Logo
Getu Temesgen
በሣውላ ከተማ ሁለተኛው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ በታላቅ ድምቀት በመካሄድ ላይ ነው
#ethiopia | በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ሁለተኛው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችና አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻያለው ገላን፣ የዞኑ የስራ አስተባባሪዎችና አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተሳትፎ በማድረግ ላይ ናቸው።

የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዋነኛ ዓላማ ለጎፋ አንድነትና ሰላም በጋራ እንሮጣለን በሚል መልእክት ሲሆን፣ በተጨማሪም የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ ባህላዊ እሴቶችንና ጭፈራዎችን ለዓለም ማስተዋወቅና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚከበረው በዓል የመጀመሪያ ቀን ውድድሩ በባህላዊ ጨዋታዎችና በህዝባዊ ተሳትፎ አምሮ የተጀመረ ሲሆን፣ ከዞኑ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተሰበሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የጎዳና ላይ ውድድሩ ሲጠናቀቅ ለአሸናፊ መደበኛ ሯጮች የሽልማት ስነ ስርዓት እንደሚከናወንም ታውቋል።
#sawla #gofa #gofazone #streetrun #masqala #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

13 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.