13 days ago
በሣውላ ከተማ ሁለተኛው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ በታላቅ ድምቀት በመካሄድ ላይ ነው
#ethiopia | በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ሁለተኛው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችና አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻያለው ገላን፣ የዞኑ የስራ አስተባባሪዎችና አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተሳትፎ በማድረግ ላይ ናቸው።
የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዋነኛ ዓላማ ለጎፋ አንድነትና ሰላም በጋራ እንሮጣለን በሚል መልእክት ሲሆን፣ በተጨማሪም የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ ባህላዊ እሴቶችንና ጭፈራዎችን ለዓለም ማስተዋወቅና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚከበረው በዓል የመጀመሪያ ቀን ውድድሩ በባህላዊ ጨዋታዎችና በህዝባዊ ተሳትፎ አምሮ የተጀመረ ሲሆን፣ ከዞኑ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተሰበሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የጎዳና ላይ ውድድሩ ሲጠናቀቅ ለአሸናፊ መደበኛ ሯጮች የሽልማት ስነ ስርዓት እንደሚከናወንም ታውቋል።
#sawla #gofa #gofazone #streetrun #masqala #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago
በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት መንትዮችን ለወለደችው እናት ማህበራዊና ቁሳቁሳዊ ድጋፍ ተደረገ
#ethiopia | በጎፋ ዞን ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን በሰላም የተገላገለችውን እናት የዞኑ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተው ጠይቀዋል።
የሳውላ ከተማ ከንቲባ አቶ በላይነህ ባህሩ እና የጎፋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንቲ ጎሽመን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በሆስፒታሉ በመገኘት ለእናቲቱ እና ለህፃናቱ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በመጀመሪያ ዙር የሚሆኑ የምግብ ቁሳቁሶችን፣ የንፅህና መጠበቂያዎችን እና አልባሳትን በስጦታ አበርክተዋል።
አመራሮቹ የህፃናቱን እና የእናቲቱን ሁኔታ በቀጣይነት በመከታተል የዞኑ እና የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በሆስፒታሉ በተደረገላቸው የህክምና ክትትል መሰረት በአሁኑ ወቅት እናቲቱም ሆነ አራቱ ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
ይህ አጋጣሚ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ሲሆን፣ የተደረገው ድጋፍም የማህበረሰቡን ደግነት እና ለእናቶችና ህፃናት የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያል።
#gofa #sawla #health #maternalhealth #ethiopiannews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments