Logo
Getu Temesgen
‎ወጣቱ ባለጸጋ ለባቡልኸይር በጎ አድራጎት 1 ሚሊየን ብር ሰጠ
#ethiopia | ‎«በረከትን ያገኘሁት በድሆች ፀሎት ነው» የሚለው ወጣቱ ባልፀጋ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለባቡልኸይር ድጋፍ በማድረግ ይታወቃል።

‎ራሱንና ጓደኞቹን በማስተባበር ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ፤ ለፆምም ሆነ ለበዓል አቅመ-ደካሞችን በመንከባከብና የበዓል ተደስተው እንዲውሉ በማድረግ በባቡልኸይር ቤተሰብ ዘንድ ይታወቃል።

‎በዛራው ዕለትም ወጣቱ ባለጸጋ ምረትአብ አዲስ መኪና ማርቼዲስ ቤንዝ መኪናውን ገዝቶ በምስኪኖች እና በአረጋውያን ለማስመረቅ በባቡልኸይር በተገበት ዕለት ነው ድንገተኛ የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታ የለገው።

‎ልገሳውን ወዲያውኑ በማስገባት ቃሉን የሞላው ወጣቱ ባለፀጋ ለሚስኪኖች ማድረግ ለራስ እንደማድረግ መሆኑን ተናግሯል።

‎ክስተቱ ታዳሚውን በእንባ ያራጨ፤ በተለይም የባቡልኸይር ተጠቃሚዎች በደስታ እንባቸው የፈሰሰበት እጅግ ልብ የሚነካ ክስተት ነበር።

‎የድርጅቱ መሥራችና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሀናን ሙሀሙድ የወጣቱ ባለፀጋ ድንገተኛ ስጦታ ከሚስኪኖች ጋር አስለቅሷቸዋል።

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.