በቦንጋ ከተማ የተገነባው አረንጓዴ ፓርክ ለአግልግሎት ክፍተት ሆነ
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በቦንጋ ከተማ የተገነባው፥ የቦንጋ ከተማ የኮርደር ልማት አካል የኾነው የአረንጓዴ ፓርክ ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆኗል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የቅርብ ክትትል ተገንብተው ለአግልግሎት የበቃው ፓርኩ በውስጡ መናፈሻ፣ የህጻናት መጫወቻ፣ የካፌ አግልግሎት እንዲሁም በፓርኩ ዙሪያ ጌጠኛ የእግረኛ መንገድ እና የመኪና መቆሚያ ያካተተ መኾኑ ተመላክቷል።
አጠቃላይ ግንባታውም ከ24.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተገለጸ ሲሆን የቦንጋ የከተማ አስተዳደር በባለቤትነት እንዲያስተዳድረው ተሰጥቷል።
በርክብክብ ስነ-ስርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የቦንጋ ከተማ እያከናወነ ያለው የከተማ ኮርደር ልማት ሥራ በክልሉ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን እንደሆነ ተናግረዋል።
የአረንጓዴ ፓርኩ ለአግልግሎት መብቃት፥የከተማ አስተዳደሩ በተሻለ አፈጻጸም እያከናወነ ለሚገኘው የክርደር ልማት ስራ ተጨማሪ አቅም የሚፈጠር መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ተሞክሮውን በመቀመር በሌሎች የከተማው ክፍሎች መሰል መዝናኛ ፓርኮች መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በፓርኩ ግንባታ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ያመሰገኑት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ አስማማው አደመ፥ የከተማ አስተዳደሩ የፓርኩን ውብት በዘላቂነት በማጠበቅ አግልግሎት እንዲሰጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በርክብክብ ስነ-ስርዓቱ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የአረንጓዴ ፓርኩ በቀጣዮቹ ቀናት በተሟላ መልኩ ለህዝብ አግልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል።
Southwest communication

12 months ago