ከነጣጣይ ትርክት ወደ የጋራ ሀገር፦ የታሪክ እውነታ እና የነገዋ ኢትዮጵያ
*******************
የታሪክ አተረጓጎም ማህበራዊ ትስስርን የመገንባትም ሆነ የማፍረስ አቅም ያለው፤ የሀገርን የሰላም እና የልማት ጎዳና በቀጥታ የሚወስን ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው።
የታሪክ ሰነድን የአንዱ ወገን ድል እና የሌላው ወገን ሽንፈት ማሳያ አድርጎ የማቅረብ አጥፊ አካሄድ በማኅበረሰቦች መካከል የቂም እና የጥርጣሬ ግንብ ሲገነባ ቆይቷል።
ዛሬ ግን ታሪክን ከርካሽ የፖለቲካ መጠቀሚያነት በማውጣት የሁሉም ማኅበረሰቦች አስተዋጽኦ እና ተሞክሮ የሚንጸባረቅበት አካታች የጋራ ሀብት መደረጉ ለአዲሱ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ እርምጃ ሆኗል።
የቆዩ የታሪክ ቁርሾዎች እና ስብራቶችን ከማባባስ ይልቅ በሰለጠነ መንገድ ተቃኝተው ለነገ የጋራ መግባባት እና ዕድገት ትምህርት እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል።
በዚህ ረገድ፣ የሀገር ታሪክ የተወሰኑ ቡድኖች የብቻ ገድል ሳይሆን የሁሉም ማኅበረሰቦች የጋራ ፈተና፣ መሥዋዕትነት፣ ስኬት እና ውርስ መሆኑን ማስረጽ ተችሏል።
የነጠላ ትርክት ወይም ልዩነቶችን የማጥፋት ፍላጎት ዘላቂ ሰላምን እንደማያመጣ በተግባር የተረጋገጠ እውነት ነው፤ ስለዚህም የሁሉም ማኅበረሰቦች ቋንቋ፣ ባህል እና ማንነት በእኩልነት ሲከበር እና ሲጎለብት ብቻ፣ የጸና ሀገራዊ አንድነት ይፈጠራል።
የብሔር ማንነት እና ሀገራዊ ዜግነት ተቃራኒዎች ሳይሆኑ፣ አንዱ ሌላውን የሚደግፉ እና የሚያጠናክሩ የመደመር ምሰሶዎች ናቸው።
ጠንካራ እና የማይበገር ሀገረ መንግሥት ሊገነባ የሚችለው ሁሉንም ድምፆች እና እሴቶች በእኩል ደረጃ በሚያስተናግድ ሰፊ ምህዳር ውስጥ ብቻ ነው።
የትናንትን የታሪክ ስብራት በፍትሐዊነት መጠገን፣ ነገ በጋራ ለሚገነባው ሀገር እና ለሚረጋገጠው ብልጽግና ትልቅ አበርክትዎ አለው።
ታሪክ የፖለቲካ መቆመሪያ እንዳይሆን መታደግ፣ መጪው ትውልድ በትናንት የታሪክ ዕዳ ምትክ የነገን ብሩሕ ተስፋ እንዲወርስ ያስችለዋል።
በምክክር የጸና የጋራ መግባባት ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ሙሉ ተሳታፊ እና እኩል ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋል።
የአንድ ወገን ነጠላ ትርክት አክትሞ ታሪክ ሁሉንም ማኅበረሰቦች ያካተተ ሀብት ሲሆን፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ የማይናወጥ የጋራ መግባባት እና የብልጽግና መሠረት ሆኖ ያገለግላል።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #democracy #multiculturalism #nationaldialogue #nationalconsensus #nationalunity #peacebuilding #sharedhistory #ebc #ebcdotstream

1 month ago