Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ማን ምን አለ?
#ethiopia | የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የውጭ ሀገራት መሪዎች የዲፕሎማቲክ መሪዎችና እና አምባሳደሮች የመልካም ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል።

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልእክት ለኢትዮጵያውያን እና አውስትራሊያውያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አዲሱ አመት የሰላም የብልጽግና እና የደስታ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በተመሳሳይ የአውስትራሊያ የተቃዋሚ መሪ የሆኑት አንገስ ቴለር በበኩላቸው እንኳን ለ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤመሰበርገር
አውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጎን እንዳለ በመግለፅ የሰላምና የደስታ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።

የካሜሩን አምባሳደር ኤዉምቡዌ ሞኖኖ አዲሱ ዓመት የተስፋ እና የእድገት እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ የዕንቁጣጣሽ እና የእስራኤል "ሮሽ ሀሻናህ" አዲስ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት መዋላቸውን በመጥቀስ "መልካም አዲስ ዓመት ዕንቁጣጣሽ" ብለዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) አምባሳደር አብደላ ሀሰን አልሻምሲ
የሀገራቸውን እና የኢትዮጵያን ጠንካራ ወዳጅነት በማንሳት የሰላምና የፍቅር ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።

የጀርመን፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስሪላንካ፣ የየመን እና ማሌዥያ ዲፕሎማቶች እና ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #ethiopiannewyear #enkutatash #ethiopia #newyear2019 #peaceandunity #diplomacy

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.