Logo
FastMereja
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

👉በሳፋሪኮም ኤምፔሳ ባቡልኸይርን የምንረዳበት መንገድ ይፋ ተደረገ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትላንትናው ዕለት ሰኔ 27/2017 ዓ/ም ለባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት የ2 ሚሊየን ብር እና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄለፑት ፣ ዶ/ር አንዱአለም አድማሴ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ውጭ ጉንኙነት ዋና ሀላፊ እና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሰራተኞች ተገኝተው ጉብኝት አካሂደዋል።

ከጉብኝት በኋላም የምሳ ግብዣ ፕሮግራም አከናውነዋል ባቡል ኸይር በማዕከሉ ውስጥ ከሚረዳቸው በተጨማሪ ቤት ለቤት የሚረዳቸውን ወገኖችም በየቤታቸው በመሄድ ጠይቀዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዊን ቫንሄለፑት በመልዕክታቸው

"ይህ 2 ሚሊየን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ሲሆን በቀጣይነትም ድጋፋችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ከ2 ሚሊየን ብር በተጨማሪ በሰራተኞቻችን አማካኝነት የተሰባሰበውን የአልባሳት ድጋፍም ይዘን መጥተናል።

እንዲሁም Mpsa በተሰኘው አፕሊኬሽን አማካኝነት ድጋፍ አድርጉ የሚለው ለይ ባቡል ኸይርን ደግፉ የሚለውን በመጫን መላ ኢትዮጵያውያን ባቡልኸይርን መደገፍ እንዲችል ቀላል መንገድ አመቻችተናል።

ለእዚህ ደግሞ ለ10 ሚሊየን ደንበኞቻችን በሙሉ ባቡልኸይርን እንዲረዱ ለአንድ አመት የሚቆይ የአጭር መልዕክት ካንፔን እድል ሰጥተናል ለእዚህ ካንፔን ማሥጀመሪያ እኔ 50 ሺ ብር ከኪሴ አስገብቻለሁ በማለት ከንፔኑን አስጀምረውታል።

ለአንድ አመት የሚያገለግል አንሊሚትድ የሆነ ነጻ ዋይፋይ ከእነ አክሰሱ አስረክበናል ብለዋል ስራ አስፈጻሚው።

ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም ባቡልኸይርን ስጎበኝ ወደ ቀደመ ህይወቴ ኡጋንዳ ላይ ያየሁትን እና ያደረኩትን ድጋፍ አስታውሶኛል ኡጋንዳ ላይ ልጆቻቸውን ያለ አባት የሚያሣድጉ እናቶችን እጎበኝ ነበር የልብስ ስፌት መኪናም እየገዛሁ ሰጥቼ ስራ አስጀምሬያለሁ ያን ነገር እዚህ በማየቴ አስደስቶኛል የባቡል ኸይር መሥራቾችና በጎ ፈቃደኞች በሙሉ ልትመሠገኑ ይገባል በራሴ በግሌ 5 የልብስ መስፊያ ማሽን አምጥቼ ለማሥረከብ ቃል እገባለሁ ብለዋል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጥቅምት 11 ቀን 2012 በመዝገብ ቁጥር 4513 ተመዝግቦ በሴቶች ብቻ የተመሰረተ የሰብዓዊ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በተለይም ዜጎች ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ጤናማ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ለማስቻል በቀን ሁለት ጊዜ የተዘጋጀ ምሳ እና እራት እንደ ቤተሰባቸው ብዛት እየመገበ ዛሬ ላይ ከ5000 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦችን የምግብ ዋትስ እና የጤና መድህናቸውን ማረጋገጥ የቻለ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ሴቶችና እናቶች ቋሚ የስራ እድሎችን ፈጥሯል።

በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶችና ሴቶችን በተለያዩ የሙያ ስልጠናዎች እንደ ልብስ ስፌት፣ የኮምፒዪተር ስልጠና ፣ የጫማ ስራ ስልጠና በመስጠትና በማስመረቅ የስራ እድሎችን ጭምር በማመቻቸት ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን እንዲደግፉ ማድረግ ችሏል።

ዛሬ ላይ ባቡል ኸይር በአበበ ቢቂላ የመመገቢያ ማዕከልና የሙያ ስልጠና ማሳያ ስፍራ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ የልዩ ስልጠና ማዕከል እና የህፃናት ማቆያ፣ በኦሎንኮሚ ለወጣቶች የስራ እድልን እየፈጠረ የሚገኝ የብሎኬት ማምረቻ፣ በቤተል አለም ባንክ የባቡል ኸይር የምገባና የአረጋዊያን መጠለያ ሁለገብ ማዕከል ፕሮጀክት ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት እየተከናወነ እንደሚገኘው ተነግሯል።
የከርሰ ምድር የንጹህ መጠጥ ውሃ በራስ ሙሉ ወጪ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፣ የመብራት ዝርጋታም በተመሳሳይ መልኩ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ግንባታ አቅም እንዲሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት አምስት አመታት የተራቡትን በማጉረስ፤ የታረዙትን በማልበስ፤ እንዲሁም ለበርካታ ወገኖቻችን የስራ እድል በመፍጠር በበርካታ የሰብአዊነት ተግባር ተሰማርቶ የበኩሉን በጎ አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኝ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.