Logo
YenetaTube
በስራ ላይ የዋለውን የብልሹ አሰራር መጠቆሚያ አፕልኬሽን ይጠቀሙ!! (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

ተቋማችን ከስነ-ምግባር ጥሰቶች ጋር የሚገናኙ ችግሮችን ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል መተግበሪያ /አፕሊኬሽን/ በስራ ላይ አውሏል፡፡

የሞባይል መተግበሪያው ተቋሙ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ማዕከላት በሚስተናገዱበት ወቅት ለሚገጥማቸው ከብልሹ አሰራር ጋር የተያያዙ ችግሮች በቀላሉ ጥቆማ እንዲያቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡

በተመሳሳይ ደንበኞች በሚያመቻቸው የቅሬታ ማቅረቢያ አማራጮች እንዲያቀርቡ የቴሌግራም ቦት እና ድረ-ገጽ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም አማራጮች የደንበኛውን ማንነት ሚስጢራዊነቱን ተጠብቆ መገልገል የሚችሉበት ነው።

መተግበሪያው በሁለት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

የጥቆማ ማቅረቢያ መተግበሪያውን ብሮዘር ላይ" https://eeuethics.et" ብላችሁ በመግባት እና በማውረድ አልያም እዛው ላይ ጥቆማቸውን ወይም ቅሬታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ፡፡

የመተግበሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ፍትሃዊ በማድረግ የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ የሚረዳ በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የብልሹ አሰራር ጥቆማዎችን እንድትሰጡ እንገልጻለን፡፡

Ethiopian Electric utility

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.