Logo
FastMereja
‎ወጣቱ ባለጸጋ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ አስረከበ።

‎በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግቢ ህጻናትና ታዳጊዎች ላይ በርትቶ እየሰራ የሚገኘው ዳን ኢነርጂ በዛሬው ዕለት ነሀሴ 24/2017 ዓ/ም በአርት፣ በኮዲንግ እና መሠረታዊ የኮምፒተር ስልጠና ፣ ለሶስት ወራት የተማሩ ተማሪዎችን በሚያሥመርቅበት ዕለት በክብር እንግድነት የተገኘው ሁሌም በጎ ማድረግ የማይሰለቸው ወጣቱ ባለጸጋ ምረትአብ ሙሉጌታ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ከቦርሳ ጀምሮ ሙሉ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ለ300 ተማሪዎች አስረከበ።

‎በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአቬሽን ባለሙያው አቶ ዮናታን መንክር ፣ የባቡልኸይር መሥራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሀናን መሀመድና ራሱ ምረትአብ ሙልጌታ ለተማሪዎች ሀገርን ስለ መውደድና ታዳጊዎቹ ነገ ለሀገራቸውና ለወገናቸው የሚጠቅም ስራን ይሰሩ ዘንድ የሚያነቃቃ ትልቅ ትምህርት አዘል መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።

‎የዳን ኢነርጂ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ሀይሉ ለሰልጣኞቻቸው አቶ ምረትአብ ላበረከቱት ስጦታና ሽልማት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው ላለፉት 8 አመት በሺህ ለሚቆጠሩ ወጣቶችና ታዳጊዎች ነጻ የኮዲንግ ስልጠና ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጸው ለተማሪዎቹ የተደረገው ሽልማት አበረታች በመሆኑ ተማሪዎቹ በ2018 የትምህርት ዘመን እንዲጠነክሩ አሳስበዋል።

‎በመጨረሻም ከፍተኛ ውጤት ያሥመዘገቡ ተማሪዎች ከአቶ ምረትአብ ሙሉጌታ የ120 ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋለ።



11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.