" በአደጋው እስካሁን 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - የሲዳማ ክልል ፖሊስ
➡️ " የወደቁ ተሽከርካሪዎችን በማንሳት መንገድ የማስከፈት ስራ እየተሰራ ነው ! "
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ ' ገመጦ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ፍቅሬ ዩእሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ዛሬ ከጠዋቱ 2:30 ገደማ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በቱላ ክፍለ ከተማ ' ገመጦ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋ 4 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
አደጋው የደረሰው ወደ ሀዋሳ መስመር ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ መስመሩን ስቶ ተሽከርካሪዎችን በመግጨቱ እንዲሁም እግረኞች ላይ በመውጣቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በአደጋው በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ እንዲሁም በእግረኞች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሀዋሳ ሪፌራል ሆስፒታል የተወሰዱ ሲህን ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሀይል ጋር በመተባበር ያደረገው አሰተዋፆ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
በአደጋው ምክንያት ተሽከርካሪዎቹ ዋናዉ መንገድ ላይ በመውደቃቸዉ ምክንያት ዋናዉ መንገድ ዝግ መሆኑንና በክሬን ተሽከርካሪዎችን የማንሳት ስራ እየተሰራ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawassa
tikvahethiopia

11 months ago