የትግራይ ክልል የአማራ ክልል ሚዲያ ተቋማት የአሸንዳን በዓል ለፖለቲካ ፍጆታ አውለዋል ሲል ከሰሰ
የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮን እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የአሸንዳን በዓል ታሪካዊና ባህላዊ ይዘቱን በመተው ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቅመውበታል ሲል ከሰሰ።
ቢሮው ባወጣው መግለጫ፣ የአማራ ክልል ተቋማት ‹‹የሶለል አከባበር በቆቦ›› በሚል ባነር በአሉ በራያ አላማጣ መከበሩን ማስተላለፋቸው፣ የኮረም፣ ኦፍላና ዛታ ወረዳዎች በአማራ ክልል ሥር እንደሆኑ ለማስመሰል ያለመ ፖለቲካዊ ጥረት ነው ብሏል።
ተመሳሳይ ድርጊት ከዚህ ቀደምም ተፈጽሟል ያለው ቢሮው፣ የፍስለታ ፆምን አስመልክቶ በምዕራብ ትግራይ፣ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የተላለፈውን ዜና እንደ ምሳሌ ጠቅሷል። በወቅቱ ‹‹በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የአድርሽኝ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በአል›› በሚል ርዕስ የተላለፈው ዘገባ፣ አካባቢውን የአማራ ክልል አካል አድርጎ ለማሳየት የተደረገ ሙከራ መሆኑንም አክሏል።
ይህ አይነቱ ዘገባ የአገሪቱን ህገ መንግስት የሚጥስ እና ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጋር የሚጣረስ ነው ያለው መግለጫው፣ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን እና አሚኮ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። በተጨማሪም፣ የፌዴራል መንግስት ጉዳዩን ተመልክቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
Seledadotio

12 months ago