“12ኛ ተጫዋች ለመሆን ተዘጋጅተናል” – የባህር ዳር ነዋሪዎች
#ethiopia | ባህር ዳር ከ5 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨዋታ ታስተናግዳለች።
የጣናዋ ሙሽራ ባህር ዳር የዋልያዎቹ የድል ቦታ በመሆኗ ትታወቃለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በከተማዋ በሚገኝበት ወቅትም ባህር ዳር የፌስቲቫል ዓይነት ድባብ ይኖራታል።
ይህ ስሜትም ከጨዋታው ዋዜማ ጀምሮ በከተማዋ ታይቷል። በኮሪደር ልማቷ የከተማዋን ውበት ካሳደጉት ዘንባባዎች እስከ ጎዳናዎቿ ድረስ የዋልያዎቹ ደጋፊነት የሚያሳይ ድባብ ተፈጥሯል።
በየአቅጣጫው በእግራቸው የሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች የጨዋታውን ድባብ ያደምቃሉ። አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማትን የያዙ ቁሳቁሶችና የብሔራዊ ቡድኑ መለያዎችን የለበሱ ደጋፊዎችም በከተማዋ ተስተውለዋል።
ያነጋገርናቸው የባህር ዳር ነዋሪዎችም በስታዲየም ተገኝተው ዋልያዎቹን ለማበረታታት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“በስታዲየም ተገኝተን እናበረታታለን፤ እንደ 12ኛ ተጫዋች ለቡድናችን ኃይል ለመሆን ዝግጁ ነን” ሲሉም ተናግረዋል።
ዋልያዎቹን በሜዳ ተገኝተው ማበረታታት የለመዱት ደጋፊዎች፣ ብሔራዊ ቡድኑ ከሴኔጋል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ እስከመጨረሻው ድረስ ድጋፋቸውን እንደማይቆጥቡ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስታዲየም ካደረጋቸው 8 የነጥብ ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ መሸነፉ የስታዲየሙን ታሪክ የበለጠ ልዩ ያደርገዋል። በተለይም አፍሪካ ላይ ከሚታወቁ ቡድኖች አንዱ የሆነውን አይቮሪኮስትን 2 ለ1 ያሸነፈበት ጨዋታ ከማይዘነጉ የባህር ዳር ስታዲየም ድሎች መካከል ይጠቀሳል።
ዛሬ ደግሞ ዋልያዎቹ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንን ይገጥማሉ። በማለዳውም በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ጨዋታውን ለመታደም በባህር ዳር ስታዲየም መግቢያ በሮች ላይ ተሰልፈዋል።
በሜዳ ላይ የሚደረገው የዋልያዎቹ ፍልሚያ ዋነኛ ቢሆንም፣ የባህር ዳር ደጋፊዎችም በድምፃቸውና በድጋፋቸው ስታዲየሙን ለሴኔጋል ቡድን አስቸጋሪ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሀብታሙ ካሴ
#ethiopia #bahirdar #afcon #senegal #matchday #football #sports #ebc #ethiopia #bahirdar #afcon #senegal #walias #matchday #football #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 days ago