(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲስ አበባ ብሄራዊ ቲአትር አካባቢ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሆቴል በከተማው ውስጥ እድሜ ጠገብ ከሆኑ የሆስፒታሊቲ አገልግሎት መስጫዎች አንዱ ነው፡፡ የዚህ ሆቴል መከፈት ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ጋር ይያያዛል፡፡ እ.ኤ.አ በ1963 አዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ምስረታ ለማስተናገድ ዝግጅት ስታደርግ ትልቁ ስጋት ለተሳታፊዎች የሚሆኑ በቂ ሆቴሎች አለመኖራቸው ነበር፡፡ ከዚህ በመነሳት ለአፓርታማነት ሲገነባ የነበረው ይህ ህንፃ ወደሆቴልነት እንዲቀየር የተደረገ ሲሆን በዚህም ለምስረታው አዲስ አበባ የተጓዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ተስተናግደውበታል፡፡ ይህ 6 አስርት አመታትን ያስቆጠረው ሆቴል አሁን ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት ጊዜ መቃረቡን ፎርቹን ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው በአሁኑ ወቅት ከሆቴሉ ጀርባ የሚገኙት ቦታዎችና ግንባታዎች በመፍረስ ላይ ሲሆኑ ሆቴሉ እስከሚቀጥለው ጥቅምት ፈርሶ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ይህ ሆቴል የሚፈርሰው በምትኩ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ሊሰራበት ነው፡፡ የሆቴሉ ባለቤት የሆነው ቢኬ ግሩፕ ከመንግስት ከገዛው በኋላ የማስፋፊያ ስራ ወዲያውኑ የጀመረ ሲሆን ከይዞታው 4000 ካሬ ሜትር በተጨማሪ በ5500 ካሬ ሜትር ላይ ትልቅ ህንፃ የመገንባት እቅድ እንዳለው አስታውቆ ነበር፡፡
ከመነሻው እቅዱ ባለ63 ፎቅ ህንፃ የመገንባት ቢሆንም በአካባቢው ካሉት ትልልቅ ህንፃዎች አኳያ ፕላኑን ለማሻሻል ውሳኔ ላይ ቢደርስም የተሻሻለውን እቅድ ግን ገና ይፋ አላደረገም፡፡ እንደዘገባው ባለ 5 ህንፃ የሆነው ኢትዮጵያ ሆቴል በአሁኑ ወቅት 109 ክፍሎች ያሉትና በ3 ፈረቃ የሚሰሩ 140 ሰራተኞች ያሉት ነው፡፡ የሆቴሉ አስተዳደር ከሳምንታት በፊት ሰራተኞቹን ሰብስቦ ሆቴሉ በቅርቡ እንደሚፈርስ የነገራቸው ሲሆን እስከዛው ግን ስራቸውን እንዲቀጥሉ ገልፆላቸዋል፡፡ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሰራተኛ እንደተናገረው ሆቴሉ ከፈረሰ በኋላ የሰራተኛ ቅነሳ እንደማይኖር ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡
ከሰራተኞቹ ውስጥ ብቃትና ልምድ ያላቸው በፊት ግሎባል ሆቴል ወደሚባለውና አሁን ኢትዮጵያ ሆቴል ቁጥር ሁለት ወደሆነው እንደሚዘዋወሩ የተነገራቸው ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በቢኬ ግሩፕ ውስጥ ወደሚገኙ ሌሎች ሆቴሎችና ድርጅቶች እንደሚገቡ ተገልፆላቸዋል፡፡ የአቶ በላይነህ ክንዴ ንብረት የሆነው ቢኬ ግሩፕ በአዲስ አበባ ካለው ቁጥር ሁለት ኢትዮጵያ ሆቴል በተጨማሪ በአዳማ የራስ ሆቴል ባለቤት ከመሆኑም በላይ በባህር ዳር ከተማ ሂልተን ሆቴል የገነባ ነው፡፡ እንዲሁም በቅርቡ በደቡብ ወሎ ዞን ሎጎ ሀይቅ ሪዞርትን ስራ ማስጀመሩ ይታወቃል፡፡
ቢኬ ግሩፕ በ7 ከተሞች ውስጥ 22 ድርጅቶች ያሉትና ከ5ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድር ትልቅ ድርጅት ሲሆን የድርጅቱ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰጠኸኝ እንግዳ የኢትዮጵያ ሆቴልን ጉዳይ በተመለከተ ተጠይቀው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ለጋዜጣው ሲናገሩ ‹‹ገና ምንም ስራ ባልተጀመረበት ሁኔታ ስለማፍረስና ስለአዲሱ ህንፃ የምናገረው የለም›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ግን የኢትዮጵያ ሆቴልን መፍረስ ተቋማቸው መከላከል እንደማይችል ተናግረዋል፡፡ በቅርስነት የተመዘገበ አለመሆኑን ገልፀውም ‹‹ቅርስ ያልሆነ ነገር እኛን አይመለከተንም›› ብለዋል፡፡

13 hours ago