የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት ከኢኮኖሚ ሕልውና እስከ ቀጣናዊ ደኅንነትና የጋራ ብልፅግና
************************
የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት ከታሪክ፣ ከጂኦፖለቲካ እና ከአሁናዊው የኢኮኖሚ እድገት ጋር የተያያዘ የሕልውና ጥያቄ ነው።
ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ፣ በዓለም ላይ ካሉ የባሕር በር ከሌላቸው ሀገራት በሕዝብ ቁጥር የመጀመሪያዋ ስትሆን፣ ይህ ሁኔታ በሀገራችን የረጅም ጊዜ ዘላቂ ልማት፣ ንግድና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
የሀገራችን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መስፋፋት ቀጣይነት ያለውና አስተማማኝ የባሕር በር መዳረሻን ግዴታ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ በጂቡቲ ወደብ ላይ ብቻ የተንተራሰ በመሆኑ ከፍተኛ የኪራይና የወደብ አገልግሎት ወጪ እንድታወጣ እና የንግድ ተወዳዳሪነቷ እንዲጎዳ አድርጎታል።
ቀይ ባሕርና የኤደን ባሕረ ሴላጤ የዓለም ንግድና የኃይል አቅርቦት የሚያልፍባቸው ዋና ዋና መስመሮች እንደመሆናቸው መጠን፣ የራሷ የባሕር በር ወይም አስተማማኝ የወደብ ባለቤትነት ማግኘት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንድታደርግ ያስችላታል።
ቀይ ባሕር የታላላቅ ሀገራት ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት የሚንጸባረቅበት ስትራቴጂካዊ ቀጣና እንደመሆኑ፣ በአካባቢው የሚታዩ የባሕር ላይ ዘረፋ፣ የህገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውር እንዲሁም የፅንፈኝነት ስጋቶች የአካባቢውን ደኅንነት እየተፈታተኑት ይገኛሉ።
በአፍሪካ ትልቅ ወታደራዊና የሕዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ በባሕር ደኅንነት ጥበቃ ላይ መሳተፏ ለቀጣናው መረጋጋት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የባሕር በር ጥያቄው የሌሎችን ሀገራት ሉዓላዊነት በሚጋፋ መልኩ ሳይሆን፣ በሕግና በድርድር ማዕቀፍ የሚተገበር በመሆኑ ቀጣናዊ ትስስርን ማዕከል ያደረገ፣ የጎረቤት ሀገራትን ጥቅም የሚያከብር እና በቀይ ባሕር ላይ የጋራ ደኅንነትን የሚያረጋግጥ የወደፊት አቅጣጫ መከተል ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ብልፅግና መሠረት ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #redsea #hornofafrica #maritimesecurity #ethiopianeconomy #regionalintegration

16 days ago