Logo
Getu Temesgen
ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ አመት ኤክስፖ 2018
#ethiopia | በኢትዮጵያ ውስጥ የካበተ ልምድ ካላቸው የኤቬንት አዘጋጅ ድርጅቶች አንዱ የሆነውና በአዳዲስ ስልቶችንና ዘይቤዎችን በማስተዋወቅ ቀደሚ የሆነው ታሜሶል ኮሚዩኒኬሸን፣ “ዘመን ገበያ አደስ ነገር በአደስ አመት ኤክስፖ 2018" የተሰኘውን የአዲስ ዓመት ኤግዚቢሸን አና ባዛር በአደስ አበባ ኤግዚቢሸን ማዕከል ከነሐሴ 17 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረሰ አንደሚያካሄድ አሳወቀ።

ለ2017 አዲስ ዓመት በደማቅ ሁኔታ የተዘጋጀውን "ሲቢኢ ብር ኘላስ አዲስ ነገር በአዲስ አመት ኤክስፓን”፣ አንደሁም በኢትዮ ቴሌኮም የታይትል ስፓንሰርነት የተዘጋጀውን የፋሲካ ኤክስፓን ጨምሮ በርካታ የተሳካላቸው ኤግዚቢሸኖቸን በማዘጋጀት ያለውን ልምድ በመጠቀም ታሜሶል ኮሚዩኒኬሸን የአገራችን የኤግዚቢሽንና ባዛር አሰራርን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ በማሳደግ የተሻሻሉ አና አዳዲስ ሀሳቦችን የማስተዋወቅ ባህሉን ቀጥሎበታል።

የታይትል ስፓንሰርሺፕ ሞዴልን ከማስተዋወቅ እንስቶ፣ ትላልቅ ሸልማቶች የሚያስገኙ የሎተሪ ዕጣዎችን ማውጣት፣ ነፃ ሸልማቶችንና ስጦታዎችን በመስጠት የምርቶችና አገልግሎቶች ትውውቅና ሸያጭን ማሳደግ አና መሰል የታሜሶል አቀራረቦች ባለፉት ኤክስፓዎች ላይ የአከፋፋዮችን፣ የስፓንሰሮችን አና የሚደያዎችን ትኩረት ስበዋል።

የኢትዮ ቴሌኮምን የታይትል ስፖንሰርነት እና ኤክስክሉሲቭ የክፍያ አጋርነትን በመጠቀም እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ተዋህዶ የተዋወቀውን የ“ዘመን ገበያ” የዲጂታል ግብይት መተግበሪያን በስፋት ለማስተዋወቅና በማሰብ ኤክስፖው “ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ አመት ኤክስፖ 2018" የሚል ሰያሜ መሠጠቱን በዛሬው እለት ኤክስፖዎን አስመልክቶ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ወደ ደጀታል የንግድ ሥርዓት አንድትገባ በማስቻል ታስቦ በኢትዮ ቴሌኮም አማካኘነት የተሰራው "ዘመን ገበያ'' መተግበሪያ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የንግድ ተቋማትን አና ሸማቾቹን በማገናኘት የኦንላይን ግብይት የሚቀላጠፍበትን መንገድ በኤክስፓው ወቅት በኤግዚቢሸኑ ጎብኚዎች፣ ሸማቾችና ተሳታፊዎች በስፋት ይተዋወቃል።

ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪም ፊንቴክ ኢንቨሰትመንት ግሩኘ ኃ የተ የግ ማ. ፣ ዩኒሊቨር ኢትዮጰያ፣ አይቴል ሞባይል፣ ቅደስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ ደሸን ባንክ፣ እንደሁም በሌሎችም በርካታ ድርጅቶች በስፓንሰርነት የሚሳተፍበት ከመሆናቸው ባሻገር የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የዝግጅቱ የክብር አጋር ነው፡፡

በዚህ ዓመት ከ300 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች በአዲስ ዓመት ወቅት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን የተለያዩ ምርቶች ይዘው ቀርበዋል።

ከትምህርት ቁሳቁስ እና የቤት ዕቃዎች አስከ ቴክኖሎጂ አና አላቂ አቃዎች ድረስ ሰፊ ምርጫ አለ። በዚህ ኤክስፓ ላይ ከአገር ውስጥ በተጨማሪም ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ከሌሎች አገራት የመጡ ኤግዚቢተሮች በመኖራቸው፣ ለግብይት ልምዶችን አለም አቀፍ ድመቀት ይጨምራል።

ሸማቾች ምቹ በሆነ ሁኔታ አንዲገበያዩ በማድረግ ነጋዴዎች በግብይት በሚመች መልኩ ተከካፍለው ይጠብቋቸዋል።

በተጨማሊም፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር፣ ዋነኛው መግቢያ በር ላይ የዘመን ገበያ ስቱዲዮ ተዘጋጅቷል። ምርት አቅራቢዎችና ነጋዴዎች ለ19 ቀናት በነፃ በዘመን ገበያ የኢ-ኮሜርስ አኘ ላይ ምርቶቻቸውን ማስመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪም ወደ ኤክስፓው መምጣት ያልቻሉ ደንበኞች የሚፈልጋቸውን ምርቶች በማዘዝ አንዲደርሳቸው ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ይህ ደግሞ ምርት አቅራቢዎች እና ነጋዴዎች ከኤግዚቢሸን ስፍራው ውጪ ገበያቸውን እንዲስፋፋ ይረዳል።

በኤክስፓው ግቢ ውስፕ፣ ፋይናንስ መንደር የሚል ልዩ ክፍል ተዘጋጅቷል፤ ይህ ክፍል ዋና ዋና ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማትን ያስተናግዳል። እነዚህ ተቋማት ኤቲኤም፣ የሞባይል ባንኪንግ ድጋፍ፣ ስለ ብድርና ቁጠባ መረጃ እና ሌሎች የገንዘብ ግብይቶችን ለማቅለል የሚረዳ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

ባህሎቻችንን ህያው ለማድረግ፣ በኤግዚቢሸን ማዕከል ውስጥ በቆሎ የሚሸጡ ተዘዋዋሪ ሻጮች ይኖራሉ። በተጨማሪም ከኋላ መግቢያ በር ልዩ የትዝታ ማስቀመጫ "ያ ዘመን" የተሰኘ ፎቶ ቤት ይኖራል። ጎብኚዎች በዚህ የትዝታ መንደር ላይ የማይረሱ ፎቶዎችን መነሳት ይችላሉ።

ቤተሰቦች የዚህ ኤክስፓ ዋነኛ ክፍል ናቸው። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ወላጆች በሰላም ገበያቸውን አንደጨርሱ እና በዓሉን አንዲያጣጥሙ፣ የልጆች መጫወቻ ስፍሁና ማቆያ ከበቂ ሞግዚቶች ጋር ተዘጋጅቷል።

ዋና ዋና ስፓንሰሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የንግድ ማህበረሰቡ ተወካዮች፣ አምባሳደሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች በሚገኙበት አጅግ ደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ቅደሜ ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከፈተው ይህ የዘመን ገበያ ኤክስፓ 2018 ዝግጅት እጅግ አስደሳች የመገበያያ፣ የመዝናኛ እና የባህል ህብረ ቀለማት መታያ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያየ የምግብ አይነቶች ቀርበዋል በተጨማሪም ጎብኚዎች የተለያዩ የምግብ ቅመሻዎችን የሚያገኙበትን የምግብና መጠጥ ቅመሻ ዞን ተዘጋጅቷል። ለምሳሌ ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ የክኖር ቅመማ ቅመምን በመጠቀም የተለያዩ ምግቦችን በማብሰል በቅመሻ ያቀርባሉ።

ከምግብ በተጨማሪ ሌላላው የዩኒሊቨሪ ብራንድ ሰንሲልክ ለሴቶች ነፃ የፀጉር ሳሎን አገልግሎት ሲሰጥ ፣ ላይፍ ቦይ ደግሞ መሠረታዊ የጤና ምርመራ የሚያደርግ የተሟላ የጤናና የመጀመሪያ እርዳታ ክሊኒክ ያቀርባል።

ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ሜሪ ጆይ ልማት ማህበር፣ ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅትና ካቲም የአካል ጉዳተኞች ማህበርን ጨምሮ በርካታ በጎ አድጎት ድርጅቶች ነፃ የኤግዚቢሸን ቦታ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.