13 በመቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ እናቶች የልጅነት እርግዝና ተጋላጭ ናቸዉ ተባለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ መሰረታዊ የሚባሉ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የልጅነት ጋብቻ ፣ግርዛት ፣ አካላዊ አዕምሮአዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች መሆናቸው ተነግሯል።
በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሚያገቡ ሴቶች ቁጥር በጣም ከፍተኛ ሲሆን ይህም 13 በመቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ እናቶች የልጅነት እርግዝና የሚፈጠርባቸው መሆኑን በፕላን ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዶክተር ምስክር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ትዳር ውስጥ ከሚገቡት ታዳጊዎች መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት አምስተኛ ክፍል ሳይደርሱ ትምህርት የሚያቋርጡ መሆናቸው ተነግሯል።
በ2016 ከ15 እስከ 49 ባሉ ሴቶች ላይ በተሰራ ጥናት በሶማሊ 99 በመቶ፣ በአፋር ደግሞ 91 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች መገረዛቸውን ተረጋግጧል ። በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጸጥታ ችግሮች ህጉ እንዳይተገበር እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንዳይደርጉ እንቅፋት ስለሚሆን በታሰበው ልክ ጥቃቶችን ማስቆም እንዳልተቻለ ገልጸውልናል።
የጠለፋ ፣ የአስገድዶ መደፈር ፣ የስነልቦና እና የአዕምሮ ጥቃቶች ቀላል የማይባሉ መሆኑን እና ሁሉም የሚመለከተው አካል በሙሉ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነግረውናል።
ለሴቶች ስጋት የሚሆንባቸው ሳይሆን የሚደግፍ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ እና ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በቀላል መንገድ የሚለቀቁ ሳይሆን ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይህም ለሌሎች መማሪያ እንደሚሆን ዶክተር ምስክር ጌታሁን ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

1 year ago