ሉዊዚያና ውስጥ የኬሚካል ተቋም ፈነዳ
በአሜሪካ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሉዊዚያና ውስጥ በሚገኝ የመኪናው መለዋወጫዎች አምራች ፋብሪካ (auto plant) ላይ የደረሰ የኬሚካል ፍንዳታ፣ በሰፊው እሳት ከመቀስቀሱም በላይ ዘይትና ሌሎች ነገሮች ከሰማይ እንደ ዝናብ እንዲዘንቡ አድርጓል እየተባለ ነው።
ፍንዳታው የተከሰተው በሮዝላንድ ከተማ በሚገኘው ‘ስሚቲ’ስ ሰፕላይ ኢንክ’ በተባለ የመኪና ዘይትና ፈሳሽ አምራች ፋብሪካ ነው። ፍንዳታው ከፍተኛ የሆነ ጭስ ወደ ሰማይ እንዲወጣ ያደረገ ሲሆን፣ በአካባቢው ላይ የዘይትና የሌሎች ኬሚካሎች ርጭት አስከትሏል ነው የተባለው።
እየነደደ ያለው እሳት አደጋ ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት፣ ከፋብሪካው አንድ ማይል ራዲየስ ርቀት ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች የግዳጅ የመልቀቂያ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
የአካባቢው ባለሥልጣናት የፍንዳታውን መንስኤ እየመረመሩ ሲሆን፣ የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅና የአካባቢን ብክለት ለመቆጣጠር እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
እስካሁን በደረሰው አደጋ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሰው አለመኖሩ ታውቋል። የአደጋ ጊዜ ቡድኖች እሳቱን ለመቆጣጠር በስፍራው እየሰሩም ይገኛሉ ተብሏል።
Seledadotio

12 months ago