የታላቁ ኢንጂነር ሰባተኛ አመት ዝክር !!
( በየኔታ ቲዩብ ታዴ የማመይ ልጅ )
እለተ ሐሙስ ሐምሌ 19፣ 2010 ዓ. ም. መሃል አዲስ አበባ በሚገኘው መስቀል አደባባይ አሳዛኝ መርዶ ሰማን የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ የሆነዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በዚሁ አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ መባሉን ተከትሎ መላዉን ኢትዮጵያ አዘነ ተቆጣ እንባ አራጭቶ አለፈ ትንሽ ቆይቶም ተረሳ ይህ ክስተት ከማንምና ከምንም በላይ የጎዳዉ ኢትዮጵያን ነዉ ።
የታላቁ ሰዉ ለሃገሪቱ በርካታ የግድብና የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በ ኃላፊነት ለሰሩ ለ32 ዓመታት ሃገራቸዉን ያገለገሉ በተለይ ግድብ ግንባታ ጉልበታቸዉን፤ ጊዜያቸዉን፤ ገንዘባቸዉን እንደዉም ቤተሰባቸዉን ሁሉ በመተዉ ቀን ከለሊት ሲለፉ የነበሩ፤ ለሃገራቸዉ ሲሉ የተሰዉት ራሳቸዉን መስእዋትነት እስከመስጠት የደረሱት ኢንጅነር ስመኛዉ ክብር ይገባቸዋል ሁሌም ልንዘክራቸዉ ይገባል በሚል እነሆ ለዛሬው ከበዛዉ ታሪካቸው ጥቂቱን ለማነሳሳት ወደድን ።
ከአባታቸው አቶ በቀለ አይናለም እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘነቡ አብተው መስከረም 3 ቀን 1957 ዓ.ም. በቀድሞው ጎንደር ልፍለ ሀገር ጠዳ ወረዳ ልዩ ስሙ ማክሰኚት ከተባለ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በእንፍራንዝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በደሴ ቅዳሜ ገበያ ትምህርት ቤት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወልዲያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከታተላቸውን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ምኅንድስና ማግኘታቸው የሕይወት ታሪካቸው ይጠቁማል።
ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ በተባለው ቦታ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የታላቁ ኅዳሴ ግድብ እስከ ዕለተ-ሞታቸው በኃላፊነት ሲመሩ ቆይተዋል።
የ53 አመቱ አቶ ስመኘው ህይወታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ 32 ዓመታት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ኃይል ህዝብና መንግስትን አገልግለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኮተቤ ማሰልጠኛ ከ1978 እስከ 1991 ኢንስትራክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ1991 እስከ 1992 ደግሞ በዋናው መስሪያ ቤት የኢንጂነሪንግ ድፓርትመንት ክፍል መሃንዲስ ሆነው ሰርተዋል፡፡
ኢንጅነር ስመኘው አገሪቱ የጀመረችውን የኃይል ልማቱ ዘርፍ በመቀላቀል ከ1992 1993 የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ካውንተር ፓርት ኢንጅነር፣ከ1997 እስከ 2002 የጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አስተባባሪና እና ስራ አስኪያጅ ፣እንዲሁም ከ2003 እስከ እስከ ሀምሌ 19፣ 2010 ድረስ ደግሞ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ነብሳቸው እስኪያልፍ ድረስ በማገልገል ላይ የነበሩ እጅግ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሙህር ነበሩ።
ሰው ከቤተሰብ ርቀው፣ እንደ ሌሎች አባቶች ከልጆቻቸው ጋር ሳይጫወቱ፣ ቀዝቀዝ ባለ አየር ሳይናፍሱ አደራቸውን ለመወጣት ኳተኑ። በኢትዮጵያውያን ታምኖ ጎድሎ መገኜት ከባድ ነበርና የራሳቸውን ደስታ ወደ ጎን ትተው የአገርን ደስታ ለማስቀደም ደከሙ፡፡ ከሙያ አጋሮቻቸውና ከኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ከመሠረት አንስተው ሥራውን ከፍ አደረጉ፡፡
ዳሩ ግን የጀመሩትን መቋጨት አልቻሉም፡፡ ሥራውን ጨርሰው ይሞገሱበታል በተባለው አደባባይ ላይ ሕይወታቸው አልፎ ተገኙና ኢትዮጵያዊያን ደነገጡ፡፡ ሀዘኑም ከፍ አለ፡፡ ከሁሉም ግን ከጉባ በረሃ ተመልሰው ፍቅር እስኪሰጧቸው ሲጠባበቁ ለነበሩ ቤተሰቦቻቸው ሐዘኑ ከባድ ነበር፡፡ በሀሩር ሥር የተደበቀን መብራት ፈንጥቀው በጨለማ ውስጥ የኖረውን የኢትዮጵያዊ ለማስደሰት የጀመሩት ውጥን መስቀል አደባባይ ላይ ተቋጨ፡፡ ለኢትዮጵያውያንም የተጀመረ ሥራ፣ የጎመራ ፍቅር፣ የተባ አንድነት፣ ከፍ ያለ መተሳሰብ ትተው እንዲጨርሱት በመንፈስ አበርትተው በአንደበታቸው ሳይሰናበቱ ላይመለሱ አሸለቡ፡፡
የኢትዮጵያውያን ተስፋ በስሎ ሳያዩት፣ አብርቶ ሳይመለከቱት በጎን የሀገር ፍቅር፣ በጎን ደግሞ የቤተሰብ ፍቅር እንዳቃጠላቸው፤ በላይ የጉባ በረሃ እንደገረፋቸው ወደማይቀርበት ተሰናበቱ፡፡
ኢንጂነር ስመኘው ለዘመናት የተመኘነውንና የተመኙትን ፈፅመው ባያሳዩንም የማይደፈር ደፍረው፣ ያልተጀመረ አስጀምረው አጋምሰው የድካማቸውን ፍሬ ሳያዩ እስከወዲያኛው ተለዩን ።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ የእሳቸው ስም፣ የእሳቸው ስም ሲነሳም የህዳሴው ግድብ በመነሳቱ የሚታወቁት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ስመኘው በቀለ (ኢንጂነር)፣ ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ማለዳ በመስቀል አደባባይ ሞተው መገኘትና የአማሟታቸዉ ሁኔታ ሚስጥር ሳይፈታ ሰባት አመት ሞላው ።
ታላቅ ጀግና ናቸዉና መቼም አንረሳቸዉም 🙏🙏

1 year ago