በደብረሊባኖስ ገዳም ለሚከበረው ዓመታዊ ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ምዕመናን ይገኛሉ ተባለ
#ethiopia | አመታዊው የደብረ ሊባኖስ ገዳም ለማክበር የገዳሙ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት በጥምረት እየሰሩ እደሚገኝ ተገለፀ። ነሀሴ 24 በድምቀት የሚከበረው የአቡነ ተክለሃይማኖት እረፍት ምክንያት በማድረግ የበአሉ ተሳታፊ ምዕመናን በሰላም አክብረው እንዲመለሱ የገዳሙ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት በጥምረት እየሰሩ እንደሆነ ተገልጿል።
በየዓመቱ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚመጡ በርካታ ምዕመናን ፣ቱሪስቶች እና ካህናትን ደህንነት ለማስጠበቅና የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት በሰላም እንዲከበር እየተሰራ መሆኑን የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኢንስፔክተር ሀብታሙ ንጉሴ ተናግረዋል።
በበዓሉ ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ምእመናን እንደሚገኙ የገለጹት ሃላፊው የስርቆት እና የማጭበርበር ተግባራት ከተፈጸመ በአፋጣኝ ችሎት ውሳኔ ለማሰጠት ጊዚያዊ የአቃቢህግና ፍርድቤት ተቋቁሞ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም እና ጎንደር የተዘረጋው የፌደራል መንገድ ቁልቁለታማ፣ ጠመዝማዛና በአብዛኛው የተበላሸ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል። በገዳሙ ውስጥ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እና ከእምነቱ አውድ ውጭ የሚደረጉ አላስፈላጊ ነገሮችን እንዳይፈፀሙ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ፀባቴ አባ ሀብተማርያም ገልጸዋል ሲል ፊደል ፖስት ዘግቧል።

12 months ago