የቀድሞ ኮከብ የባንክ ምስጢር ወጣ
#ethiopia | የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኢቶ በከባድ የሙስና እና የገንዘብ ምዝበራ ክስ ተመሠረተበት።
የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኢቶ ከሩሲያ ወደ ግል የባንክ ሂሳባቸው የተላከ ከ500,000 ዩሮ በላይ ገንዘብን በተሳሳተ መንገድ ተጠቅሟል በሚል መከሰሱን የፊፋ ሕጋዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ።
ኢቶ ለመልካም አስተዳደር ብልሹነት እና ለገንዘብ ምዝበራ ውንጀላ መጋለጡን የፊፋ የፍርድ ቤት መዝገቦች እና ሕጋዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ።
በክሱ ወደ ኳታር ብሔራዊ ባንክ የግል የባንክ ሂሳባቸው ሁለት የተያዩ ክፍያዎች ቀጥታ እንዲገቡ የተደረጉበት ደረሰኞች በክስ ሰነዱ ላይ መቅረባቸው ተገልጻል።
ይህ ገንዘብ ለምን ዓላማ እንደዋለ እና ወደ ግል ሂሳብ እንዲገባ የተደረገበት ሕጋዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ግልጽ አለመሆኑ ክሱን ጠንካራ ያደርገዋል።
የፊፋ ፕሬዚዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ቅርብ ወዳጅ የሆነው ኢቶ ስሙ የተነሳው ፊፋ ሊተገብረው አቅዶት በነበረውና በኋላ ላይ በተሰረዘው የዓለም ዋንጫ ሽያጭ ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀረበ የፍርድ ቤት መዝገብ ላይ ነው።
በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ሳሙኤል ኢቶ ከተፈጸሙት የገንዘብ ዝውውሮች ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ የሕግ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና ምርመራዎች ከፊቱ ተደቅነውበታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #samueletoo #fecafoot #fifa #caf #footballnews #breakingnews #cameroonfootball #sportsnews

27 days ago