Logo
Getu Temesgen
የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውሃ ክምችት ህመሞችን በእርግዝና እቅድ መከላከል ይቻላል ተባለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ20 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሚደርሱ ሕፃናት የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina Bifida) እና ከልክ ያለፈ የጭንቅላት ውሃ ክምችት (Hydrocephalus) በሚባሉ የአፈጣጠር ችግሮች እንደሚወለዱ ተገለጸ።

ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ይህ አሃዝ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ነው። እነዚህ ህመሞች በዋነኝነት የሚከሰቱት የፎሊክ አሲድ እጥረት በመኖሩ ሲሆን፣ በእርግዝና እቅድ አማካይነት መከላከል እንደሚቻል በዘርፉ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የሆፕ ኤስቢኤች መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቤዛ በሻ ተናግረዋል።

የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውሃ ክምችት ህመሞች በዋነኝነት የሚከሰቱት የቫይታሚን B9 ወይም ፎሊክ አሲድ እጥረት ሲሆን፣ ይህ የአፈጣጠር ችግር የሚፈጠረው በእርግዝና የመጀመሪያ ወር ውስጥ ነው። በዚያ ወሳኝ ወቅት የፅንሱ የነርቭ ዘንግ እድገት ስለሚካሄድ፣ በእናቲቱ ደም ውስጥ በቂ የፎሊክ አሲድ መጠን መኖር ወሳኝ ነው።

የሕመሙ ስርጭት በኢትዮጵያ ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከ70 እስከ 75 በመቶ የሚሆኑት ሕፃናት በእነዚህ ችግሮች እንደሚወለዱ ወ/ሮ ቤዛ ተናግረዋል። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ለሕይወት ዘመን የአካል እና የአእምሮ ጤና ችግሮች ይጋለጣሉ ተብሏል።

ወ/ሮ ቤዛ እንዳብራሩት፣ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመምን ለመከላከል ከሁሉ በፊት እርግዝናን ማቀድ ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን የእናትየው የነርቭ ዘንግ እድገት የሚፈጠረው ፅንስ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 28ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ስለሆነ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ በቂ የፎሊክ አሲድ ክምችት በእናት ደም ውስጥ መኖር አለበት።

ይህን ለማረጋገጥ፣ ለእርግዝና የምትዘጋጅ ሴት ከመፀነሷ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በቂ የፎሊክ አሲድ እና ሌሎች ጠቃሚ የምግብ ንጥረ ነገሮችን መውሰድ እና በአመጋገብዋ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርባታል። የህመሙን ስርጭት ለመግታት፣ በዘርፉ በቂ ትኩረት እና ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን በዘርፉ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በትናንትናው እለት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ተገልጿል።

📷 Sisay Guzay

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.