ለታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ዘመናዊ ህንጻ ሊገነባለት ነው
አዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ የሚገኘው አንጋፋው የኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርርስ መሆኑ ተሰማ። ከዚህ ቀደም የሆቴሉ ጀርባ ያለው የስብሰባ አዳራሽ መፍረስ የጀመረ ሲሆን፣ ዋናው ሕንፃም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተገልጿል። በቅጥር ግቢው ውስጥ የነበሩ ሰባት የንግድ ሱቆችም አስቀድመው ተነስተዋል።
ይህንን ባለ አምስት ፎቅ ሆቴል ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በ2002 ዓ.ም በ94 ሚሊዮን ብር ገዝተውት ነበር። አሁን ላይ በቦታው ላይ ዘመናዊ ሕንፃ ለመገንባት ታቅዷል። ሆቴሉ ሲፈርስ 140 ሠራተኞች ሥራቸውን እንደማያጡና በባለቤቱ ሌሎች ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚዛወሩ ተነግሯል።

5 hours ago