በቀይ ባሕር ላይ የተደቀነው የደኅንነት አደጋ እና የማይተካው የኢትዮጵያ ሚና
*******************
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በቀይ ባሕር እና በባብ ኤል-መንደብ ስትራቴጂያዊ መተላለፊያ ላይ እየተባባሰ የመጣውን ወታደራዊ ውጥረት የተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
ኮሚሽኑ በንግድ መርከቦች እና በኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በማስመልከት ያወጣው ይህ ይፋዊ መግለጫ የቀጣናውን አጣዳፊ የደኅንነት ስጋት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የዓለም አቀፍ ንግድ ከፍተኛው ድርሻ በሚንቀሳቀስበት በዚህ የባሕር መስመር ላይ የተከሰተው ቀውስ በአቅርቦት ሰንሰለት፣ በኃይል አቅርቦት ደኅንነት እንዲሁም በመላው አፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ የከፋ አደጋ ደቅኗል።
ወታደራዊ ፍጥጫዎቹ ለአህጉራዊ እና ለቀጣናዊ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፈተና መሆናቸውን የጠቀሰው የአፍሪካ ኅብረት አደጋው ወደ ምሥራቅ አፍሪካ እንዳይስፋፋ አጥብቆ አስጠንቅቋል።
አሁን መላው ዓለም እና የአፍሪካ ኅብረት እየሰጉበት ያለው በቀይ ባሕር ቀጣና የተደቀነ የደኅንነት ክፍተት፣ ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት ቀድማ ስትተነብየው እና ስታስጠነቅቅበት የነበረ እውነት ነው።
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ሽብርተኝነትን እና ጽንፈኝነትን በመዋጋት ረገድ የከፈለችው መሥዋዕትነት በታሪክ የጎላ ስፍራ አለው።
በሶማሊያ ተንሰራፍቶ የነበረውን አሸባሪው አል-ሸባብን በመመከት እና አካባቢውን በመታደግ ረገድ የነበራት የፊት መስመር ተሰላፊነት ኢትዮጵያ ለራስ ደኅንነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላም የቆመች ጠንካራ የደኅንነት መሠረት መሆኗን አስመስክሯል።
በዚህ ታሪካዊ እውነታ ላይ የተመሠረተው የባሕር በር ፍላጎት ከ130 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ ህልውና እና ልማት ከማስፈልጉ ባሻገር፣ የቀይ ባሕር እና የምሥራቅ አፍሪካን ሰላም በጥንካሬ ለማስጠበቅ የሚደረግ የጋራ ጥረት አካል ነው።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር ኃይል እንዲኖራት ማድረጉ ለቀጣናው የተሟላ የደኅንነት ዋስትና ይሰጣል።
ኢትዮጵያ ያላት ጠንካራ እና የተፈተነ የሠራዊት አቅም፣ የፀረ-ሽብር ትግል ልምድ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅሟን ከዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ነፃነት ጋር አስተሳስራ መመልከቷ የመርከቦችን ደኅንነት ከሚያውኩ ወንበዴዎች፣ አሸባሪዎች እና ሕገ-ወጥ ታጣቂዎች ለመጠበቅ የማይተካ ሚና እንድትጫወት ያደርጋታል።
ግዙፍ የሕዝብ ቁጥር እና እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ በባሕር መስመሩ ደኅንነት ላይ ቀጥተኛ ባለድርሻ መሆኗ ተሳትፎዋን ታማኝ፣ ተግባራዊ እና ዘላቂ ያደርገዋል።
ይሁን እንጂ ይህን አሳታፊ እና ሰላማዊ ጥያቄ እንደ ኤርትራ እና ግብፅ ያሉ ሀገራት በበጎ ካለመመልከታቸውም በላይ፣ ኢትዮጵያን ያገለሉ ጥምረቶችን ለመፍጠር ሲሯሯጡ ተስተውለዋል።
እነዚህ ሀገራት የባሕር ዳርቻ ተጋሪነትን ብቻ መሠረት ባደረገ ጠባብ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ያገለለ የቀይ ባሕር ጥምረት ፈጥረው ቢንቀሳቀሱም፣ አሁን በቀይ ባሕር ላይ የተከሰተውን የቀውስ ማዕበል እና የሁቲ ጥቃቶችን ለመግታት አቅምም ሆነ ፍላጎት አጥተው ተስተውለዋል።
በውኃ ወሰን ላይ ብቻ የተመሠረተው ይህ አግላይ አካሄድ በቀጣናው ያለውን የደኅንነት ክፍተት ከመጨመር ባለፈ ምንም ዓይነት ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አለመቻሉን የመሬት ላይ እውነታው አረጋግጧል።
ይህ የሚያሳየው በቀይ ባሕር እና በባብ ኤል-መንደብ መስመር ላይ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን ብቸኛው መፍትሔ ኢትዮጵያን ያሳተፈ የጋራ የደኅንነት መዋቅር መገንባት ብቻ መሆኑን ነው።
በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ዘላቂ ሰላምን ማረጋጋት የሚቻለው የኢትዮጵያን ሕልውናዊ ስጋት፣ የደኅንነት አቅም እና ታሪካዊ ሚና ያገናዘበ አሳታፊ የደኅንነት ማዕቀፍ ሲተገበር ብቻ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #redsea #seaaccess #africa #maritimesecurity

17 days ago