Logo
FastMereja
የምርመራ ዘገባ ጋዜጠኛ ብርሀኑ ወልደ ሰማያት አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ አቀረበ።
***
*ሁለቱ ኩላሊቶቹ አገልግሎት አቁመዋል።

ጋዜጠኛ ብርሀኑ ወልደሰማያት ይባላል፡፡ ለረጅም ጊዜ በቀድሞ ራዲዮ ፋና በአሁኑ FBC ውስጥ ሲሰራ የነበረና በኋላም ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሲቋቋም ለዓመታት በዘጋቢ ፊልሞች በልዩ ልዩ ወቅታዊ የትንታኔ ዜናዎች በምርመራ ዘገባዎች በማቅረብ ይታወቃል።
በዋልታ ቴሌቪዥን "ዋልታ ምርመራ" በተሰኘ ፕሮግራሙ በሰብዓዊ መብት፣ መልካም አስተዳደርና በሙስና ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የምርመራ ዘገባዎችን ያቀርባል።የተቋሙ የምርመራ ዘገባ አዘጋጅ አንዱ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ወልደሰማያት ነበር።"የምርመራ ዘገባ መሐንዲስ" በማለት የሚጠሩት ጥቂቶች አይደሉም።
በ2013 ዓ.ም. በጦር ግንባር ራያ ግንባር በግራካሶ በአላማጣ በኮረም በማይጨዉ በሰቆጣ በራያ ቆቦ...ወዘተ የነበረዉን የጦርነት ዘገባ ከስፍራው ሲያቀርብ የነበረና በተደጋጋሚ ከመድፍና ከታንክ ቅንቡላ መትረፍ ችሏል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዩቲዩብ ሚዲያ አራዳ ዴይሊ ሲሰራ የኖረና በአሁኑ ሰዓት በሀሌታ ቲዩብ ዓለምአቀፍና ሀገራዊ ዘገባዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነዉ።
የአንጋፋዉ ጋዜጠኛ ብርሀኑ ወልደሰማያት ሁለቱ ኩላሊቶቹ አገልግሎት አቁመዋል።ስለሆነም በአስቸኳይ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልጋል። ለዚህ ኩላሊት የሚሰጠው ሰዎችና የምርመራ ውጤት ውጭ ተልኮ መጥቶ ከዛም በኋላ ውጭ ሀገር ንቅለ ተከላው የሚደረግ ሲሆን ለዚህ ሁሉ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስፈልገዉ ሆኗል።በአሁኑ ሰዓት በሆስፒታል ዉስጥ ይገኛል።ሆስፒታል ከገባ 11 ቀናት አልፎታል።ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነዉ ጋዜጠኛ ብርሀኑ ወልደሰማያት በአሁኑ ሰዓት የወገኖቻችንን እገዛና እርዳታ በመጠየቅ ላይ ስለሚገኝ ሁላችንም በሚቻለን ሁሉ እናግዘዉ።

ስለሆነም በጎነትንና መልካምነትን የተላበሳችሁ ሁሉ (ማገዝ ለምትፈልጉ)
ጋዜጠኛ ብርሀኑ ወልደሰማያት መኮነን
1000000177777
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
5178906082011
ዳሽን ባንክ
የምትችሉትን ሁሉ እንድታግዙት በፈጣሪ ስም ጥሪዉን አቅርቧል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.