዋንኛው ሽልማት 20 ሚሊየን ብር ነው። ቀጥሎም 10 እና 5 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል። የዚህ ሎተሪ ዕጣ ጳጉሜ 5 ላይ የሚወጣ ሲሆን፣ በወረቀትም ሆነ በዲጂታል መንገድ ትኬቱ ገቢያ ላይ ይገኛል።

የአዲሱ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ጳጉሜ 5 ቀን እንደሚወጣ የተገለጸ ሲሆን፣ ደንበኞች በወረቀትም ሆነ በዲጂታል መልክ ሎተሪውን በመግዛት ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.