ጾመ ፍልሰታ
እንኳን አደረሳችሁ
#ethiopia | አገራችንና ሕዝባችንን ሰላም አርጊልን፤ ፍቅር አላብሽልን፤ አብሮነት (አንድነት) አከናንቢልን - አሜን!
...
‹‹ፍልሰታ›› - ‹‹ፈልስ›› ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ መፍለስ ወይም አገር ለቆ ወደ ሌላ አገር መሰደድ ማለት ነው። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።
...
ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ 01 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
...
ጠቢቡ ሰለሞን … ውቢቴ ሆይ ተነሽ…. እነሆ ክረምት አለቀ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦቹም አበቡ ምድር ተገለጠች ወይኖቹም መዓዛቸውን ሰጡ…. ውቢት ሆይ ተነሽ… በማለት ስለ እመቤታችን ዳግም መነሳት በምሳሌ ተናግሯል። መኃ 2፣10-13
አቤቱ ፥ ጸሎቴን ስማ ፥ ጩኸቴንም አድምጥ ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና ፥ እንደ አባቶችም እንግዳ ነኝና ።"
መዝ . ፴፱ ፥ ፲፪ ( 39 ፥ 12 )
#መልካም ፆም

1 year ago